በአልጋዎቻቸው ላይ ዝጓቸው እና ደብድቧቸው

(መሐመድ ለሴቶች ያለው ዝቅተኛ አመለካከት)

በDavid Wood

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

በአረቡ ዓለም ውስጥ የሚገኘው የሴቶች ደረጃ በእስልምና ላይ ለሚሰነዘሩ ትችቶች አንዱ ምንጭ ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም ያሉ ሴቶች በብዙ ጋብቻ፣ በሴቶች መሸፋፈን እና በሙስሊሞች አገሮች ውስጥ ባሉት ሌሎች እኩልነቶች አለመኖር እንዲሁም በእስልምና ፈጣን መስፋፋት ላይ ስጋት ስለአደረባቸው ሁኔታውን በትኩረት እየተከታተሉ ነው፡፡ የምዕራባውያን ተቺዎች እስልምና የሴቶችን የበታችነት ያስተምራል በማለት የእስላም አስተማሪዎችን ሲወነጅሉ፣ ብዙውን ጊዜ ሙስሊሞች የሚመልሱት፣ በወንዶችና በሴቶች መካከል የሚኖር ማንኛውም እኩል አለመሆን የባህል ልዩነት ውጤት ነው እንጂ የእስልምና ሕግ አይደለም በማለት ነው፡፡

ቁርአን ለሴቶች አዲስ የሆነ ደረጃን አስቀምጦላቸዋል፣ እንዲሁም ደግሞ ከአረቢያ በፊት ሊያልሙት የሚችሉትን መብትም ሰጥቷቸዋል፣ ስለዚህም አንዴ ድሮ በነበረውና አሁን ባለው መካከል ልዩነት የሚመስል ነገር ያለው ለምንድነው? መልሱ የሚገኘው በእስልምና መሰረታዊ ትምህርት ውድቀት መከሰት ነው፡፡ ይህም የሆነው በሞንጎሎች ወረራ ሙስሊሙ ዓለም ላይ በደረሰው ጥፋትና ከአስራ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እስከ አስራ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በሆነው የክሩሴድ ጦርነት በኋላ ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተነሱት ባህሎች የሚታወቁት በአካባቢ ባህልና ልማዶች ላይ የተመሰረቱ ሆነው ነው፣ ይህም ከእውነተኛው የእስልምና እሴት በበለጠ መልኩ ነው፡፡ በእስላም ዓለም ውስጥ ያለው የሴቶች አያያዝ የሞንጎል ወረራዎችና እና የክሩሴዶች ውጤት ነው፡፡ የክርስትያኖችና የሞንጎሎች ተፅዕኖዎች ባይኖሩ ኖሮ የሙስሊም ሴቶች በመሐመድ የተሰጣቸውን ዋና ስፍራ አሁንም ይደሰቱበት ነበር፡፡ የሙስሊም አቃቤ እምነታውያን መሐመድ ለሴቶች መብት ታላቅ አስተዋፅዖን ያደረገ ዋና ሰው እንደሆነ ሰዎችን በማሳመን በኩል አስደናቂ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ በእርግጥም መሐመድ ሴቶችን ነፃ አውጥቷል የሚለው ክርክር አንዳንዶችን ያሳመናቸው ‹የሴቶችን መብት በተመለከተ ዓለም ካየቻቸው ሰዎች መካከል መሐመድ እጅግ ታላቁ ሰው ነው› በማለት ነው፡፡ የፆታ ልዩነቶችን በተመለከተ የሚነገረው የመሐመድ ማሻሻያዎች ገለፃ በሙስሊሞች ጽሑፎች

ውስጥ ሞልቷል፡፡ ከሰባተኛው መቶ የክርስትያን ዘመን አንስቶ በጣዖት አምላኪዎች አረቦች ይደረግ የነበረውን አሰቃቂውን የሕፃናት ሴቶችን ግድያ እስልምና አጥፍቷል፣ የጣዖት አምልኮን ስለማቆም በተመከለከተ ግልፅ የሆኑ መመሪያዎችን ሰጥቷል፣ በሚስቶች ላይ ይተገበር የነበረውን ገደብ የለሽ የወንዶች መብት አግዷል፣ እንዲሁም ሴቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ እኩልነት ከወንዶቸ ጋር እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

የአረብ ሰብዓዊ መብት ለዚያን ጊዜው ሁኔታ እንኳን በጣም ኋላ ቀር ነበር፡፡ ሴቶች ውድ የሆኑ ጥቂት መብቶች ነበሯቸው፡፡ አንዲት ሴት በጋብቻ የምትሆነው የባል ንብረት ነበር፣ ሴት በአባቷ የተደረገውን የጋብቻ ስምምነት በምንም መንገድ ልትቃወም አትችልም ነበር፡፡ በሚስት ላይ ይደረግ የነበረው ብልግና በጣም በሰፊው ይታወቅ ነበር ለዚህም ሴቶች ምንም ዓይነት እርዳታ ከየትም አያገኙለትም ነበር፡፡ አንዲት ሴት ባሏ ከሞተ በኋላ በወንድ ልጇ ልትወረስና የወንድ ልጇ ሚስት ልትደረግ ትችላለች፡፡ የሕፃን ሴት ልጆች ግድያ የሕፃን ሴቶች እንደተወለዱ በሕይወት በአሸዋ ውስጥ የመቀበራቸው ልምምድ በማህበረ ሰቡ ውስጥ በጣም የተለመደ ነበር፡፡ በማህበረ ሰቡ ውስጥ የብዙ ሴቶች መኖር እንደከባድ ሸክም ይቆጥር ነበረ፡፡ ሴቶች የመፍታትም ሆነ የታወቀ ውርስ መብት እንዲሁም በእርግጥ የፖለቲካ ድምፅ የመስጠት መብት አልነበራቸውም፡፡ አንድ ወንድ ሴትን ያለምንም ምክንያት መፍታትና ያለምንም ሳንቲም ለማስቀረት ይችል የነበረ ሲሆን አንድ ወንድ ሊኖረው ለሚችለው ሚስት ምንም የቁጥር ገደብ አልነበረውም፡፡ ወንዶች ሚስቶቻቸውን የሚንከባከቡበት ሕግና ስርዓት አልነበረም፡፡ የአረብ ባህል ሁልጊዜ ይናገር

የነበረው ሴቶች የሃይማኖትም ሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ወስጥ ተሳትፎ እንዳያደርጉ ጨቁኖ በመግዛት ነበር፡፡

ወንዶች በሴቶች ላይ የነበራቸው የበላይነት በማንኛውም መንገድ በጣም በስፋት ታዋቂነትና ተቀባይነት የነበረው አመለካከት ነበረ፡፡ መሐመድ ያንን አመለካከት ወንዶችና ሴቶች በእግዚአብሔር ፊት በማንኛውም መንገድ እኩል ናቸው በሚል አባባል ለወጠው፡፡ የመሐመድንና የተልእኮውን ዘገባ መመርመር በወንዶችና በሴቶች ሕይወት መሻሻል ውስጥ ስላመጣው መሻሻል አዲስ ገፅታን ለማግኘት ያስችላል፡፡ነው፡፡ [Emerick, pp. 8-9, 141, 142.]

ቁርአን ሴቶች ንብረትን እንዲወርሱ ግልፅ የሆነ መብትን ይሰጣቸዋል፣ በፍርድ ቤት ሕግ ፊት ቀርበው የመመስከርን ግዴታ እንዲሁም የመፋታትን መብትም ይሰጣቸዋል፡፡ በሕፃናት ሴቶች እንዲሁም በሴቶች ላይ የሚፈፀመውንም ዓመፅ በግልፅ ይከለክላል እንዲሁም በጋብቻና በማህበራዊ ጉዳይ የሚደረጉ ግድጃዎችን (በሴቶች ላይ) ... ሴቶች የግለሰብ እና የማህበረሰብ ሃይማኖታዊ ግዴታዎች መወጣታቸውን በማረጋገጥ በኩል፣ በማህበራዊ ቅጣቶች፣ በስነምግባር መጣሶች ላይ ሴቶችም እኩል የሆነ ሃላፊነት ነበራቸው፡፡ እንዲሁም ከፍተኛ መልካምነትን ወይንም ውለታንም በማምጣት በኩል (በማስገኘት) እኩል የሆነ ዕድል፣ ገነት መግባታ እንዲሁም ለአላህ ቅርብ መሆንን ተሰጥቷቸዋል ይህም በሚችሉት ሁሉ መንገድ ‹መልካም የሆነውን ለመመስረትና ክፉ የሆነውን ለመቃወም› ከጣሩ ነው፡፡ Ziauddin Sardar and Merryl Wyn Davies, The No-Nonsense Guide to Islam (Oxford:New Internationalist Publications, 2004), pp. 121, 122. መሐመድ የአረቢያን ሴቶች በተወሰነ መልኩ ከፍ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም፣ ይህ እውነታ በሌሎች አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ደመና እንዲጥልበት ለመፍቀድ አንችልም፣ እነዚህም፡-

1. ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲመቱ መሐመድ ፍቅዷል፤

2. የሴቶችን የአዕምሮ ችሎታ ዝቅተኝነትን በመደጋግም አውጇል፤

3. ከሞት በኋላ የሚኖረው የሴቶች ሁኔታ እጅግ በጣም የጠበበ መሆኑን አስተምሯል፤ እንዲሁም ደግሞ

4. በመሐመድ መሰረት የሴቶች የጦር ምርኮኞች በወንዶች መደፈር ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ መሐመድ በማህበረ ሰቡ ውስጥ ያመጣው ጠቃሚ ተፅዕኖ ከሚገልፁት አንቀፆች ጋር ከዚህ በላይ ያሉት ነጥቦች ጋር አብረው ሲደባለቁ፣ እነዚህ አራት እውነታዎች መሐመድ ለሴቶች የነበረውን በጣም ትክክለኛና ሁሉን አቀፍ ስዕል ላይ እንድንመጣ ይፈቅዱልናል፡፡ አራት እውነታዎች

እውነታ 1፡- ቁርአን ወንዶች ሴቶችን እንዲታዘዙዋቸው እንዲመቷቸው ይፈቅዳል (ወይንም ምናልባትም ያዛል)፡፡ አንድ ሚስት ባሏን የማትሰማው ከሆነ፣ ባሏ ሊገስፃት ይገባል፡፡ ያ የማይሰራ ከሆነ ደግሞ እሱ እርሷን አልጋ ለይታ እንድትተኛ ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ ሚስት የባሏን ስልጣን የማታከብር ከሆነ ወደ ሌላ አልጋ እንድትገለልም ከተደረገ በኋላ እንኳን ባል የተነገረው በአካል እንዲደበድባት (እንዲቀጣት ነው)፡፡ የሚከተለውን ጥቅስ በተመለከተ የተሰጡትን ሦስት ትርጉሞች ተመልከቱ፡፡ ‹ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፤ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አላህ ባስጠበቀው ነገር

ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ እነዚያንም ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው፣ በመኝታዎችም ተለዩዋቸው፣ (ሳካ ሳታደርጉ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅነውና፡፡› 4.34፡፡ የአማርኛው ትርጉም፡፡ ‹ምክንያቱም አላህ ወንዶቹን በሴቶቹ ከበላይ እንዲልቁ አድርጎአቸዋልና፣ እንዲሁም ደግሞ ሴቶችን ለመርዳት ንብረታቸውን ስለሚያፈስሱ ነው፡፡ በጣም ጥሩ የሆኑት ሴቶች ታዛዦቹ ናቸው፣ አላህ በምስጢር የጠበቀውን ነገር የሚጠብቁት ናቸው፡፡ ዓመፅ ያደርጋሉ ብለህ የምትፈራቸውን እነሱን ገስፃቸው እንዲሁም ለብቻቸው በአልጋ ላይ ተዋቸው፣ እንዲሁም ግረፏቸው፡፡ ከዚያም የሚታዘዙህ ከሆነ በእነሱ ላይ ክፉን ነገር ለማድረግ አትፈልግ፡፡ እነሆ አላህ በጣም የከበረ ነው ታላቅ ነው፡፡› (የፒክታል ትርጉም 4.34)፡፡

‹ወንዶች የሴቶች ባለቤቶች ናቸው ምክንያቱም አላህ ከእነሱ አንዳንዶቹን ሌሎቹን እንዲበልጡ አድርጓልና፣ እንዲሁም ከንብረታቸው ለእነሱ ያወጣሉና፣ መልካም ሴቶች ስለዚህም ታዛዦች ናቸው የማይታየውን የሚጠብቁ ናቸው አላህ እንደጠበቀው፣ እንዲሁም እንደሚከዱ የምትፈሯቸውን፣ ተቆጧቸው፣ እንዲሁም በመኝታ ቦታ ላይ ብቻቸውን ተዋቸው እናም ምቷቸው፤ ከዚያም የሚታዘዟችሁ ከሆነ፣ በእነሱ ላይ ተንኮልን አትፈልጉ በእርግጥ አላህ ታላቅና ከፍ ያለ ነው፡፡› (የሻኪር ትርጉም 4.34)፡፡

‹ወንዶች የሴቶች ጠባቂዎችና ባለቤቶች ናቸው ምክንያቱም አላህ ወንዶቹን ከሴቶቹ ይልቅ ጥንካሬን ስለሰጣቸው ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ካላቸው ላይ ሴቶቹን ስለሚደግፏቸው ነው፡፡ ስለዚህም ፃድቃን የሆኑት ሴቶች በጣም ትጉ የሆኑ ታዛዦች ናቸው እንዲሁም ጠባቂዎች ናቸው (የባሎቻቸውን) አለመኖር፡፡ አላህ እንዲጠብቁ የሚፈልገውን ነገር፡፡ ታማኝ አለመሆናቸውን የምትፈራቸውን ሴቶች በተመለከተ እንዲሁም ጥሩ ፀባይ የሌላቸውን (በመጀመሪያ) ገስፁዋቸው፣ (ቀጥሎም) ከእነሱ ጋር አልጋዎችን አትጋሩ፣ (ቀጥሎም) ምቷቸው (በመጠኑ)፡፡ ነገር ግን መታዘዝን ከመለሱ በእነሱ ላይ ምክንያትን አትፈልጉባቸው (ለማስቸገር)፤ አላህ በጣም ታላቅ ነውና፣ ታላቅ ነውና (ከሁላችሁም በላይ)፡፡› (የዩሱፍ አሊ ትርጉም 4.34)፡፡

ይህንን አንቀፅ በተመለከተ የሙስሊም ተርጓሚዎች ብዙ ታግለዋል እናም ግልፅ የሆነውን ትርጉሙን ለማለስለስ ብዙ መንገዶችን ፈልገዋል፡፡ ለምሳሌም ያህል አሊ በትርጉሙ (በመጠኑ) የሚልንና በመጀመሪያው አረብኛ ላይ የሌለውን ቃል ጨምሮበታል፡፡ ይሁን እንጂ አሊ አስፀያፊ ሆኖ ያገኘውን የቁርአን ክፍል እንዲያለሰልሰው ብንፈቅድለትም ጥቅሱ አሁንም ባሎች ሚስቶቻቸውን እንዲደበድቡ ይፈቅድላቸዋል፡፡ ስለሆነም በእግዚአብሔር የመጨረሻውና ታላቁ ነቢይ አማካኝነት የባሎች በስልጣን መባለግ የተፈቀደ ነው፣ ምናልባትም አስፈላጊም እንኳን ነው፡፡ በሚስቶቻቸው ላይ ባሎች ጉዳት እንዳያደርሱ ሕግ ያላቸው ዘመናዊ መንግስታት በቁርአን ላይ ባለው የአላህ ቃል መሰረት መተላለፍን አድርገዋል፡፡ (የአላህን ቃል ጥሰዋል ማለት ነው)፡፡

እውነታ 2:- በመሐመድ መሠረት ሴቶች የተፈጥሮ እውቀት ይጎድላቸዋል ምክንያቱም አዕምሮአቸው ጉድለት አለበትና፡፡ በእርግጥ ይህ መግለጫ ያለተግዳሮት አልቆየም፡፡ መሐመድ ለስሙ መታወቅ ሲል ለሴቶች ስለ እውቀት ችግራቸው እንዲጠይቁት ፈቅዶላቸው ነበር፡፡ ለእነዚህም ጥያቄዎች የእሱ መልሶች በሚገባ ገላጮች ናቸው፣ (መሐመድ አለ)፡ ኦ ሴቶች በሲዖል ነዋሪዎች መካከል እናንተን በብዛት ስላየኋችሁ ምፅዋት መስጠትና ብዙ ይቅርታ መጠየቅ አለባችሁ፡፡ በእነሱም መካከል የነበረች አንዲት ብልህ ሴት እንዲህ አለች፡- የአላህ መልክተኛ የእኛ ሴቶች በሲዖል ውስጥ በብዛት የሆኑት ለምንድነው? በዚህ ላይ ቅዱሱ ነቢይ ያስተዋለው፡ እናንተ ብዙ መሐላን ታደርጋላችሁ እንዲሁም ለባሎቻችሁ መልካም አይደላችሁም፡፡ በተፈጥሮ እውቀት የጎደለና በሃይማኖትም የወደቀ ነገር ግን (በተመሳሳይ ወቅት) የጠቢባንን ጥበብ የሚዘርፍ ከእናንተ በቀር ማንንም አላየሁም፡፡ በዚህ ላይ ሴትየዋ የሚከተለውን አስተያየት ሰጠች፡ በእኛ የተፈጥሮ እውቀትና ሃይማኖት ላይ ምን ችግር አለበት? እሱም (ቅዱሱም ነቢይ) ያየው፡ የእናንተ የተፈጥሮ እውቀት ጉድለት (የሚታወቀው ከእውነታ) የሁለት ሴቶች ማስረጃ ከአንድ ወንድ ማስረጃ ጋር እኩል ከመሆኑ እውነታ ላይ ነው፣ ያ ነው የተፈጥሮ እውቀት የጎደላችሁ የመሆኑ ማስረጃ፡፡ Sahih Muslim, Abdul Hamid Siddiqi, tr., Number 142. እንዲሁም ነቢዩ (የአላህ በረከትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) የሚከተለውን ተናገረ፡ ‹የሴት ምስክርነት የአንድ ወንድ ግማሽ አይደለምን?› ሴቲቱም አለች፡ ‹አዎን›፡፡ እሱም አለ፡ ‹ይህም የሆነበት ምክንያቱ አዕምሮዋ ጎደሎ ስለሆነ ነው›፡፡ Sahih Al-Bukhari, Dr. Muhammad Matraji, tr. (New Delhi: Islamic Book Service, 2002), Number 2658. እዚህ ላይ ያሉትን ነጥቦች አስተውሉ፤ በመጀመሪያው ክፍል ውስጥ ሴቶች የተፈጥሮ እውቀት ይጎድላቸዋል ያለውን መሐመድ ያረጋገጠው፣ የእነሱ ምስክርነት የአንድ ወንድ ግማሽ ነው በሚለው አባባሉ ነው፡፡ ነገር ግን በሁለተኛው ክፍል ውስጥ፣ መሐመድ በፊት የተናገረውን ያረጋገጠው የሴት ምስክርነት እንደ ግማሽ ወንድ ምስክርነት ነው በሚለው ሐሳቡ ነው፡፡ ይህም ሴቶች የአዕምሮ ጉድለት ስላለባቸው ነው በማለት ነው፡፡ ይህም የሽክርክሮሽ ምክንያታዊነት የተለመደ ምሳሌ ነው፡፡ በመሐመድና በጣም አስተዋይ በሆነ ጠያቂ መካከል ስለተደረገ ውይይት እንደሚከተለው ልንገምት እንችላለን፡-

ጠያቂ፡- ‹ኦ መሐመድ ሲዖል በሴቶች የተሞላ የሆነው ለምንድነው?›

መሐመድ፡- ‹የተፈጥሮ እውቀት ስለሌላቸው ነው›፡፡

ጠያቂ፡- ‹ሴቶች የተፈጥሮ እውቀት የሌላቸው መሆኑን እንዴት አወቅህ?›

መሐመድ፡- ‹የእነሱ የተፈጥሮ እውቀት ማጣት ሊታይ የሚችለው የእነሱ ምስክርነት እንደ ግማሽ ወንድ ምስክርነት ብቻ ተቀባይነት ያለው ከመሆኑ እውነታ አንፃር ነው›፡፡

ጠያቂ፡- ‹እንደገና የእነሱ ምስክርነት ግማሽ የሆነው ለምንድነው?›

መሐመድ፡- ‹ምክንያቱም አዕምሯቸው ጎደሎ ስለሆነ ነው›፡፡

ጠያቂ፡- ‹ምናልባትም የጎደለው ነገር ቢኖር የአንተ የክርክር መንገድ ነው›፡፡ የመሐመድ አነጋገር እዚህም ላይ ውሸት ሊሆን የሚችል መሆኑን አስተውሉ፡፡ ያም በፅንሰ ሐሳብነታቸው ሊፈተኑና (ሊመረመሩና) ትክክል አለመሆናቸው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ እኛ መሐመድ ስለሴቶች እውቀት የተናገረው አረፍተ ነገር ትክክል መሆን አለመሆኑን በቀላሉ ሙከራ ሰርተን ማየት እንችላለን፡፡ እንዲሁም አንድ የወንዶች ቡድንና የሴቶች ቡድን በአንድ ዓይነት የአደጋ ክስተት ላይ የሚሰጡትን ምስክርነት ላይ ሙከራ ማድረግንም እንችላለን፡፡ ከወንዶቹ ቡድን ላይ የተወሰደው ምስክርነት ከሴቶቹ ቡድን ከተወሰደው ላይ እጥፍ ከሆነ የመሐመድ አረፍተ ነገር ተረጋግጧል ማለት ነው፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ ከሁለቱም ቡድን የመጣው ዘገባ አንድ ዓይነት ከሆነ የመሐመድን ሐሳብ፣ በባህላዊ ሁኔታዎች መምታታት የተበከለ የአመንዝራ ሰው አስተያየቶች ናቸው በማለት መጣል እንችላለን፡፡

እውነታ 3፡- መሐመድ ከዚህ ሕይወት በኋላ ስላለው ሕይወት ለሴቶች የሰጠው ነገር በጣም ጥቂት የሆነ ተስፋን ነው፡፡ በእርግጥ እርሱ በትክክል ያስቀመጠው ዓረፍተ ነገር በሲዖል ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ለባሎቻቸው ክብርን ያልሰጡ ሴቶች ናቸው በማለት ግልጥ አድርጎታል፡፡ (ምንም እንኳን ለሴቶቻቸው ክብርን የማይሰጡ ባሎች ተመሳሳይ ቅጣት ይቀበላሉ በማለት በጭራሽ ባይጠቅስም)፡፡ ይህ ደግሞ አንድ ጠቃሚ ጥያቄን ያስነሳል፡ የሙስሊም ባሎች ለሚስቶቻቸው ምስጋና ቢስ ከነበሩት በበለጠ የሙስሊም ሴቶች ለባሎቻቸው ምስጋና ቢሶች ነበሩን? ይህ ደግሞ የሚመስል አይመስልም፡፡

በሙስሊም የኣቃቤ እምነታውያን መሰረት የሴቶች መብት ጉዳይ በአረቢያ ከእስልምና በፊት በጭራሽ እንዳልነበረ ነው፡፡ ሙስሊም ወንዶች ለሚስቶቻቸው ትልቅ ክብር ነበራቸውን? ምናልባትም አይደለም፡፡ በጣም የሚመስለው አመለካከት፤ ‹በሚገባ ስለያዝናችሁ እናንተ ሴቶች ብታመሰግኑን መልካም ነው› የሚመስል ነበር፡፡ ከላይ እንዳየንው ሁሉ ይህን ዓይነቱ አመለካከት ነበር በትክክል በመሐመድ ውስጥ የነበረው፣ እሱም የነገረን ምስጋና ቢስ የሆኑት ሴቶች ምስጋና ቢስነታቸው በሲዖል ውስጥ ቦታ ያስገኝላቸዋል በማለት ነው፡፡ ይህም ደግሞ ሴቶች ከተገሰፁ በኋላ፣የተለየ አልጋ ላይ ይተዋሉ፤ ከዚያም በባሎቻቸውም ይደበደባሉ፡፡ ፈቃደኛ የሆነች ምስጋና ያላት ሴት ግን ወደ ፊት የምታየው ዘላለም በሲዖል ውስጥ መሆንን ነው፡፡

ነቢዩ (የአላህ ሰላምና በረከት በእርሱ ላይ ይሁን) እንዲህ አለ፡ ‹ገነትን አየሁኝና እጄንም ወደ ፍሬዎቿ ዘለላዎች ዘረጋሁኝ እናም ወሰድኩኝ፤ ዓለም እስከሚኖር ድረስ ከእርሱ ልትበሉ ትችላላችሁ፡፡ እንዲሁም ደግሞ የሲዖልን እሳት አየሁኝ እንዲህ ዓይነት የሚያሰቅቅን ነገር በፍፁም አይቼ አላውቅም፡፡ በዚያም ውስጥ ከሚኖሩት ብዙዎቹ ሴቶች እንደነበሩም አየሁኝ፡፡› ሰዎችም ጠየቁት፣ ኦ የአላህ መልእክተኛ ይህ ለምንድነው? ነቢዩ (የአላህ ሰላምና በረከት በእርሱ ላይ ይሁን) እንዲህ አለ፡ ‹በእነሱ ምስጋና ቢስነት ነው›፡፡ ምስጋና ቢስ የሆኑት ለአላህ ነው ወይ ተብሎም ተጠይቆ ነበር፡፡ ነቢዩ (የአላህ ሰላምና በረከት በእርሱ ላይ ይሁን) እንዲህ አለ፡ ‹እነሱ ምስጋና ቢስ የሆኑት ለሕይወት ጓደኞቻቸው ነው (ለባሎቻቸው) እንዲሁም መልካምን ነገር ለማድረግ የሚያመሰግኑ አይደሉም፡፡› Sahih Al-Bukhari, Dr. Muhammad Matraji, tr. (New Delhi: Islamic Book Service, 2002), Number 1052.

መሐመድም አለ፣ ‹ኦ ሴቶች ሆይ! ምፅዋትን ስጡ ምክንያቱም በሲዖል እሳት ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች ሴቶች እንደነበሩ አይቻለሁኝና›፡፡ ሴቶቹም ጠየቁ ‹የአላህ ሐዋርያ ሆይ! ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው?› እርሱም አለ፡ ‹ኦ ሴቶች ሆይ! እናንተ ብዙ ጊዜ ትምላላችሁ እንዲሁም ለባሎቻችሁ ምስጋና ቢሶች ናችሁ፡፡ በሃይማኖትና በእውቀት እንደ እናንተ በጣም ጎደሎ የሆነን ማንንም አላየሁኝም፡፡ ኦ ሴቶች ሆይ ከእናንተ አንዳንዶች ጥንቁቅ ሰውን ወደ ስድነት ትመራላችሁ›፡፡ Sahih Al-Bukhari, Dr. Muhammad Matraji, tr. (New Delhi: Islamic Book Service, 2002), Number 1462.

ይሁን እንጂ፣ እነዚህ ሴቶች መራገምን ቢያቆሙምና ባሎቻቸውንም ማመስገንን ቢጀምሩም እንኳን፣ ከሞት በኋላ ያለውን ሕይወት ማግኘትን አስመልክቶ አሁንም የሚመኙትን ነገር ብዙም አይጨምርም፡፡ እንደ መሐመድ አባባል ሙስሊም ሴቶች መመልከት የሚችሉት ወንዶች መጥተው ከእነሱ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲያደርጉ በገነት ከተማ ጠርዞች ላይ ዘላለም በመቆም መጠባበቅ ነው፡፡ የአላህ ሐዋርያ (የአላህ በረከትና ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) እንደሚከተለው አለ፡ ‹በገነት ውስጥ ስልሳ ማይልስ ስፋት ያለው ሰገነት አለ፤ በእያንዳንዱም ጠርዝ ሚስቶች አሉ እነሱም በሌሎቹ ጠርዞች ያሉትን ሚስቶች ማየት አይችሉም፣ ገብኝዎችም እነሱን ይጎበኟቸዋል በእነሱም ይደሰታሉ፡፡› Sahih Al-Bukhari, Dr. Muhammad Matraji, tr. (New Delhi: Islamic Book Service, 2002), Number 4879.

ስለሆነም ጥሩ የሆኑት ሙስሊም ሴቶች ማለትም በዚህ ሕይወት ውስጥ ባሎቻቸውን የሚያከብሩት በገነት ውስጥ የግበረ ስጋ ግንኙነት አገልግሎትን ለባሎቻቸው በመስጠት የማገልገል ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ገነትን በተመለከተ ይህ ትክክለኛ የሆነ አመለካከት መሆኑን መሐመድ አስተውሎታል፣ ብዙ ሴቶች ግን በትክክል በዚህ አይስማሙም፡፡

እውነታ 4፡- ቁርአን ሙስሊሞች በጦርነት ከማረኳቸው ባሪያ ሴቶች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲያደርጉ ይፈቅድላቸዋል (ይህም ‹ቀኝ እጆቻቸውን የያዟቸውን ነው›)፡፡ የሙስሊም ተዋጊዎች ብዙ ከተማዎችን እየወረሩ እያሉ እንደ ባሪያ የሚሸጡና የሚነገዱ ብዙ ሴቶችን ይዘዋል፡፡ ሆኖም ሙስሊም ወንዶች ከሚስቶቻቸው በጣም ርቀው ስላሉ የማረኳቸውን ሴቶች እንዴት ሊይዟቸው እንደሚችሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሪትን ፈለጉ፡፡ አማኞቹ በስተመጨረሻ ማሸነፍ አለባቸው - እነዚያም በፀሎት እራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉቱ ተራ ንግግርን የሚያስወግዱቱ እንዲሁም በመልካም ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉቱ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነት የተቆጠቡቱ፣ በጋብቻ ከተጣመሩት ሴቶች ውጪ የማይገናኙቱ፣ ወይንም (ከምርኮኞቻቸው) በቀኝ እጆቻቸው ከያዟቸው በስተቀር (በእነሱ በኩል) ከነቀፋ ነፃ ናቸው፡፡ Qur’an 23:1-6, Abdullah Yusuf Ali Translation. ‹ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑተወ፡፡ ለለማኝ ከልመና ለሚከለክልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ እነዚያም እነሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የሚያስተማምን ነውና፡፡ እነዚያም እነርሱም ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሮች) ላይ ሲቀር እነሱ (በነዚህ)፣ የማይወቀሱ ናቸውና› የአማርኛው ቁርአን 70.22-30፡፡

ከምርኮኛ ሴቶች ጋር የሚደረገው የሙስሊሞች ግብረ ስጋ ግንኙነት ልምምድ በሐዲት ውስጥ ብዙ ጊዜ ተዘግቦ ይገኛል፣ ይህም ሙስሊሞች የማረኳቸውን ሴቶች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው በተጨነቁበት ሁሉ ላይ ነው፡፡ አላህም ለእነዚህ ግራ ለተጋቡት ሙስሊም ተዋጊዎች ከሴቶቹ ጋር እንዲተኙ መገለጥን ከላከ ብዙ አልቆየም ነበር፡ የአላህ መእክተኛ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ወደ ኡታስ ሰራዊትን ላከ እና ጠላትን ገጠመ እና ከእነርሱም ጋር ተዋጋቸው፡፡ እነሱንም በማሸነፍና ምርኮኞች በማድረግ የአላህ መልእክተኛ ጓደኞች (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን)፣ ከማረኳቸው ሴቶች ጋር ግንኙነትን ከማድረግ ተቆጠቡ ምክንያቱም ባሎቻቸው ብዙ ጣዖታትን አምላኪዎች ነበሩና፡፡ ከዚያም አላህ ከፍተኛው ይህንን በተመለከተ መልክትን ላከ፡ ‹ከሴቶችም (በባል) ጥብቆቹ እጆቻችሁ (በምርኮ) የያዙዋቸው ሲቀሩ በእናንተ ላይ እርም ናቸው› 4.24፡፡ (ማለትም የ ኢዳ ጊዜ እንዳበቃ ለእነሱ የተፈቀዱ ነበሩ› Sahih Muslim, Number 3432.፡፡

ወደ ቢኢል-ሙስታሊክ ዘመቻም ከአላህ መልእከተኛ ጋር ወደ ውጪ ወጣን አንዳንድ በጣም ግሩም የአረብ ሴቶችንም ምርኮኞች አድርገን ማረክን፤  እኛም ተመኘናቸው፣ ምክንያቱም ሚስቶቻችን ከእኛ ጋር ስላልነበሩ በስቃይ ላይ ነበርንና (ነገር ግን በተመሳሳይ ሰዓት) ለእነሱም ካሳን መቀበልን ተመኘን፡፡ ስለዚህም ከእነሱ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን አደረግን ነገር ግን አዚልን በመጠበቅ ነበር (ይህም የወንድ ዘር እንዳይፈስና ፅንስ እንዳይፈጠር ብልቶቻችን በማውጣት ነበር)፡፡ ነገር ግን እኛ አልን፡- እኛ የአላህ መልእክተኛ ከእኛ መካከል ባለበት ሰዓት እንዲህ ያለ ነገርን አደረግን፣ ለምን እሱን አንጠይቀውም? ስለዚህም የአላህን መልእክተኛ ጠየቅነው (ሰላም በእሱ ላይ ይሁንና) እርሱም እንዲህ አለ፡ ባታደርጉት ምንም አይደለም ምክንያቱም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ሊወለድ የነበረው እያንዳንዱ ነፍስ ይወለዳልና፡፡› Sahih Muslim, Number 3371፡፡

ወደ ቡን አል-ሙስታሊክ ዘመቻም ከአላህ ሐዋርያ ጋር አብረን ወጣን (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን)፤ እኛም ምርኮኞችን ከአረብ ምርኮኞች ተቀበልን እናም እኛ ሴቶችን ተመኘናቸው እና ያለግንኙነትም እራሳችንን ማቆየት በጣም ከባድ ሆነብን እናም ዘራችንን በውጭ ማፍሰስንም (ከዚህ በላይ ከተጠቀሰው አዚል ጋር ተመሳሳይ ነው) ወደድን፡፡ ይህንንም ለማድረግ ባቀድን ጊዜ እኛ እንደዚህ አልን፡- ‹ይህንን ዘርን በውጪ ማፍሰስን እንዴት ልናደርግ እንችላለን በመካከላችን ያለውን የአላህን ሐዋርያ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) በመጀመሪያ ለምን አንጠይቀውም? እኛም ስለዚህ ነገር ጠየቅነው እርሱም፡ ‹ይህንን ባታደርጉት ለእናንተ መልካም ነው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ እንዲኖር የተወሰነለት ማንኛውም ነፍስ ይኖራልና አለን› Sahih Al-Bukhari, Number 4138.፡፡

ጃቢር ቢን አብደላህ (አላህ በእነሱ ደስ ይበለው) የዘገቡት አንድ ሰው የአላህን ሐዋርያ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) ጠየቀው እንዲህ በማለት፡- እኔ ሴት ባርያ አለችኝ እኔም ዘሬን በውጪ እያፈሰስኩኝ እለማመዳለሁኝ፡፡ የአላህ ሐዋርያ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) እንዲህ ብሏል፡ አላህ የወሰነውን ነገር ይህ አያግደውም በማለት፡፡ ሰውየውም ከዚያ መጣ (ከጥቂት ጊዜያት በኋላ) ተመልሶ እንዲህ አለ፡ የአላህ መልእክተኛ ስለ እሷ የነገርኩህ ሴት ባሪያ ፀነሰች፣ በዚያም ጊዜ የአላህ መልእክተኛ (ሰላም በእሱ ላይ ይሁን) እንዲህ አለ፡ እኔ የአላህ ባሪያ እና የእሱ መልእክተኛ ነኝ፡፡ Sahih Muslim, Number 3384፡፡

ሙስሊሞች በመጀመሪያ ከምርኮኞቻቸው ጋር ግንኙነትን ለማድረግ አልፈለጉም ነበር ምክንያቱም የጣዖታት አምላኪዎች ሚስቶች ናቸውና፣ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከሴቶች ጋር ግንኙነትን እንዲያደርጉ ነፃ ናቸው የሚልን መልእክት ላከ፡፡ ዘመናዊ ሙስሊሞች የሚያምኑት ይህ የግብረስጋ ግንኙነት የሚደረገው ከጋብቻ በኋላ ብቻ ነው በማለት ነው፣ ይሁን እንጂ ይህ አመለካከት በግልፅ የተሳሳተ ነው፡፡ የመሐመድ ተከታዮች ከሴቶቹ ጋር መገናኘትን ፈለጉ ነገር ግን ደግሞ በሌላ ጎኑ አሁንም ሴቶቹን ለመሸጥ ፈለጉ፡፡ መሐመድንም ዘርን በውጭ ስለማፍሰስ ጠየቁት፣ መሐመድ ግን ይህ ምንም ችግር የለበትም በማለት መለሰ፡፡ ሊወለዱ የታቀዱት ልጆች ሁሉ ይወለዳሉ ስለዚህም ሰው ዘሩን በውጪ አፈሰሰም አላፈሰሰም ምንም ለውጥን አያመጣም፡፡ ስለዚህም ቁርአን ወንዶች ከሴት ምርኮኞቻቸው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲያደርጉ ይፈቅድላቸዋል (ባሎቻቸው አንዳንድ ጊዜ በሕይወትም እያሉ ቢሆንም)፡፡ For more on this, see "Muhammad and the Female Captives" and "Adultery: Do It! Do It! Do It!"፡፡

እንዲሁም ደግሞ ሐዲት ይህ ልምምድ መቼ ይደረግ እንደነበረ ምሳሌን ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን ይህንን እውነታ እስከ ሎጂካዊ መደምደሚያው መከተል ይኖርብናል፡፡ ሙስሊሞቹ በኋላ ከሚሸጧቸው ከሴት ምርኮኞቻቸው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትነት ለማድረግ ወሰኑ፡፡ እነዚህ ምርኮኞች ባሎቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በሙስሊሞች የተገደሉባቸው ነበሩ፡፡ እነዚህ ሴቶች ቤተሰቦቻቸውን ከገደሉባቸው ወንዶች ጋር በደስታ ግብረ ስጋ ግንኙነትን ለማድረግ ይስማማሉን? ምናልባትም አይስማሙም፡፡ ቁርአንና መሐመድ ከምርኮኞች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግን ስለፈቀዱ፣ ሙስሊሞቹ ምርኮኞቹን ሴቶች አስገድደው እንዲደፍሩ መሐመድ የፈቀደ የመሆኑ እውነታ አሳማኝነቱ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

ግምገማ፡-

መሐመድ በሆነ መንገድ የአረብያን ሴቶች ሕይወት አሻሽሏል፡፡ በሌላ መንገድ የሴቶችን መብት የሚለው ከእስልምና ጅማሬ ጋር ወደኋላ የተመለሰ ነው፡፡ ለምሳሌም የመሐመድ የመጀመሪያ ሚስት ከዲጃ በጣም የተሳካላት ሴት ነጋዴ ነበረች፣ እሷም ባሏ እንዲሆን የመረጠችውን ማንንም ባሏ ማድረግ ችላ ነበር፡፡ ስለዚህም ሴቶች በማህበረ ሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ቦታን ሊይዙ ችለው እንደነበር እና ከእስልምና መነሳት በፊትም ትልቅ ስልጣን ለማያዝ ይችሉ እንደነበር ነው፡፡ ይሁን እንጂ በእስልምና ሕግ ስር ሴቶች ብዙ ነገርን ማድረግ አይችሉም ቤታቸውንም ትተው ለመውጣት የባሎቻቸው ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል (ይህንንም ማድረግ የሚችሉት ተገቢውን ልብስ በመልበስ ነው)፡፡

ይሁን እንጂ ሙስሊሞች ብዙውን ጊዜ ይህንን እውነታ መሐመድ ነቢይ የመሆኑ ማስረጃ ነው በማለት ይወስዱታል (ይጠቅሱታል)፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ክርክር ዋጋ ቢስ ነው፡፡ በሴቶች ሕይወት ውስጥ ያለው መሻሻል የሚያመለክተው ነገር እስልምና ከእርሱ በፊት እንደነበረው ባህል መጥፎ አለመሆኑን ብቻ ነው፣ ያም በብዛት የሚናገረው ስለ ፓጋኖቹ እንጂ ስለ ሙስሊሞቹ አይደለም፡፡ እኛ እንዳየነው መሐመድ በሚስቶች ላይ የሚደረግን የወንዶች ብልግና ፈቅዷል፣ እንዲሁም በመደጋገም ሴቶች ከወንዶች አዕምሯቸው ደካማ መሆኑን ተናግሯል፣ በሲዖልም ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ሴቶች ናቸው ብሏል፣ እንዲሁም ወንዶቹን ከሴቶች ምርኮኞች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲያደርጉ ፈቅዶላቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ምናልባትም ከእስልምና መነሳት በፊት ከነበሩት ሴቶች የተሻለ ሊሆን ይችላል፣ ይሁን እንጂ መሐመድ ‹ዓለም ካየችው የሴቶች መብት አስጠባቂ ሁሉ በጣም ታላቁ ነው› በመባል እንዲቆጠር አያስችለውም፡፡ በምዕራብ የሴቶች ሁኔታ (መብት) ባለፉት ጥቂት ምዕተ ዓመታት በጣም ተሻሽሏል፡፡ በአንዳንድ የሙስሊም ዓለም አካባቢ ውስጥ ለውጦችን እና ተመሳሳይ ፖሊሲዎችን መውሰድ ጥረት ሲደረግ እያየን ነው ይህም መሐመድ በሴቶች ላይ ካለው ዝቅተኛ አመለካከት በተቃራኒው በመሆኑ እኛ ሁላችንም በምስጋና እንሞላለን፡፡ ነገር ግን ብዙ አካባቢዎች የመሐመድን መርሆ የመከተል ዝንባሌ ነው ያላቸው፣ እናም አሁንም በጨለማ ውስጥ ናቸው፡፡ እነዚያም ቁርአንን ለመከተል የሚፈልጉቱ አንድ ቀን መጽሐፍ ቅዱስን አንስተው የጳውሎስን ቃሎች ያነባሉ ብለን እንናፍቃለን፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የሚከተሉት ጥቅሶች አስደናቂዎች ናቸው፡-

‹ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።› ቆላስያስ 3.19፡፡

‹ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤› ኤፌሶን 5.25-26፡፡

‹በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና። እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።› ገላትያ 3.26-29፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

በመደምደሚያ ላይ የቀረቡት ሦስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ሴቶችን በተመለከተ አስደናቂ እውነታዎችን ያቀርባሉ፡፡ አማኝ ሴቶች ከአማኝ ወንዶች እንክብካቤ እንዲደረግላቸው፤ እንዲወደዱ፣ እንዲከበሩ ከመናገራቸውም በላይ በእግዚአብሔር ፊት ወንዶችም ሴቶችም እኩል እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶችንም ወንዶችንም በኃጢአታቸው እኩል ይወነጅላቸውና፣ ሁለቱም ዘላለማዊዋን ገነት መውረስ የሚችሉት በአንድ መንገድ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ይህም መንገድ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነው በክርስቶስ እየሱስ በጌታችንና በአምላካችን ማመን ብቻ ነው፡፡ አዎ ሴቶችም ወንዶችም ያለምንም የፆታ ልዩነት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት ይችላሉ ይህም የሚሆነው ኃጢአታቸውን ተናዘው በአዳኙ በጌታ በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ከመጡ ነው፡፡

አንባቢ ሆይ እግዚአብሔር ለሰዎች ሁሉ ያለምንም የፆታና የመደብ ልዩነት ያቀረበውን የንስሐ ጥሪ ሰምተሃልን? ይህንን የእሱን ጥሪ ለሰሙና እግዚአብሔርን በመታዘዝ ኃጢአታቸውን ተናዘው በአዳኙ በጌታ በኢየሱስ ለሚያምኑት ስለገባው የቃልኪዳን ስጦታስ ሰምተሃልን? ስጦታው የዘላለም ምህረትና መንግስተ ሰማይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ስጦታ የዘላለም ሕይወት በማለት ይጠራዋል፡፡ ስለዚህም የዚህ ገፅ አዘጋጆች ይህንን የእግዚአብሔርን ጥሪ እያቀረቡልህ እንድትታዘዘው በእርሱ ፍቅር ይጠይቁሃል፡፡ ጌታም በፀጋውና በምህረቱ ይርዳህ፣ አሜን፡፡

 

የትርጉም ምንጭ:The Majority in Hell are Women

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ