ክርስትናና እስልምና

M. J. Fisher, M.Div.

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ማነፃፀር ወሳኝ ነው፡፡

ቁርአንን በተመለከተ የሚደረግ ማንኛውም ጥናት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ንፅፅርን መጨመር አለበት ምክንያቱም ሙስሊሞች የሚያምኑት እስልምና የተገነባው በአይሁድና በክርስትያኖች ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ነው በማለት ነውና፡፡ መሐመድ ያስታወሰውም ቁርአን፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚስማማና የመጽሐፍ ቅዱስንም ሐሳብ እንደሚያሟላ ይናገራል፡፡ ሙስሊሞች የሚያምኑት አላህ ሕግን ለሙሴ፣ መዝሙርን ደግሞ ለዳዊት፣ እና መልእክቶችን ለብዙ ሌሎች ነቢያት፣ ወንጌልን ደግሞ ለኢየሱስ በመጨረሻም ቁርአንን ለመሐመድ እንደገለጠ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በአረቢያን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ በሚገባ የተመሠረተ ነበረና ስለዚህም አይሁዶች እና ክርስትያኖች ይጠሩ የነበረው የመጽሐፉ ሰዎች ተብለው ነበር (ያም የግሪኩ ‹ባይብል› የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉም ነበር)፡፡

ከዚህም ምክንያት የተነሳ የተለመዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ዋና ሐሳቦች በቁርአን ውስጥ በብዛት ይገኛሉ፡፡ እነዚህም በአንድ አምላክ ማመን፣ ፍጥረት፣ ነቢያት፣ ኃጢአት፣ ፅድቅ፣ ሰይጣን፣ የፍርድ ቀን፣ መንግስተ ሰማይና ሲዖል በቁርአን ውስጥ ሁሉ ይገኛሉ፡፡ በቁርአን ውስጥ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ገፀ ባህርያት ተጠቅሰዋል ለምሳሌም ያህል ኖህ፣ አብርሃም፣ ሙሴ፣ ሰሎሞን፣ እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይገኙባቸዋል፡፡

ቁርአን የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍን የፈለገበት ምክንያት ግልፅ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአደረጃጀቱ እጅግ በጣም ብዙ ታማኝነት ያለው ነው፡፡ ቁርአን ግን የተዘጋጀው በአንድ ነቢይ የሕይወት ዘመን ላይ ነው፡፡ ቁርአን የግጥሙ ውበት ቅዱስ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው በማለት ይናገራል ነገር ግን የወደፊት ሁኔታዎችን ክስተት በተመለከተ ምንም ትንቢቶችን አይሰጥም፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በ1400 ዓመታት ጊዜ በግምት አርባ በሚሆኑ የተለያዩ ነቢያት እና ሐዋርያት አማካኝነት በእግዚአብሔር መገለጥ የተጻፉ የስድሳ ስድስት መጻሕፍት ቤተ መጽሐፍት ነው፡፡ ይሁን እንደጂ መጽሐፍ ቅዱስ ሲነበብ የሚሰጠው አንድ ወጥ የሆነን ታሪክ ነው፡፡ በውስጡም ተካትቶ የሚገኘው ነገር፣ በመጀመሪያው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ፍጥረት እና በመጨረሻው መጽሐፍ ውስጥ ደግሞ ስለ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ወጥ የሆነን ትምህርት ይዟል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በብዙ መቶ ዓመታት ውስጥ በመፈፀም ትክክለኛነቱን አረጋግጠዋል፡፡ በውስጡ የተነገሩ ትንቢቶች ተፈፅመዋል አሁንም እንኳን ያለምንም መዛነፍ እየተፈፀሙ ነው ያሉት፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝነት

ቁርአን ተቀባይነት እንዲያገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ አስፈልጎታል፣ ነገር ግን ሁለቱ መጽሐፎች  እርሰ እርስ በእርስ ይቃረናሉ፡፡ ቅራኔውም በዋና ዋና ነገሮች ላይ ነው፡፡ ለምሳሌም ያህል እንደ ክርስቶስ አምላክነት ላይ ቅራኔ አላቸው፡፡ ሙስሊሞች የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ‹ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው› አይልም ይላሉ፡፡ ክርስትያኖችና አይሁዶች እነዚህን ትምህርቶች ለመጨመር መጽሐፍ ቅዱስን በዘመናት ለውጠውታል በማለት ይናገራሉ፡፡ ክርስትያኖች ግን የሚያምኑት እንደዚህ ዓይነት ውንጀላዎች በታመነ ማስረጃ ላይ ያልተመሰረቱ መሆናቸውን ነው፡፡ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚደረግ ማንኛውም እውነተኛና ጥልቅ ጥናት የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ መሆናቸውን በትክክል እንደሚያረጋግጥ ክርስትያኖች ያምናሉ፡፡

የጥንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ማስረጃ መጠን እጅግ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ ከ20,000 በላይ የሚሆኑ የአዲስ ኪዳን ጥንታዊ የእጅ ጽሑፍ ኮፒዎች በተለያየ ቋንቋዎች ይገኛሉ ከእነዚህም ውስጥ በጣም ጥንታዊ የሆነው ኮፒ ከመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ኮፒ ከሃያ አምስት ዓመት ብቻ በኋላ ብቻ የተደረገ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጌታ ኢየሱስ ሐዋርያት ሰልጥነው ከነበሩ ሰዎች የተጻፉ ጥንታዊ ደብዳቤዎችም አሉ (የቤተ ክርስትያን አባቶች ከሚባሉት የተጻፉ) የእነሱም ጽሑፎች ከ30,000 በላይ የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን የያዙ ናቸው፡፡ ሁሉም ልዩ ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ከቤተክርስትያን አባቶች ከተጠቀሱት ዶክመንቶች ጋር ይስማማሉ፡፡ ተዓምራት የሆነው ነገር በዶክመንቶቹ መካከል ያሉት ልዩነቶች እጅግ በጣም ጥቂቶችና ምንም ጠቀሜታ የሌላቸው መሆናቸው ነው፡፡ የእነዚህ የፊደላት ማለትም የስፔሊንግ ወይንም የተወሰኑ ሐረጎች ወይንም ታሪኮች ልዩነቶች መኖር ውስጥ ልንገነዘበው የሚገባ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰነድ ወይንም ጽሑፍ በእጅ ሲቀዳ ወይንም ተጨማሪ ቅጂዎችን ሌሎች ለማባዛት እንዲጽፉት ሲደረግ እንደዚህ ዓይነት ነገር መገኘቱ የታወቀ ነገር ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ልዩነቶች ወይንም የተለያዩ ቅጅዎች ድብቅ እንዲሆኑ አልተደረጉም ወይንም አልተደበቁም፣ ነገር ግን በእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግርጌ ማጣቀሻ እንዲቀመጡ ተደርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ቅራኔን የሚያመጣ ልዩነት እስከአሁን ድረስ አልተገኘም እንዲሁም የተለየ ንባብ ስላለው የተቃጠለ መጽሐፍ ቅዱስ የለም፡፡ የቁርአንን አመጣጥ እድገት በተመለከተ ግን እውነታው እንደዚህ አይደለም፡፡ በእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካካል ያለው አስደናቂ ስምምነት የክርስትያን ጸሐፊዎች ምን ያህል ስራቸውን የምር አድርገው ወስደውት እንደነበረ የሚጠቁም አስደናቂ ምስክርነት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ምዕራፍ ውስጥ ያለውን ማስጠንቀቂያ ማለትም ሆነ ብሎ በቃሉ ላይ የሚጨምርና ከቃሉም የሚቀንስ ጥብቅ ቅጣት እንዳለበት የሚናገረውን ክፍል አውቀውት የነበረ መሆን አለበት፡፡

እግዚአብሔርና አላህ

ክርስትያኖችና ሙስሊሞች አንድ ዓይነት እግዚአብሔርን ያምናሉን? ይህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይጠየቃል፡፡ በእርግጥ ሁለቱም ያተኮሩት አገልግሎት፣ እምነትና ታዛዥነት እንዲሁም አምልኮ የሚገባውን አንድ አምላክን በማክበር ሐሳብ ላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ታላቁን አምላክ በመግለጥ ላይ ልዩነቶች አሏቸው፡፡ ለምሳሌም ያህል የሚከተለውን ማብራሪያ እንመልከት፡- እንበልና ሁለት የተለያዩ ሰዎች አያሌው የተባለ አንድ የጋራ ጓደኛ እንዳለቸው ያስባሉ፡፡ እነሱ ሁለቱም አያሌውን እንደሚያደንቁት ይስማማሉ፡፡ ስሙም አንድ ነው፡፡ ነገር ግን አንደኛው አያሌው ረጅም፣ ቀይ እራስ ያለው ሰው ነው ሲል ሌላው ግን ባለመስማማት አያሌው አጭር ነው ፀጉሩም ደግሞ ነጣ ያለ ሰው ነው አለ፡፡ እነዚህ ልዩነቶች እጅግ በጣም ሃይለኛዎች ናቸው፡፡

በአላህና በእግዚአብሔር መካከል መመሳሰሎች ቢኖሩም እንኳን እጅግ በጣም ብዙ የሆኑም ልዩነቶችም አሉ፡፡ የመጀመሪያውም በሥላሴ ላይና በጌታ ኢየሱስ አምላክነት ላይ ነው፡፡ ሩቅ የሆነው አምላክ - አላህ - በክርስቶስ በኩል ሰው ከሆነው - ከእግዚአብሔር - ጋር በፍፁም አይመሳሰሉም፡፡

ቁርአን አላህን የሚያቀርበው ከፍጥረቱ እንደራቀ አድርጎ ነው ነገር ግን በግለሰብ ሕይወት ውስጥ ያለውን ግንኙነትና ጥቃቅኗን ነገር ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡ አላህ ከፍ ብሎ የነገሰና በነቢያትና በመላእክት በኩል የሚናገር ነው፡፡ እርሱም የእያንዳንዱን ግለሰብ ስራዎች የሚወስድና ክፉን ከመልካሙ ጋር የሚመዝን ነው፡፡ ምህረትንም ለሚገባቸው ብዙ ጊዜ ያሳያል በተለይም እነሱ በእስልምና የሚያምኑ ከሆነ ነው፡፡ ከዙፋኑም ሆኖ እርሱ ሙሉ ለሙሉ ሁሉንም ነገር ይቆጣጠራል፡፡ ይህም የሚጨምረው ነገር ቢኖር የግለሰቦችን ሕይወት የዘላለምን ፍፃሜ እንዲሁም የእያንዳንዱን ጦርነት ውጤትም ጭምር ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የገለጠው ነገር እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ አምላክ ነው ደግሞም በባህርዩ ቅዱስ ሲሆን ከሕዝቡም የፅድቅን ሕይወት ይጠይቃል፡፡ በ1ኛ ዮሐንስ 4.8-11 ላይ እንደተገለጠውም እርሱ ፍቅር ነው፡፡ ይህም ፍቅር በወንጌሎች ውስጥ በግልጥ ተገልጧል፣ የወንጌልም መልእክት የሚናገረው እግዚአብሔር ወደ ዓለም በክርስቶስ በኩል በእርሱ የሚያምኑትን ለማዳን እንደመጣ ነው፡፡ ክርስትያኖች በጥምቀት የሚያውጁት ነገር እነሱ ከሁሉን ቻዩ አምላክ ጋር ወደ ግል አንድነት ውስጥ መግባታቸውን ነው፡፡ ይህም የግል ግንኙነት እነሱ ሕያው እግዚአብሔርን እንደ ሰማያዊ አባታቸው አድርገው እንዲያውቁት አስችሏቸዋል፡፡ ይህ ጥብቅ ግንኙነት እንዲቻል የተደረገው በክርስቶስ በኩል ነው፡፡ የዕብራይስጡ ኢየሱስ የሚለውም ስም የሁለት ቃላቶች ማለትም ‹ያህዌ ደኅንነት› ነው የሚሉ ቃላቶች ድብልቅ ውጤት ነው፡፡

በአላህና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ሌላው ልዩነት በእነሱ ምህረት ዙሪያ ላይ ያለው ነው፡፡ በእስልምና ደኅንነት የሚባለው ነገር የተመሰረተው በሙስሊሞች ጥረትና እምነት ላይ ነው፡፡ በሌላ ጎኑ የምናገኘው የእግዚአብሔር ፍቅር ታላቅ ሆኖ ነው፡፡ በመሆኑም በምንም ሰዋዊ ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ነው፡፡ ይህንንም እውነታ ጌታ ኢየሱስ አባካኙን ልጅ ለመገናኘት የወጣውንና የሮጠውን አባት ምሳሌ ሲናገር ገልጦታል ሉቃስ 15፡፡ ለዚህ ምሳሌ እውነታ ያለው ሙስሊሞች ምላሽ ‹አላህ እንደዚህ ዓይነት ነገርን አያደርግም› የሚል ነው፡፡ የዚያን ዓይነት ፍቅር የአላህ ባህርይ አይደለም፡፡

ለእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ (ክርስትያኖች) ይህ የእግዚአብሔር ፀጋ ፍፁም ምሳሌ ነው፡፡ እነሱም ያስተዋሉት ነገር ቢኖር ደኅንነት የእግዚአብሔር ነፃ ስጦታ እንደሆነ ነው ኤፌሶን 2.8-9፡፡ ደኅንነት በስራ አይገኝም ወይንም ለእኛም አይገባንም፡፡ በሰማያዊ አባቱ ለእሱ የተሰጡትን ሰዎች አንዳቸውንም ጌታ ኢየሱስ በፍምፁም አይጥላቸውም ዮሐንስ 6.35-40፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግልጥ ያደረገውም ነገር መልካም ስራ ከክርስትያኖች ሕይወት ውስጥ በተፈጥሮ የሚመነጭ እንደሆነ ነው ምክንያቱም እነሱ አዲስ ፍጥረት ናቸውና ክርስቶስም በእነሱ ውስጥ ይኖራልና ኤፌሶን 2.10፡፡

በአላህና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ሌላው ልዩነት በስላሴ ላይ ነው፡፡ ክርስትያኖች የሚያውቁት እግዚአብሔር ምስጢራዊ በሆነ መንገድ ከአዕምሮአችን በላይ እንደሆነ ነው፣ ምክንያቱም ስላሴ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተገልጧልና ማቴዎስ 28.18-20፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የገለጠው አንድ አምላክ እንዳለ ነው ይህም አንድ አምላክ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ሲሆን ክርስትያኖች ይህንን የገለጡት ስላሴ (ሦስት በአንድ) በማለት ነው፡፡ የስላሴም አንድ ማብራሪያ ሊሆን የሚችለው የፀሐይ ምሳሌ ነው፡፡ ፀሐይ ያለማቋረጥ ብርሃንንና ሙቀትን ትሰጣለች እንዲሁም ስላሴ ሁልጊዜ የአንዱ እግዚአብሔር መግለጫ ነው፡፡ ይህንን ምሳሌ ለመቀጠል ያህል ፀሐይ የብርሃን ጨረሯን እንደምትሰጥ ሁሉ ልክ እንደዚሁ አንዱ እግዚአብሔር ዓለምን ለመፍጠር ቃሉን ልኳል፣ ለነቢያቱ ተገልጧል ከዚያም ይህ የእግዚአብሔር ብርሃን በክርስቶስ በኩል ሰው ሆኗል ዮሐንስ 1 እና ዕብራውያን 1.3፡፡ በመጨረሻም ፀሐይ ሙቀቷን እንደምትሰጠው ሁሉ እግዚአብሔርም የማይታየውን የመንፈስ ቅዱስን ሕልውና ወደ አማኞች ሕይወት ውስጥ ይልካል፡፡ ሌላው ምሳሌና በጣም ግላዊ የሆነው ደግሞ የእያንዳንዱ የግል ተፈጥሮ በጣም ግሩምና ድንቅ መሆኑ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ምሳሌ በትክክል የስላሴን እውነታ ሊገልጠው አይችልም ነገር ግን ስላሴ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትክክልና በግልጥ ተቀምጧል፡፡ ይሁን እንጂ በቁርአን ውስጥ ተክዷል፡፡

የቁርአኑ አላህ ከመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ጋር ተመሳሳይ ነውን? ቁርአን የሚናገረው እግዚአብሔርና አላህ አንድ እንደሆኑ አድርጎ ነው፣ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ክርክር አለ፡፡ የአረብኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የእግዚአብሔርን ስም አላህ ነው በማለት እግዚአብሔርን ወይንም ያህዌን ለመወከል ቢጠራውም እንኳን የክርስትና ግንዛቤ ግን በጣም የተለየ ነው ስለዚህም እነዚህ ሁለቱ አንድ አምላክን የሚጠሩ ስሞች አይደሉም፡፡

የቤተክርስትያን ስኬት

የክርስቶስን ተልእኮ በተመለከተ ክርስትያኖችና ሙስሊሞች ያላቸውም አመለካከት ልዩነት አለው፡፡ እስልምና የተመሰረበት ሐሳብ ክርስቶስ የጀመራት ቤተክርስትያን ከመጀመሪያው እንዳልተሳካላት ነው፡፡ ስለዚህም እነሱ የሚያምኑት ከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ መሐመድ የመጣው በክርሰቶስ ወንጌል አማካኝነት የተፈጠረውን ችግር ለማስተካከል ነው፡፡

ክርስትና በሌላው ጎኑ የሚያምነው ክርስቶስ ኢየሱስ ጠንካራዋን ቤተክርስትያኑን በተመረጡት ደቀመዛምርቱ ላይ እንደመሰረታት ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዓለም አቀፍ በመሆን በፍቅርና በመልካምም ምስክርነትና ስራ ቤተክርስትያን እያደገች ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ቃል ኪዳንን የገባው የገሃነም ደጆች የቤተክርስትያንን ዕድገትና የወንጌል ስራ ሊገቱት እንደማይችሉ ነው፣ ስለዚህም በእያንዳንዱ አገር ቋንቋ እና ሕዝብ በምድር ላይ ተሰሚነትን አግኝቷል ማቴዎስ 16.18 እና ማቴዎስ 24.14፡፡ ጌታ ኢየሱስ መከፋፈሎች እንዳይኖርና ደቀመዛምርቱ አንድ እንዲሆኑ ፀልዮአል፣ ነገር ግን ቤተክርስትያኑ እንደምትወድቅና ሌላ እረኛ ወይንም ነቢይ እንደሚነሳላት በፍፁም ትንቢትን አልተናገረም፡፡ በአንፃሩ ደቀመዛምርቱን ያስጠነቀቀው ነገር ቢኖር የሐሰት ነቢያት ከእሱ በኋላ እንደሚነሱና እንደሚመጡ እነሱም አስደናቂ ተዓምራቶችን እንኳን እንደሚያደርጉ እንዲሁም ብዙ ተከታዮችንም እንደሚያፈሩ ነው ማቴዎስ 24.11፡፡

ቤተክርስትያን ምንድናት? ታሪክ የሚያስተምረን ቤተክርስትያን የሁለት ሺ ዓመት የሴቶችና የወንዶች አማኞች እና የተጠመቁ የእግዚአብሔር የሆኑ እና እርስ በእርስም አንድ የሆኑ አማኞች ማህበረ ሰብ እንደሆነች ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እነሱን ለመግለጥ እጅግ ብዙ ምሳሌያዊ ስሞችን ይጠቀማል፡፡ እያንዳንዱ አማኝ በቤተመቅደስ ግንቡ ውስጥ ያለ ድንጋይ ነው በዚያም የማዕዘኑ ራስ ድንጋይ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው ኢሳያስ 28.16፣ ኤፌሶን 2.19-22፡፡ እነሱም የክርስቶስ አካል እና እያንዳንዱም የዚያ አባላት ናቸው 1ቆሮንቶስ 12.27፡፡ እነሱ የተመረጡ ሕዝቦች እንዲሁም የተቀደሱ ሕዝቦች ናቸው 1ጴጥሮስ 2.9-12፡፡ እነሱም የአንዷ ቤተክርስትያን የተጠመቁ አባላት ናቸው ያችም ቤተክርስትያን ጌታ ኢየሱስ ከደቀመዛምርቱ ጋር የጀመራት ናት ገላትያ 3.26-29፡፡

ቤተ እምነቶች የሚባሉት የአብያተ ክርስትያናት (አገር አቀፍ) ማህበራትስ? በዓለም ውስጥ ያሉት ቤተክርስትያናት በቤተ እምነት ልዩነቶች ቢከፋፈሉም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው እነሱ አንድ የሆኑ የአማኞች ኅብረት እንደሆኑ ነው፡፡ እነሱ አንድ ሆነዋል በዚያም እነሱ ሁሉም በአንዱ በስላሴ ያምናሉ፣ በአንዱ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በክርስቶስ የማዳን ስራ እና በትንሳኤው ያምናሉ፡፡ ቤተክርስትያናትም ከሐዋርያት ጊዜ ጀምሮ የታቀደላቸውን ዓላማ ለማሳካት አግልግሎታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልም የተነሳ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሰዎች ሁሉ ያሳያሉ በዚህም በጎ (ምግባረ ሰናይ) ስራዎችን ይሰራሉ ሆስፒታሎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ሚሽነሪዎችን እንዲሁም ደግሞ በፍቅር የተሞላ አንድነትና ሕብረትን ያሳያሉ፡፡

ቤተ እምነቶችን የሚያልፈውን የቤተክርስትያንን መሠረታዊ አንድነት በተመለከተ ያለው አንዱ ምሳሌ በመስከረም 2001 በአሜሪካ ከሆነው ነገር ሊወሰድ ይቻላል፡፡ ከመስከረም (9/11) ጥቃት በኋላ ዓለም ያየው ነገር፣ በአገሪቱ ውስጥ ብዙ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢኖሩም በዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ ዜጋነታቸው፣ የጋራ ነፃነታቸው ሲጠቃ ነፃ የሆኑት ሕዝቦች በአንድነት ቆሙ፡፡ ሁሉም ለአገራቸው ያላቸውን የጋራ ፍቅር ገለጡና አሳዩ፡፡ ለነፃነት ያላቸው ፍቅር እና በአሜሪካን ውስጥ የሚደሰቱበት ነፃነት እያንዳንዳቸው ልዩነቶች ቢኖሩአቸውም ወደ አንድነት አመጣቸው፡፡ ክርስትያኖች ሁሉ ለሚያጠኑት መጽሐፍ ቅዱስ ይህ ምሳሌ የሚሆነው አሜሪካኖች አንድ ሰነድን የሚወዱ በመሆኑ ላይ ነው፣ ያም የአሜሪካን መንግስት የሕገመንግስት ለጋራ ሕይወታቸው መመሪያ ሰነድ በመሆኑ ነው፡፡ አሜሪካኖች በአንድ ባንዲራ ዙሪያ ተሰባስበዋል (ልክ መስቀል የክርስትያኖች ሁሉ የጋራ ምስል እንደሆነው ሁሉ) ይህም ክርስትያኖች ሊበራልም ሆኑ አጥባቂዎች መስቀል ምልክታቸው እንደሆነው ማለት ነው፡፡ 

ጌታ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስና በቁርአን

መጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ስለጌታ ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ስዕሎችን ይሰጡናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የጌታ ኢየሱስን ምድራዊ አገልግሎት በተመለከተ የብዙ የዓይን ምስክሮችን ዘገባ ይሰጠናል፡፡ ይህም አዲስ ኪዳን ስለጌታ ኢየሱስ ለሚለው ብዙ ታማኝ የሆኑ ነገሮችን ይሰጠናል፡፡ እሱም የክርስቶስን አገልግሎት ክስተቶች በጊዜያቸው በሚያውቁ ሰዎች ተነቦ ነበር በእነሱው ዘመን የተከናወነ የቅርብ ታሪክ ነበርና፡፡

ክርስትያኖች የሚያምኑት የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔርን ነቢያትና ሐዋርያትን ሲጽፉ ይመራቸው እንደነበረ ነው፡፡ እነሱ ሁሉም የተስማሙት በኢየሱስ ውስጥ የሰው ዘር ሁሉ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳየ ይህም የሆነው የማይታየው አምላክ ምሳሌ (ምስል) በአይሁዳዊ ነቢይ በኢሳያስ ትንቢት ኢማኑኤል ማለትም ‹እግዚአብሔር ከእኛ ጋር› ተብሎ ኢሳያስ 7.14 ማቴዎስ 1.23 በተነገረለት ሰው በኩል እንደታየ ነው፡፡ ሐዋርያቱም የጻፉት በኢየሱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ሙላቱ በእውነተኛ ሰው ውስጥ እንደኖረ ነው ቆላስያስ 2.9፡፡

በዚያ ማህበረ ሰብ ውስጥ የተዘነጉትንና እንደጠቃሚ የማይታዩት የነበሩትን ልጆችን ኢየሱስ እንዴት ያዝንላቸው እንደነበረ ሐዋርያቱ ይነግሩናል፣ ኃጢአተኛ ሴቶችን የተናቁትንና የተወገዙትን፣ የተጠሉ እና ከማህበረ ሰቡ የተገለሉትን የቀረጥ ሰብሳቢዎችን እንዴት ያዝንላቸው እንደነበረ ይነግሩናል፡፡ በበሽታ ላይ፣ በክፉ ኃይላት ላይ፣ በማዕበል ላይ፣ በሞት ላይ፣ በራሱም ሞት ላይ እንኳን የነበረውን ኃይሉን ይነግሩናል፡፡ ስለ ስነምግባር ያስተማረው ከፍተኛ ትምህርት እስከ አሁን ድረስ በዓለም ውስጥ እንደተከበረ ነው፡፡ በመስቀል ላይ የከፈለው መስዋዕትነት በትንሳኤው የተቀዳጀው ድል በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ቃሉን በጻፉት ሐዋርያት ዘንድ ሁሉ ማዕከላዊ ሐሳቦች ናቸው፡፡

የክርስቶስ ሐዋርያት፣ የክርስቶስ ሕይወት የዓይን ምስክሮች፣ በአንድነት (ያለምንም ልዩነት) የሚስማሙት ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እና ብቸኛ አዳኝ እንደሆነና ለሚቀበሉት እና በእሱ ለሚያምኑት አዲስ የሆነውን የዘላለምን ሕይወት ብቸኛ ሰጪና አዳኝ በመሆኑ ላይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የመዘገበው ነገር የጥንቷ ቤተክርስትያን የተሰራችው በተጠመቁ እና የወንጌልን መልክት፣ የክርስቶስ ፍቅርና ኃይል አብሯቸው እና በእነሱ ውስጥ እየሰራ በሰላም በሚያሰራጩ ክርስትያኖች ነው፡፡

ከክርስቶስ 700 ዓመታት በኋላ ቁርአን መጽሐፍ ሆነ፡፡ ይሁን እንጂ የክርስቶስን ደቀመዛምርት የዓይን ምስክርነት ዘገባ ይቃረናል፡፡ ቁርአን የሚቀበለው ኢየሱስ ለረጅም ዘመናት ሲጠበቅ የነበረው የአይሁድ መሲህ እንደሆነ፣ እሱም ከድንግል እንደተወለደ፣ ተኣምራትን እንደሰራ ወንጌልንም (ማለትም የምስራችን ዜና) እንዳመጣ ይቀበላል፡፡ ይሁን እንጂ ቁርአን ኢየሱስን ከእግዚአብሔር ልጅነት አውርዶት ከሌሎች መጽሐፍ ቅዱስ ነቢያትና ከመሐመድ ጋር እኩል አድርጎታል፡፡ ቁርአን አይሁዶች ክርስቶስን አልገደሉትም በማለት ይናገራል፣ የሆነውም ነገር እነሱ የገደሉት መስሏቸው ብቻ ነው ይላል፡፡ አላህ ወደ ላይ ወሰደው በማለት ይናገራል፡፡ ይህንን አባባል ብዙዎቹ ሙስሊሞች የሚተረጉሙት አንድ ሰው እንደ ይሁዳ ያለ፣ ጌታ ኢየሱስን የሸጠው ሰው፣ ኢየሱስን እንዲመስል ተደረገና በእሱ ቦታ ሲሞት ኢየሱስ ግን በምስጢር ከዚህ ዓለም ተወሰደ በማለት ነው፡፡

ቁርአን ትክክል ከሆነ ኢየሱስ ትቶ የሄደው ነገር እጅግ በጣም ትልቅ መምታታትን ነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የኢየሱስ ሐዋርያት አላህ ባመጣው የማስመሰል ማታለል ላይ ተመርኩዘው፣ በመስቀሉ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ቤተክርስትያንን ስለመሰረቱ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነሱ ሁሉም ጌታ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ እንዳዩት ተናግረዋል፡፡ መሐመድ የሚናገረው ግን ዘመናትን ያሳለፈውንና እውነት እንደሆነ የታመነውን፣ የዓይን ምስክሮች ያሉትን ነገር እንደ ስህተት ቆጥሮ እሱን ለማረም ምሪትን ወይንም መገለጥን እንዳገኘ ነው፡፡ የቁርአን ሐሳብ እውነት ከሆነ ለሦስት መቶ ዓመታት ያህል በሮማውያን ስደት አማካኝነት የተገደሉት እጅግ በጣም ብዙ የክርስትና ሰማዕታት ሕይወት ያለፈው በከንቱ ነበር ማለት ነው፡፡

ኢየሱስና መሐመድ

የኢየሱስና የመሐመድ ሕይወትም ልዩነቶች አላቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጠቃልለው ኢየሱስ የምድር ሕይወቱን ያጠቃለለው ሳያገባ፣ ድሃ እና ዓመፀኛ ሳይሆን ነው፣ ይህም ደግሞ የብዙ ታላላቅ ተዓምራቶች ምንጭ ሆኖ ነው፡፡ የኢየሱስም የመጨረሻው ተዓምር የራሱ ከሞት መነሳት ነው፡፡ ለምድራዊው አገልግሎቱ ማብራሪያነት በማርቆስ 10.45 ላይ የተናገረው ሊያገለግል እንጂ ሊገለገል እንዳልሆነ ነው፡፡

መሐመድን በተመለከተ ግን ሊነገር የሚችለው ተቃራኒው ነው፡፡ እርሱ በዘመናት ውስጥ በችግር ውስጥ በማለፍ ትግልን አድርጓል፣ ነገር ግን ፍፃሜው አካባቢ ብዙ ሚስቶችንና ቅምጦችን አድርጎ ነው፡፡ እርሱም እጅግ በጣም ሃብታም ሆነ ይህም በወታደራዊ ጦርነት እና ሙስሊም ያልሆኑትን ጭቆና የሞላበት ታክስ በማስከፈል ነበር፡፡ የሙስሊሞች አፈታሪኮች መሐመድ ተዓምር ሰርቷል በማለት ቢናገሩም እንኳን ቁርአን እራሱ የሚናገረው እርሱ ምንም ተዓምራትን እንዳላደረገ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ያሉ ሙስሊሞች ቁርአን ለመሐመድ ተዓምር ነው በማለት ይናገራሉ፡፡ ይህ ሊሆን ይችላልን? የሚከተሉት ምዕራፎች ሙስሊም ያልሆኑ ብዙ ሰዎች እነዚህን ነገሮች ለእራሳቸው እንዲመረምሩ በጣም ይረዷቸዋል፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡-

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የቀረቡት አራት ንዑስ ርዕሶች ስለ ክርስትናና እስልምና መሠረታዊ ግንዛቤን ይሰጡናል፡፡ አንድ ሰው የአንድ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ፣ እኔ በሃይማኖቴ እረክቻለሁ በማለት ለእውነት ሁሉ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት እራሱን በሚሰማውና በመጠኑ በሚያውቀው ነገር በመሸፈን ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ትልቁ ጥያቄ ያ ሰው የሚከተለው ሃይማኖት እውነት ካልሆነስ የሚለው ነው፡፡ ስለዚህም ለሙስሊም አንባቢዎች የምናሳስበው፣ የእስልምና ሃይማኖት ሲጀመር የተመሰረተው በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀባይነት ላይ ተንተርሶ እንደነበረ እና ቀስ በቀስም እያፈገፈገ መጽሐፍ ቅዱስን በመቃወም ወይንም በሚቃረን ሐሳብ እየተሞላ እንደመጣ እንዲገነዘቡ ነው፡፡

በመሠረቱ እውነተኛውና ትክክለኛው ሃይማኖት ማስረጃ እና ምስክሮች ያሉት ነው፡፡ ይህንንም የምንረዳው በአምላካችን በእግዚአብሔር በተሰጠን አስተዋይና አመዛዛኙ ሕሊናችን አማካኝነት እውነትን ለመረዳት ፈቃደኞች ስንሆን ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን ጽሑፍ ለሚያነቡ ሙስሊሞች ሁሉ የምናቀርበው ጥሪ ማስረጃዎችን እንዲመረምሩና እውነቱን ከስህተት በመለየት ወደ እውነቱም እንዲመጡ ነው፡፡

ይህ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም የዘላለምን ሕይወት የት እንደምናሳልፈው የሚወስነው እምነታችን ነው ብለን የምንከተለው ነገር ነውና፡፡ ይህንን በተመለከተ እንከን የሌለው የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው፣ ‹በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና› በማለት በዮሐንስ ወንጌል 3.16 ላይ ያበስረናል፡፡ የዘላለም ሕይወት በጌታ በኢየሱስ በማመን የሚገኝ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳትሉ ይህንን እውነተኛ የዘላለም ሕይወት ስጦታ ለመቀበል ወደ ጌታ ኢየሱስ ኑና ኃጢአታችሁን ተናዛችሁ ይቅርታንና ስጦታውን ከእርሱ ዘንድ ተቀበሉ፣ ከዚያም በሕይወታችሁ ውስጥ ከዚህ በፊት አይታችሁት የማታውቁት አዲስ ሰላም፣ አዲስ ደስታ፣ አዲስ ተስፋ እና እውነተኛ የሆነ አዲስ ሕይወትን ታገኛላቸሁ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: Christianity and Islam,  Chapter 2 of "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: ርእሳዊ የቁርአን ጥናት በክርስትና አይን ሲመረመር

ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ