የቁርአን ውጪያዊና ውስጣዊ ሁኔታ ሲገመገም

በJay Smith

[ክፍል አንድ] [ክፍል ሁለት]

ትርጉምና ቅንብር በAI አማርኛ ቡድን

በቁርአን ውስጥ ስላሉት የተምታቱ ታሪኮችና ስሞች፡-  ቁርአን ስለተጠቀመባቸው የተምታቱ ታሪኮችና ስሞች መጠየቅ ይቻላል፡፡ ቁርአን ስለ ኢብራሂም የሚናገረው ስለ መጽሐፍ ቅዱሱ አብርሃም ከሆነ ተሳስቷል፡፡ አብርሃም በመካና በመዲና ስለመኖሩ የታሪክም የከርሰ ምድራዊም ማስረጃ አልተገኘም ጣዖታትን የሰባበረበት ታሪክም በመጽሐፍ ቅዱስም ውስጥ የለም፡፡ ይልቁንም ከአባቶቹ ሃገር ርቆ እንዲሄድ በእግዚአብሔር መጠራቱን በዘፍጥረት 12.1 እና በዘፍጥረት 15.7 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል #የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብረሃም በካራን ሳይቀመጥ ገና በሁለት ወንዝ መካከል ሳለ ታየና ከአገርህ ከዘመዶችህም ወጥተህ….ና አለው፣ በማለት የአዲስ ኪዳኑም ሐዋርያት ስራ 7.2-4 ይነግረናል፡፡ ስለዚህም አብርሃም የነበረው ዑር በሚባለው ምድር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ወንዞችም ጢግረስና እና ኤፍራጥስ እንጂ ሁለት ከተሞች መካና መዲና አልተባሉም እነዚህ ወንዞች የሚገኙትም በፋሪስ ባህረ ሰላጤ ባቢሎን (የዛሬዋ ኢራቅ አካባቢ ነው) የተለወጠ መልክዓ ምድር የለም፡፡ 

የአብርሃምን የትውልድ ሐረግ በዘፍጥረት 11. ውስጥ ተጽፎ እናገኛዋለን፡፡ ‹ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ታራንም ወደለ ታራንም ከወለደ በኋላ ታራን 119 ዓመት ኖረ፤ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፡፡ ‹የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው፡፡ ታራ አብራምን ናኮርንም ሐራንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ፡፡ ሐራንም በተወለደበት ሀገር በከላዳውያን ከተማ ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ› ዘፍጥረት 11.27-28 በማለት ይናገራል፣ እውነቱ ይኽ ነው፡፡ 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጣዖታትን የሰባበረው ጌዴዎን ነው፡፡ ጌዴዎን ደግሞ ከእስራኤላዊያን መሣፍንት አንዱ እስራኤላውያንን ከምድያማውያን ጥቃት ሊያድን የተጠራ በኣል የተባለውን የጣዖት መሠዊያ ያፈራረሰ ነው፡፡ ከዚያም ስሙ ይሩበአል ተብሎ የተጠራ ከ32,000 ሠራዊት በ300 ብቻ በእግዚአብሔር ኃይል ድልን የተቀዳጀ ሰው ነው፡፡ ታሪኩን በመጽሐፍ ቅዱስ መሳፍንት ምዕራፍ 6 ውስጥ ያለምንም ማምታታት መመልከት ይቻላል፡፡ 

ላቆምከው ምሥል አንሰግድም በማለት ፀንተው ድልን የተቀዳጁትም ሚሳቅ ሲድራቅና አብድናጎም እንጂ አብራም አይደለም፡፡ ታሪኩንም በዳንኤል ምዕራፍ 3 ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ዘመኑም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ539 ዓ.ቅ.ክ ነው ይህም ማለት በቁርአንና በዚህ ታሪክ ዘገባ መካከል የ1,1ዐዐ ዓመታት ልዩነት አለ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህ ስያሜዎች በእርግጥ በአንድ አምላክ እውቅና ባለው የዘመናት ሂደት ውስጥ የተከናወኑ ከሆነ ቁርአን አዛብቷቸዋል ለውጧቸዋልም፡፡ ወይም የሚያወራው ስለ ሌላ አብርሃም ካልሆነ በስተቀር እውነቱ ይኸው ነው፡፡ እንግዲህ እነዚህን የተደበላለቁ ገለፃዎች ማጥራት የቁርአን መልእክተኞች ድርሻ ነው፡፡ የቁርአን የተወሰኑ አንቀፆች ሚድራስ-ራባህ ከተባለው በ2ኛ ክፍለ ዘመን ከተፃራሪ አይሁዳዊ አፈታሪክ እና ጆንስ ቤን ዑዚል ከተባለ ሌላ የአፈታሪክ ጋር መልእክቱ ተመሣሣይ እንዲያውም ቀጥተኛ ቅጂዎች ናቸው፡፡ ለዚህም ማስረጃ ስለ ኢብራሂም በአል-አንቢያ ምዕራፍ ቁጥር 66 የተተረከው በእነዚህ መጽሐፍቶች ውስጥ በቀጥታ ይገኛል፡፡ መጽሐፎቶቹን London,England ከብራቲሸ መጽሐፍት ቤት ማግኘት ይቻላል፡፡ በሙስሊሞች ዘንድ እንደሚባው ቁርአን ከሰማይ መዝገብ “ከኡሙ አልኪታብ” የተቀዳ ነው ይባል እንጂ እዚህ ከመሬት ላይ በሰው ከተጻፈ አፈ ታሪክ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ 

የተጠቀሱትን መረጃዎች ስንጠቅስ ታሪኮቹ የተጻፉበትን ዘመን እንዲሁም በሰው የተዘጋጁ ስለመሆናቸው እርግጠኛ በመሆን ነው፡፡ መቼም እነዚህ ታሪኮች አፈ ታሪክ እንጂ የመለኮት መገለጦች አይደሉም፡፡ ቁርአንን በጥልቀት ባጠናነው መጠን የመልእክቱን ምንጭ አብጠርጥረን ለማወቅ አያዳግተንም ምርመራችን ይቀጥላል፡፡

የሰለሞንና የንግስተ ሳባ ታሪኮች ተብለው በመጽሐፈ ቁርአን አን-ነምል የተዘገበውን ደግሞ እንመልከት፡፡ ንግስተ ሳባ ለመወያያት ወደ ንጉስ ሰለሞን በመራመድ ላይ እያለች ከፊት ለፊትዋ ያለው ወለል ውሃ መስሏት ቀሚሷን ወደላይ ስብስብ እንዳደረገች በመተረክ የቀጠለው ቁጥር 44 ያለው ታሪክ ከወዴት እንደተገኘ እንጠቁም፡፡

ይህ ታሪክ እንዳለ ታንጉን ኦፍ ኢሸተር (Tangun of Esther) ከተባለ መጽሐፍ የተወሰደ አፈ ታሪክ ነው በምዕራፍ ያለው የሰለሞን የወፎች ሰራዊት የ2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አፈ ታሪክ እንጂ ከሰማይ የመጣ መልእክት አይደለም፡፡ እንዲያውም ከቁርአን ቀድሞ የተጻፈው አፈታሪክ ንግስተ ሳባ ቀሚስዋን ወደ ላይ ሰብሰብ ስታደርግ ንጉስ ሰለሞን የባቶችዋን ውበት በመመልከት ደንግጦ እንደጨኸ ነው የሚተርከው ቁርአን በአል-ነምል 44 ግን የንጉስ ሰለሞንን መጮኽ በመተው ነው የዘገበው፣ ታዲያ ይህ እንዴት የመለኮት ቃል ሊሰኝ ይችላል?

አብዛኛው ሙስሊም እነዚህን የቁርxን ክፍሎች በወጉ አያውቃቸውም፡፡ ባያውቃቸውም እንኳን ሁሉም የአላህ መገለጥ እንደሆኑ ተደርጎ ስለተማረ ምንም አስተያየትና ጥያቄ ለማቅረብ አይፈቀድለትም ጥያቄ ካነሳም፣ ኩፋር /ወይም ከሐዲ ስለሚባል/ ይፈራልና፡፡ ነገር ግን እውነትን ፈላጊዎች ለሆኑት እነዚህን ታሪኮች መመርመር እንዳለበት እንጠቁመዋለን፡፡

ስለ ቁርxን ስህተት አርተር ጄፍሪ የተባለው የቁርxን ሊቅ /ተመራማሪ/ ቁርአንን እንኳን በስህተት አልባነት ለመወሰን ይቅርና ራሱ ቁርአን አንድ ብቻ ያልነበረና አስራ ስድስት ዓይነት የቁርአን ቅጂዎች እንደነበሩ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ይህም እስከ ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ማለት ነው፡፡ እስልምና ከመጣበት ከ61ዐ-632 ባሉት 268 ዓመታት መካከል መሆኑ ነው፡፡

ቁርአን ከመጽሐፍ ቅዱስ ከብሉይና ከአዲስ ኪዳን የሚታወቁ ስሞችን ይጠቅሳል፡፡ ለምሳሌ በአል-አንቢያ ምዕራፍ 51-71 ያለው ታሪክ ፈፅሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጣጣም አይደለም፡፡

ስለ ይስሐቅና ኢስማኤል አባት ወይስ ሌላ ሰው ነው የሚተርከው? መልስ አንጠብቅም ግን ጥያቄያችንን እንቀጥላለን፡፡ በአል-አንአም ምዕራፍ ቁጥር 34 ላይ የአላህን ንግግሮች ለዋጭ የለምና በቁጥር 115፣ የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትሆን ተፈፀመች ለቃላቱ ለዋጭ የለም በማለት ተናግሯል፡፡ እንግዲህ አላህ የአብርሃም የሙሴ የይስሐቅና የእስማኤል አምላክ ከሆነ፣ ደግሞም የአላህ ቃል የማይለወጥ ከሆነ፤ የቁርአኑ ነቢያትና ስማቸው ከሞላጎደል የተጠቀሱት በእርግጥ እነሱ ከሆኑ፣ ስለምን ታሪካቸውን በመቀየር በማዛባት አዲስ ገለጣ ለመሐመድ ሊነገር ቻለ፡፡ የአብርሃም አምላክ ቃሉን የማይለውጥ እንደሆነ እናምናለን ነገር ግን የቁርአኑ መልእክት የተዛባው ከተቀባዩ? ወይስ ከጸሐፊው ነው? 

በአልጀዚራ ቻናል ቁርአን እንዴት ሳይንሳዊ መረጃዎች ጋር እንደሚስማማ እና ከሳይንስ ምርምር ግኝቶች መምጠቅ ከ1ዐዐዐ ዓመታት በፊትና ቀድሞ እውነትን የገለጠ መጽሐፍ፣ ፍፁም መለኮታዊ መገለጥ እንደሆነ ሼህ ዩሱፍ አልቀርዳዊ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሼኩ መጽሐፍቶችንም ጽፏል፡፡ ነገር ግን አንድ ድንቅ ጥያቄ መጠየቅ እንዳለበት አጋግጠናል፡፡

ሼህ ዮሱፍ እንደሚለው ከሆነ ቁርአን፣ ፅንስ አፈጣጠርና ዕድገት አራት ደረጃዎችን ገልጧል፡፡ በመሆኑም 1ኛ. የፈሳሽ መልክ 2ኛ. የረጋ ደም 3ኛ. የአጥንት 4ኛ. የስጋ መልበስ ደረጃዎችን በተከታታይ እንደሚፈጠረ ነው፡፡ ይህንንም የቁርአን የሚለውን ገለጣ ሳይንሳዊ ነው ይለናል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የሳይንስ ምርምር ውጤት በየወቅቱ የሚያድግ አንድ ጊዜ ተገኘ የተባለው ሌላ ጊዜ እየተሻረ እየተሻሻለ መሄዱን እናውቃለን እናም ይህ ቁርአን ገለጠው የተባለው ግኝት ጌለፕ የባለው አይሁዳዊ የስነ-ፅንስ ተማራማሪ አራት ደረጃዎች ናቸው ብሎ ያቀረበው ነው፡፡ ይህ የጌለፐ ምርምር በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሳይንስ ምርምር ውድቅ ተደርጓል፡፡ አዲሱ የሳይንስ ጥናት ግኝት ስጋና አጥንት እኩል የሚያድጉ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ይህም የዕድገት ደረጃውን ወደ 3 ቀንሶታል፡፡ የጌለፕም ምርምር ለመነሻነት አገልግሏል እንጂ ቁርጠኛ እውነት ሊሆን አልቻለም፡፡ 

እንግዲህ የቁርአን ሊቃውንት ቁርአናቸውን ይለውጡታል አይባልም የምርምር ውጤቱን ከመተው ውጪ ሌላ መንገድ የላቸውም፡፡ ቁርአንን የላቀ መለኮታዊ ለማድረግ የሚገባበትን ቀዳዳና ችግር ሁሉ እስኪ ተመልከቱ! ስህተት መሆኑ ብቻ ሳይህን የተፈጥሮ ሳይንስን ለመለኮታዊ መልዕክት ማስረጃ በማቅረብ ዕውነትን ከማረጋገጥ ስህተት ላይ መውደቅን እንደሚያስከትል ጭምር ማወቅም ተገቢ ነበር፡፡ 

በአል-አዕራፍ ምዕራፍ 124 የተጠቀሰውን ስለ ስቅላት የተናገረውንና በዮሱፍ ምዕራፍ 41 ያለውን ችግር እንመልከት፡፡ በሙሴ ጊዜ ፈርዖን እሰቅላችኋለሁ ያላቸው አስማተኞችን እንደሆነ ቁርአን ይነግረናል፡፡ ነገር ግን የቁርአኑ ሙሳ የመጽሐፍ ቅዱሱ ሙሴ ከሆነ እርሱ በነበረበት ዘመን የስቅለት ቅጣት ነበረ ወይ? የዚያን ጊዜው ፈርዖን ስለ ስቅላት ቅጣት ይህንን እንዴት ሊናገር ቻለ? 

ሙሴ እስራኤላውያንን እየመራ ከግብፅ እንዳወጣቸው እናውቃለን፡፡ ይህም 1446 ዓ.ቅ. ክርስቶስ አካባቢ ነው፡፡ እስራኤል በግብፅ ባርነት በነበሩበት ዘመን 18ኛውን ስርወ መንግስት በተመለከተ ያለው የግብፃውያን የጊዜ ቅደም ተከተል በትክክል ባይታወቅም እንኳ በቅርብ በተደረጉ ጥናቶች እንደተረጋገጠው እስራኤላውያን ከግብፅ ግዞት የወጡት በፈርዖን ስርወ መንግስት ውስጥ ከሳልሳዊ ታውትስ እና ከልጁ ዳግማዊ አሙኖቲፕ አገዛዝ በኋላ ነው፡፡ 

ይህን የታሪክ ማጣቀሻ መግለጥ ያስፈለገው በዚያን ወቅት ወንጀለኛ በስቅላት የሚቀጣበት ሁኔታ በፈርዖን ግዛት ታሪክ ውስጥ አልነበረምና ነው፡፡ ቁርአን ምን እያለ ነው ተብሎ ሲጠየቅ ‹አንክ› የተባለው አናቱ ላይ ቀለበት ያለው መስቀል በዚያን ዘመን የነበረ መሆኑን እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹አንክ› የአንገት ጌጥ እንጂ የመስቀያ መስቀል አይደለም፡፡ ፈርዖን ይህንን እንዳላደረገ መጽሐፍ ቅዱስም ይህንን እንዳላወራ ተረጋግጧል፡፡ ቁርዓን ለእውነተኝነቱ የጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ካልነገረን ከወዴት እንዳመጣው ሊጠየቅ ይገባዋል፡፡ 

የ14ኛው ክፍለ ዘመን ቅድመ ክርስቶስ ታሪክ እንዴት ተዛብቶ እንደቀረበ ተመልከቱ፡፡ በታሪክ ተመራማሪዎች ጥናት መሰረት እነዚህ የተዘበራረቁ ጽሑፎች ለህፃናት መጫወቻ ለማዝናናት የቀረቡ ነበሩ እንጂ ከመገለጥ በላይ ያሉ መገለጦች አይደሉም፡፡ የሰው የስነ ጽሑፍ ታሪክን ወደ መለኮታዊ ደረጃ ማላቅ ተገቢ አይደለም፡፡ 

በተጨማሪም በመርየም ምዕራፍ 26 ያለው የመርየም የመውለድ ጭንቅ ከወዴት የመጣ እንደሆነ እንመልከት ይህ ታሪክ በ2ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ነው፡፡ የታሪኩ ምንጭ የኢየሱስ የልጅነት ሕይወት ታሪክ ተብሎ የተዘጋጀ ነበር መጠሪውም “the last book of bible” century እንዲሁም Gosple of the infancy of Jesus Christ. 2nd ይባላል፡፡ ለማስታወስ የመርየም ምዕራፍ 26 ታሪክ መርየም ወዲያው በቅፅበት አረገዘች ኢሳን በሆዷ ይዛ ገለል አለች ምጥ መጣባት ዘንባባ ዛፍ ስር ሄደች ተጨንቃ በሞትኩ ስትል አይዞሽ ጌታሽ ከበታችሽ ወንዝ አድርጓል እንደተባለች ዛፉን ነቅንቂው ፍሬው ይረግፍልሻልና ብይም ጠጭ እንደተባለች ይናገራል፡፡ የዚህ ታሪክ መሠረቱ ቁርአን እንደሆነ ሙስሊሞች ዛሬ ቢናገሩም ምንጩ ግን ከዚህ በላይ የተጠቀሰው መጽሐፍ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን አይልም፡፡ 

ሊቃውንቱ የቁርአን ውበቱ ግጥማዊነቱ ነው ብለው ይነግሩናል፡፡ ነገር ግን Gunther Lulling የተባለው ሰው እንዳጠናው ይህ የግጥም መልእክት አጻጻፍ /በሲሪያክ/ የክርስቲያን ሲሪያክ ቋንቋ ግጥም እንደሆነ ተደርሶበታል፡፡ እሱ ወደ አረብኛ ተተርጉሞ እንደገባ ለማወቅ ተችሏል በእርግጥ ግጥሙ በትርጉሙ ሥራ ሥህተት ቢኖርበትም ከወደዱት ለቀደመው ታሪክና ጸሐፊው እውቅና መስጠትና ምሥጋና ማቅረብ ይገባቸዋል ብሏል፡፡ 

እኛ እንደምናምነው እውነት ፍፁም የሚሆነው አንፃራዊ አፍራሽ መረጃ ሳይኖርበት ብቻ ነው፡፡ ይህ እውነት መረጃ ለብዙዎቹ ብርቱ የምርምር መንገድ እንደሚከፍት መገመት ይቻላል፡፡ መጽሐፈ ቅዱስ ተበላሽቷል ተለውጧል ማለት ብቻ አያዋጣም የራስን ገመና መመርመር ያስፈልጋል፡፡ 

አል-ንህል ምዕራፍ 15 ተራራ የመሬት ችካል ወይም ማዕዘን እንደሆነ ያወራል፡፡ የኺማሊያ ተራራ ባለበት ህንድ አካባቢ በየዘመናቱ ከፍተኛ የመሬት ነውጥ ይከሰታል፡፡ ምክንያቱ ምን ይሆን? የማይገናኙ ነገሮችን በልማድ አይደረስባቸውም በሚል የተነገረው ይህ ክፍል ስህተትነቱ ከዘመናት በኋላ ታውቋል፡፡ የተራሮች አቀማመጥ ከመሬት ነውጥ ጋር በፍፁም ተያያዥነት የለውም፡፡ 

ሊላው ዲርሃም ስለተባለው ገንዘብ በዩሱፍ ምዕራፍ 2ዐ ዩሱፍ የተሸጠው ዲርሃም በተባለ ሳንቲም እንደሆነ ቁርአን ይናገራል፡፡ ነገር ግን በዘፍጥረት 7.28 ሃያ ሰቅል መሸጡን እንጂ በዲርሃም መሸጡን አይነግረንም፡፡ ዲርሃም ሳንቲም ሲሆን ሰቅል ደግሞ የክብደት መለኪያ ነው፡፡ ዲርሃም በ7ተኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ቅ.ክ. የተፈጠረ ቢሆንም በዩሴፍ ጊዜ ዲርሃም አልነበረም፡፡ ማለትም በ1,800 ቅድመ ክርስትና ዓመተ ዓለም ዩሴፍ በግብፅ አልነበረም፡፡ በ1,900-1,800 ቅድመ ክርስቶስ የባሪያ ዋጋ ሃያ ሰቅል እንደሆነ እዚያው መጽሐፍ ቅዱስን ሳንጠይቀው መልስ ሰጥቶናል፡፡

ቁርአን ትክክለኛው የዝውውር ገንዘብ የቱ እንደሆነ አላወቀም ወይም ዲርሃምን በሰቅል ምትክ ተጠቅሟል እንዳንል ሰቅል የክብደት መለኪያ በመሆኑ መጠኑም ሃያ ሰቅል አንድ ነጥብ ሁለት ኪሎ ግራም ብር ነው፡፡ ታዲያ ዲርሃም በመሐመድ ጊዜ የነበረ ነው ወይስ ለሰዎች እንዲገባ ተደርጎ ሲመነዘር የተፈጠረ ስህተት? በመሐመድ ጊዜም ዲርሃም ስራ ላይ አለመኖሩ መታወቅ አለበት፡፡ በመሐመድ ጊዜ የነበረው ድራሃባዝ የተባለ መገበያያ ነበር፡፡ ዲርሃምን የአረቢያ አካባቢዎች መጠቀም የጀመሩት ከ642 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ መሐመድ በትንቢት ሊመጣ ያለውን ተናግሯል እንቀበል ካላልን በስተቀር ይህ መጽሐፍ ከመሐመድ በኋላ ተደራጅቶ የተፃፈ በመሆኑ ስህተት ገጥሞታል እንላለን፡፡ 

ቁርአን ከወዴት መጣ? በ20ኛውና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ የተጀመሩ የክርክር ንግግሮች ምስጋና ይግባቸውና ቁርአን በ7ተኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረ እንዳይደለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እስልምና ለመዳበር ከ200-300 ዓመታትን እንደፈጀበት ታውቋል፡፡ ምናልባትም በ22 ዓመታት ለአንድ ሰው የተገለጠ ላይሆንም ይችላል፡፡ ሐዲስ የተባለው መጽሐፍም የተጻፈው መሐመድ ከሞተ ከ200 ዓመታት በኋላ በሰዎች ትዝታ ውስጥ የነበረው መልእክት ተሰባስቦ ነው፡፡ ነገር ግን በአፈ ታሪክ የተነገረውን እየተቀባበሉ ያቆዩትን መልእክት እንደ ስህተት አልባ ማረጋገጫ መጠቀም ጥያቄ ውስጥ ለመውደቁ ሌላው ምክንያት ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ሲሰበሰብ ያልነበሩ ሰዎች የሰሙትን ለጸሐፊዎች አስተላልፈዋልና፡፡ መቼም ከመሐመድ ልደት ወዲህ 200 ዓመታትን በሕይወት የኖረ ሰው የለም፡፡ ደግሞም አልተገኘም፡፡ 

ለምሳሌ ቡኸሪ (ከቡኸሪ) ታኻባሪ (ከበረስተን) ማለትም ኢራንና ኢራቅ ናቸው እንጂ የመዲናና የመካ አይደሉም እነዚህ ቦታዎች እንግዲህ ትክክለኛ የሰዎቹን ማንነት በአንድም በሌላ የሚጠቁሙ ይመስለናል፡፡ ኢራንና ኢራቅ ደግሞ ከመካና መዲና በቅርበት የሌሉ ናቸው፡፡ ታዲያ ከሐዲስ ዘጋቢዎች የላቀ ተቀባይነት ያገኘው ቡኸሪና የቁርአን ትስስር እንዴት ተፈጠረ? በመምርኮ ወይስ በመገለጥ? በአካል ወይስ በመንፈስ? ሐዲስ የተጻፈው ከቁርአን በኋላ 200 ዓመታት መካከል ከሆነና ደግሞም ከመሐመድ ንግግር በቀጥታ የተቀዳ ካልሆነ ስህተት አይኖርበትም ብሎ መሟገት እየዋለ እያደረ ማሳፈሩ አይቀርም፡፡ በዘመነ መሐመድ ኩፋ ባግዳድ ምንም መስኪድ እንኳን አልነበረበትም፡፡

በተያያዥነት የስግደት አቅጣጫ ቂብላን በሚመለከት በተደረገው ጥናት ከ622-624 የስግደት አቅጣጫ ወደ መካ እንደተደረገ እስላም ያስተምራል ነገር ግን በ670-680 ኡማያድ መስጊድ አቅጣጫውን ወደ እስራኤል አድርጎ እንደተሰራ ለማግኘት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ወሰት መስጊድ፣ ኩፋ መስጊድ፣ ፉስታት መስጊድ (ከካይሮ ውጪ የሚገኝ የስግደት አቅጣጫቸው የተለወጠው ዘግይቶ ነው፡፡ 

ኢብኒ አልማሊክ የተባለው በ691 ዓመተ ምህረት ታላቁ የአረብ የተሃድሶ መሪ ይህንን ታላቅ ህንፃ እንደሰራና አረባዊነትን እንደመሰረተ ታውቋል፡፡ ሶስተኛውን ቅዱስ መስጊድ አል አክሳን ባለ 8 ማዕዘን ህንፃ አድርጎ በዚያው ዘመን ሰርቶታል፡፡ ይህ መስጊድ በሱራ አል-ኢስራዕ 1 እና በአል-በቀራህ 47 ቂብላ የለውም፡፡ መስጂደል አል አቅሳ ቂብላው ራስ መስጊዱ ነበር ወይ? ይህ መስጊድ 11 ጊዜ እየፈረሰ የተሰራ ነው ጥናቱም ገና አላለቀም፡፡ በ624 ይህ መስጊድ በዚህ ስፍራ አልነበረም፡፡ በ641 እየሩሳሌም በሙስሊሞች አልተያዘችም፡፡ በአል-ኢስራ ምዕራፍ 1 መሐመድ ከሰማይ ሲመለስ ስግደትን ለማስቀነስ እንደቻለና ለዚህም መታሰቢያ ተመስርቷል የሚባለው ይህ አል አቅሳ መስጊድ በውስጡ ስለዚህ ጉዳይ የተጻፈ መረጃ አልተገኘበትም ደግሞም የለበትም፡፡ እንዲያውም አላህ አንድ እንደሆነ የሚያትቱ መልእክቶች ብቻ ናቸው ያሉት፡፡ ስለመሐመድ የሌሊት ጉዞ ምንም የተጻፈ መረጃ በመስጊዱ ከሌለ፣ ለምን ይሆን? ተብሎ መጠየቅ አለበት፡፡ እንዲያውም በመስጊዱ ውስጥ ክርስቲያኖችን የሚቃወሙ በርካታ ጥቅሶች ናቸው የተገኙት፡፡ ህንፃው ዛሬም ትልቅ ምስክር ነው፡፡ 

በአጠቃላይ ሙስሊሞች አዳም፣ አብርሃም በከዓባ እንደነበሩ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች በዚያ ስፍራ እንደነበሩ ምንም መረጃ አልተገኘም፡፡ የእስልምናው ትልልቅ ከተሞች ከታሪክ አንፃር የሚነግሩን ምንም መረጃ የለም ሸኸዳን እንኳን (ለኢላ ኢለላ መሐመድ ረሱሉላ) የሚለው መልእክት የተገኘው በ691 ዱም ኦፍ ዘ ሮክ (መስጊደ አልአቅሳ) ላይ ነው፡፡ ነገሩ በአንድ ቀን የተፈጠረ ይመስላል መሐመድ ከሞተ ከ60 ዓመት አካባቢ በኋላ እንዴት ነው ይህ ሊሆን የቻለው? ቁርአን ለኢስላም መሰረት ተብሏልና መስራቹ ካለፈ አዲስ ቀመር ለምን ተጨመረበት? 

 በሌላ አንtAር የኢብን አብዱልድ ኪታብ አልማሳኸፍ (ገፅ 23) ዘይድ ኢብን ሀበት መዲና፣ አብደላ ኢብን መስኡድ ባስራ፣ አቡ ሙሳ እና ኡባያ ኢብን ካአብ የተባሉት ቁርአኖች የተጻፉት መቼ ነው? መልሱን ለአማኞቹ እንተውላቸው፡፡ 

የቁርዓን መጻሕፍት 10,000 ልዩነቶች አሉዋቸው፡፡ ሙስሊሞች ይህንን ያውቃሉ ወይስ አያውቁም? እነሱ የቁርአን ትክክለኛነቱን እና አልተለወጥም መባሉን እንጂ ሌላ አያውቁም፡፡ ከላይ የተጠቀሱት አራቱ የቁርአን ዓይነቶች እንዴት ይመለከቷቸዋል? ያውም እርስ በእርስ የማይስማሙ ሆነው፡፡ ከአራቱ ሁለቱ ትርፍ ምዕራፎች አሉዋቸው፡፡ ሁለቱ 116 ምዕራፍ ሲኖራቸው ሌሎቹ 114 ናቸው፡፡ እንዴት ልዩነት ሊፈጠር ቻለ? ሦስተኛው ከሊፋ ኡስማን አልቡካሪ መጽሐፍ ስድስት የሐዲስ ቁጥር 509 እና 510 ታሪኩን መመልከት ይቻላል፡፡ ሰኢድ ኢብን ታቢት በድጋሚ ስለምን ጻፈው? 

ለውጡ ያስፈለገው እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን አናባቢ ስላልነበረ ለማስተካከል ተብሎ ነው ወይም እንደዚህ እንደሆነ ይጠረጠራል፡፡ ኡስማን የሚስማማውን በመምረጥ ሌላውን እንዳቃጠለ ደግሞ ይታወቃል፡፡ ስለምን ማቃጠል አስፈለገ አልቡካሪ ከመሐመድ ሞት 20 ዓመት በኋላ የተመረጠና የተወሰደ የታመነው ዶክመንት ነው፡፡ ኢብን ዳውድ የተወሰኑ የቁርአን ክፍሎች ጠፍተዋል ብሏል፡፡ አልሰኢዲ የተወሰነ የቁርአን ክፍል ተሰውሯል ይላል፡፡ በሰሂህ ሙስሊም ደግሞ ከሐዲስ የተወሰነ የቁርአን ክፍል ተረስቷል ይላል ሳሂህና አልቡካሪ ደግሞ ተሰርዟል ይላሉ፡፡ ሌሎችም ተረስተዋል እነዚህ ቀዳሚና ታማኝ የእስልምና ሊቃውንት የተናገሩት ተጽፎ እያለ አሁን ያለው ቁርአን እና ሐዲስ ምንም ስህተት የሌለው ተብሎ ለምን ይጠቀሳል? ኢብን ማሊክ ተለውጧል፡፡ ኢብን አቢ ዳውድ ተሻሽሏል፣ ተሰውሯል፣ ተረስቷል፣ ተሰርዟል እያሉን የቱን እንመን? በትክክልና በሙሉ የተዘጋጀ መጽሐፍ ከሆነ ይህ የሊቃውንቱ ንግግር ምን ይባላል ሙስሊሙ ይህንን መረጃ ማወቅ አለበት፡፡ ቁርአን የአንድ ሰው ስራ አይደለም፡፡ በመሐመድ ጊዜ ብቻ የነበረ መጽሐፍ ከሆነ ይህ የሊቃውንቱ ንግግር ምን ይባላል? ሙስሊሙ ይህንን መረጃ ማወቅ አለበት፡፡ ቁርአን የአንድ ሰው ስራ አይደለም፡፡ በመሐመድም ጊዜ ብቻ የነበረ መጽሐፍ አይደለም፡፡ 

አራቱ ጥንታዊ መጽሐፍትስ የት አሉ? የመዲና፣ የባስራ የደማስቆስ?  ቶፕ ካፒ ማንስክራፕት፣ የሃጅራ ማንስክሪፕ፣ የዑመያድ ማንስክሪፕ እንዲሁም የአባሲድ ኮይንስ ሂስትሪ (ኩፋ) የት ነው ያሉት?

ወደ ክፍል አንድ ይመለሱ

 

Critique of the Qur'an: internal and External critiques, Jay Smith

 ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ