ጋብቻና ፍቺ በቁርአን

M.J Fisher, M.Div.

ቅንብር በአዘጋጁ

መግቢያና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ንፅፅር

በእስልምና እምነት ጋብቻ ፅኑ የሆነ አንድነት አይደለም፡፡ የጋብቻ ፍቺን አማራጮች ሁሉ (ካልተሳኩ) ካለቁ በኋላ የሚወሰድ አሰቃቂ እርምጃ እንደሆነ አድርጎ ቁርአን አይመለከተውም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረውና ቁርአን በሚያስተምረው መካከል አስደናቂ ልዩነቶች አሉ ይህም ግልፅ የሚሆነው ከሚከተሉት ሃያ አምስት የቁርአን ጥቅሶች ማስረጃነት ነው፡፡

Not Without My Daughter, በተባለውና Betty Mahmoody (St. Martin’s Press, 1987) በተጻፈው መጽሐፍ ውስጥ ይህንን እውነታ የሚያስረዳ አንድ እውነተኛ ታሪክ አለ፣ እንደዚሁም በዚያው ርዕስ በተሰራው እና ሳሊ ፊልድ ዋና ተዋናይ በሆነበት ፊልም ውስጥ አለ፡፡ እሱም የሚያሳየው ክርስትያን ሴቶች ሙስሊም ወንዶችን አግብተው የሚያጋጥማቸውን ውድቀት ነው፡፡ ወይዘሮ ማህሙዲ እስካመለጠችበት ቀን ድረስ በባሏ ዘመዶች ምርኮኛ ሆና በኢራን ውስጥ ተይዛለች፣ ነገር ግን ሴት ልጇን ሳትይዝ መልቀቅ አልነበረባትም፡፡ ርህራሄ ያላቸው ሙስሊሞች እንድታመልጥ እረድተዋታል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የተያዙ ሴቶችን በመርዳት ስራ ላይ ተሰማርታለች፡፡ በአሜሪካን ከሰባ አምስት በላይ የሆኑ ልጆች  ከእናቶቻቸው ጋር እንደገና እንዲገናኙ ረድታለች (Ladies Home Journal, November 1998, p.44).

እስልምና ስለ ጋብቻና ፍቺ የሚያስተምረው ትምህርት በሙስሊሞችም መካከል ከፍተኛ ጥያቄን አስነስቷል፡፡ ያለምንም ምክንያት የተፈታች አንዲት ሙስሊም ሴት፣ የዚህን እውነታ መልስ የመገንዘብ ምርመራ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታነብ መርቷታል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያውጀውን የጋብቻን ቅድስና ስትረዳ ክርስትናን እንደ እምነቷ ተቀብላለች፡፡ የእሷም ስም Bilquis Sheikh ሲሆን I Dared to Call Him Father (Chosen Books of The Zondervan Publishing House, Grand Rapids, Michigan, 1978) የሚለውንና በጣም ታወቂውን መጽሐፍ የጻፈችው ሴት ናት፡፡ ልዩነቱ ምንድነው? መጽሐፍ ቅዱስም ቁርአንም ስለ ዝሙት ኃጢአት ይናገራሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ግን እጅግ በጣም የተለየ ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ገና በመጀመሪያው መጽሐፍ ውስጥ፣ ሰው የተተረጎመው ወንድና ሴት ሆኖ እንደተፈጠረና በእግዚአብሔርም መልክ እንደተሰራ ነው ዘፍጥረት 1.27፡፡ በጋብቻ ውስጥ ሁለቱ ‹አንድ ስጋ› ይሆናሉ ዘፍጥረት 2.24፡፡ ጌታ ኢየሱስ ይህንን ክፍል በመጥቀስ የጋብቻን ቅዱስነት አፅንዖት ሰጥቶ ተናግሮበታል እናም ጋብቻ ሊፈርስ የሚችለው ዝሙትን በመፈፀም ታማኝነት ሲጎድል ብቻ ነው ማቴዎስ 19.3-12፡፡ ብዙ ክርስትያኖች እንደሚያምኑት ‹አለመታመን› የሚለው ቃል ጋብቻን መተውንና በደለኝነትን ያጠቃልላል፡፡ የክርስትና ጋብቻ እጅግ በጣም ቅዱስና ክቡርም ነው፣ በአዲስ ኪዳንም ውስጥ ተጠቅሶ የተመሰለው እግዚአብሔር ለሙሽራው ማለትም ለቤተክርስትያን ያለውን ፍቅር ለማሳየት ነው፡፡ ይህም ምሳሌ ዓለም አቀፏንና እውነተኛ አማኞችን የያዘችውን ቤተክርስትያንን የሚወክል ነው ኤፌሶን 5.31፣32፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለጋብቻ ካለው መመሪያ በተቃረነ መልኩ በምዕራብ አገሮች ውስጥ የፍቺ ቁጥር በመቶ ሲሰላ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ አንዳንድ ሙስሊሞች የዚህን እውነታ ለትችት ሊጠቀሙበት ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ አንፃር ትክክል ናቸው፡፡ አዎን በዚህ በኩል በምዕራቡና ክርስትያን ነው ተብሎ በሚጠቀሰው ክፍል ውስጥ በትክክል ችግር አለ፡፡ (ይሁን እንጂ በምዕራብ የሚኖረውና የጋብቻ ሕይወቱ ምስቅልቅሉ የወጣው የክርስትናን እምነት ይወክላል ማለት አይቻልም፣ ክርስትና ስለጋብቻ ያለውን አመለካከት መመልከት ያለብን ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብቻ ነውና)፡፡ ሆኖም በኃጢአት ውድቀት ምክንያት እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔር ክብር የጎደለው የመሆኑን እውነታ ከሚያስረዱት ዋና ዋና እውነቶች መካከል ይህ አንዱ እንደሆነ ክርስትያኖች ያምናሉ፡፡ ስለዚህም የአዳኙ የጌታ ኢየሱስ ፀጋና ምህረት እንዲሁም መፅናናት ለሰው ሁሉ ያስፈልገዋል ሮሜ 3.22-24፡፡

ቁርአን የሚከተለውን ይናገራል፡- 

የሚስቶችና የወንድ ልጆች በረከት፡- አማኞች የሆኑት ሙስሊሞች፣ ሚስቶች፣ ወንድ ልጆችና የወንድ የልጅ ልጆች ተሰጥተዋል በማለት ቁርአን ይናገራል፡፡ እነሱም መልካም ነገርን ተሰጥተዋል፡፡ የማያምኑት ከእንደዚህ ዓይነት በረከት መራቃቸው ያስደንቃል 16.72፡፡

የብዙ ጋብቻ (ፖሊጋሚ)፡- ሙስሊሞች ሁሉ እስከ አራት ሚስት ድረስ እንዲያገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አንድ ሰው ብዙ ሚስቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር የሚፈራ ከሆነ አንድ ሴት ብቻ ማግባት ይኖርበታል 4.3፡፡ አንድ ወንድ ሁሉንም እኩል ለማስተዳደር በጣም በተቻለው መጠን ቢሞክርም እንኳን የማይቻል ነው፡፡ ነገር ግን ከሚስቶቹ አንዲቷም እንዳትተው እንዲሁም እርግጠኛ ባልሆነ ጉጉት ውስጥ እንዳትተው እርግጠኛ መሆን አስፈላጊ ነው፡፡ ‹በሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ (በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡ እንደ ተንጠለጠለችም አድርጋችሁ ትተዋት ዘንድ (ወደምትወዷት) መዝዘንበልን ሁሉ አትዝዘንብሉ ብታበጁም ብትጠነቀቁም አላህ መሐሪ አዛኝ ነው፡፡› 4.129፡፡

ቅምጦች:- ሙስሊሞች ከሚስቶቻቸው እና በጦርነት ከማረኳቸው ከሴት ባሪያዎቻቸው ውጪ የግብረ ስጋ ግንኙነትን የማያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ግንኙነት ምንም ወንጀል የለበትም 23.5፣6፡፡ ባሪያዎች ለአሳዳሪዎቻቸው አላህ ከሰጠው ሃብት እኩል መካፈል የለባቸውም (አይካፈሉም)፡፡ የባሪያዎች ጌቶች እኩያዎቻቸውን ሙስሊሞችን እንደሚፈሩ ባሪያዎቻቸውን መፍራት የለባቸውም 30.28፡፡

የአደገች ሴት ልጅ ጋብቻ፡- ሙስሊሞች የወር አበባ ያላየች ሙሽራ ልጃቸውን ለማፋታት በሚፈለጉበት ጊዜ ፍቺውን ከማካሄዳቸው በፊት ሦስት ወራት መጠበቅ ይኖርባቸዋል ይህም ልጅቷ እርጉዝ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ልጅቷ እርጉዝ ሆና ከሆነ ግን ባለቤቷ እስከምትወልድ ድረስ ፍቺውን ማዘግየት አለበት 65.4፡፡

የእጀራ ሴት ልጆች፡- አንድ ሙስሊም አስቀድሞ ሴት ልጅ ያላትን ሴት ቢያገባ፣ ሴት ልጆቿንም ማግባት ይችል ይሆናል፣ ይህም ከእናታቸው ጋር ምንም ግብረ ስጋ ግንኙነትን ካላደረገ ነው 4.23፡፡

ያገቡ ሴቶች፡- ያገቡ ሴቶችን ማግባት ለሙስሊሞች የተከለከለ ነው፣ ይህም በጦርነት በኃይል ካገኟቸው ሴት ባርያዎች ውጭ ነው 4.24፡፡

ፍቺ፡- አንድ የሙስሊም ባል አሁን ያለችውን ሚስቱን ለሌላ ሴት ለመለወጥ ቢፈልግ ለእሷ የሰጣትን የጋብቻ ስጦታ መልሶ መውሰድ የለበትም ሃብትም እንኳን ቢሆን 4.20፡፡ እሱም ሚስቱን የፈታው ‹አንቺ እናቴ ነሽ› በማለት በፓጋናዊው ዓረፍተ ነገር ከሆነ እሱ ፍቺውን የፈፀመው በተሳሳተ መንገድ ነው፡፡ እሷ የአንተ እናት ልትሆን አትችልም፡፡ እሷንም እንደገና መልሰህ ለማግባት ከፈለግህ አንድ ባሪያን ነፃ ማድረግ፣ ወይንም ለሁለት ወራቶች መፆም ወይንም ስድሳ ድሃዎችን መመገብ ይኖርብሃል 58.1-4፡፡

ያላመኑ ሚስቶች፡- ሙስሊም ካላመነች ሚስት ጋር ተጋብቶ መቆየት የለበትም፡፡ በእሷ ላይ የወጣውን ወጪ መልሶ ማግኘት አለበት እሷም በእሱ ላይ ያወጣችውን ወጪ መልሳ ማግኘት አለባት 60.10፡፡

የተወረሰች ሴት፡- ሙስሊሞች አንድን ሴት ከፈቃዷ ውጪ ላይወርሷት ይችላሉ፡፡ የተወረሰች ሴት ገንዘብን በተመለከተ ያላግባብ (እኩል ባልሆነ መንገድ) ልትጎዳ አይገባም የዝሙትን ኃጢአት ካልፈፀመች በስተቀር 4.19፡፡

ድጋሚ ጋብቻ፡- አንድ ሙስሊም ባል ሚስቱን በማይሻር ሁኔታ ቢፈታ (ሦስት ጊዜ ፈትቼሻለሁ በማለት) ቢፈታ መልሶ ሊያገባት አይችልም ይህም ሌላ ወንድ አግብቶ እስካልፈታት ድረስ ነው፡፡ ሌላ ሰው አግብቶ ከፈታት በኋላ የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት እንደገና ቢጋቡ በደለኞች አይሆኑም 2.230፡፡

የሴቶች መብት፡- ፍቺን በተመለከተ ሴቶች ተመሳሳይ የሆነ ነገር ግን ዝቅተኛ መብት ነው ያላቸው፣ ይህም ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ከፍተኛ ደረጃ ስላላቸው ነው 2.228፡፡ አንዲት ሴት ባሏ ጨካኝ መሆኑ ከተሰማት ወይንም እንደተዋት ሁለቱ ያላቸውን ነገር አብረው ማየትና ማስተካከል አለባቸው ከዚያም ወደ አንድ የጋራ የሆነ ነጥብ ላይ መድረስ አለባቸው 4.128፡፡

ሽርሙጥና፡- እነዚያ ባሪያዎች የሆኑት ሴቶች እና ንፁህነትን የሚፈልጉቱ ምድራዊ ሃብትን ለማግኘት ሲባል ወደ ሴትኛ አዳሪነት መገፋፋት የለባቸውም፡፡ ነገር ግን አሳዳሪዎቻቸው የሚያስገድዷቸው ከሆነ አላህ ይቅር ባይ ነው 24.33፡፡

የመበለቶች ውርስ፡- ሊሞት ያለ ባል ለሚስቶቹ በቂ የሆነን ነገር ሊተውላቸው ይገባል ስለዚህም ለአንድ ዓመት ያህል ቤታቸውን ለቅቀው መውጣት አይኖርባቸውም ይህም እነሱ እራሳቸው ለማድረግ ካልፈለጉ በስተቀር ነው፡፡ ለተፈታችም ሴት እንደዚሁ አንዳንድ የስጦታ ነገሮች ሊደረጉላት ያስፈልጋል፡፡ 2.240፣241፡፡

የሚታረስ ሜዳ፡- ሴቶች ለወንዶች የእርሻ ቦታዎች ናቸው ይህም መቼም እና እንዴትም አድርገው ሊያደርጉ ቢፈልጉ ነው 2.223፡፡

ሚስቶችን መደብደብ፡- ወንዶች በሴቶች ላይ ሃላፊነት አለባቸው ምክንያቱም ወንዶች ከሴቶች ይልቅ የበለጡ ሆነው ስለተፈጠሩና እነሱንም ስለሚደግፏቸው ነው፡፡ ጥሩ ሴቶች ታዛዦች ናቸው፡፡ አለመታዘዝ ከታየ ወይንም ከተጠረጠረ ግን አመፀኛዋ ሴት መሰደብ አለባት ብቻዋን እንድትተኛ መደረግ አለባት፣ ይህም እስከምትሻሻል ወይንም እስከምትለወጥ ድረስ ነው 4.34፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

ከላይ የተመለከትነውና በሃያ አምስት ጥቅሶች ዙርያ ያለው የቁርአን ትምህርት አስገራሚ ነው፡፡ በጋብቻና ፍቺ እንዲሁም በሕይወት ዙርያ ላይ ቁርአን የሚሰጠው ትምህርት እንዲሁም የሚያበረታታው ልምምድ ከተፈጥሮ ስርዓት ከሕይወት እውነታ ጋር አብሮ የሚሄድ ነውን? ሁሉን ከሚያውቅና ከሚችል አምላክስ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚጠበቅ ነውን? የሚሉትን ጥያቄዎች ልንጠይቅና መልሳቸውንም ልንፈልግ ይገባናል፡፡

በዚህ ምድር ያለንን ሕይወትን ልንመለከት የሚገባን በእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል መርሆ ላይ በመመስረት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለጋብቻም ሆነ ስለ ሕይወት የሚናገረው ነገር ከቁርአን በጣም የተለየ ነው፣ ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የመጣ መጽሐፍ ነውና፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶች በቤተሰብም ሆነ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባው ስፍራ ዝቅተኛ አመለካከትን ሲሰጥ አንመለከተውም፡፡

ሴቶችም ወንዶችም እኩል ኃጢአተኞች በመሆናቸው የእግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል፡፡ ሁለቱም ያለምንም ልዩነት ከእግዚአብሔር መንግስት የራቁ ናቸው፡፡ ለሁለቱም የእግዚአብሔር ምህረትና ይቅርታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በእግዚአብሔር እውነተኛ ምህረትን ያገኙና ይህንንም ያረጋገጡት ወደ ጋብቻ ሲመጡ በመከባበርና በመፈቃቀር በቃሉ መሰረት ጌታን አብረው እያገለገሉ ይኖራሉ፡፡

በእግዚአብሔርና በቅዱስ ቃሉ የሚያምኑ ክርስትያኖች ይህንን እውነት ያከብሩታል በዚህም እውነት መሰረት እግዚአብሔርን እየታዘዙ ይኖራሉ፡፡ እውነተኛ ክርስትያኖች ሚስቶቻቸውን የሚያዩአቸው፣ መንግስተ ሰማይን አብረው እንደሚወርሱ እና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጡ ክቡር ስጦዎች እንደሆኑ ነው፡፡

በቁርአን ውስጥ ባሉት ሃያ አምስት ጥቅሶች ላይ የተገለጠውን የጋብቻንና የፍቺን ነገር የተመለከታችሁ አንባቢዎችን ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታነቡ ስለ ጋብቻና ፍቺ ብቻ ሳይሆን ለግል ሕይወታችሁም የሚያስተላልፈውን መልእክት እንድታስተውሉ ጭምር እንጋብዛችኋለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክም መንፈሳዊ መረዳትን እንዲሰጣችሁ የዘወትር ፀሎታችን ነው፣ አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ:  Marriage and Divorce, Chapter 5 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ