አጫጭር ዜናዎች 

በግብፅ ክርስትያኖች ሁሉ እንዲገደሉ የሚደረገው ቅስቀሳ!
የልብ ልብ የተሰማቸው እስላሚስቶች በግብፅ ያሉ ክርስቲያኖች ይገደሉ አሉ!!

 

Barnabas Fund  29 August, 2012.


ፓኪስታን

23 ነሃሴ 2004 (Wed  29 Aug 2012) እትሙ የግብፅ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሞርሲ ስልጣኑን እያረጋገጠ መሆኑንና  እስላሚስቶች እንዴት የልብ ልብ እንደተሰማቸው እንደሚከተለው ያስነብበናል።

ክርስቲያኖች ይገደሉ ጥሪ፣ ተቃወሚዎችን በእንጨት ላይ መሰቀል ዘገባ፣ የዜና አገልግሎት ሃያሲያንን  ፀጥ ማሰኘት፣ የስልጣን ተቀናቃኞችን ማስወገድ አዲሲቱ ግብፅ በእስላሚስቱ ፕሬዜዳንት ይህን ትመስላለች። ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በግብፅ የሚያስደነግጡ ሁኔታዎች  ተከስተዋል። ፕሬዚዳንት መሐመድ ሞርሲ ስልጣኑን በሃይል እያረጋገጠ ሲሆን  በፊት በቁጥጥር ስር የነበሩ  እስላሚስቶችን የልብ ልብ እንዲሰማቸው አድርጎአል።   በራሪ ወረቀቶች ከጂሃዲ ድርጅቶች  “ለሁሉም ለወንድም ለሴትም» የተበተነ ጥሪ «በሁሉም የግብፅ ክልሎች በሚገኙ ክርስቲያኖች፤ የመስቀል አሽከሮችና በአላህ ጠላቶች ላይ ግድያ ወይም አካል ጉዳት አደርሱ» የሚል ነበር።  ለማንም ተባባሪ «የአላህን መብት በጠላቶች ላይ ላስከበረ» የገንዘብ ሽልማት  እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል። እነዚህ በራሪ ወረቀቶች ከታዩ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ርፋት እስክንዳር (Refaat Eskander) የተባለ ክርስቲያን የሱቅ ባለቤት በእሱዩት (Assuit) ተገድሏል። ከገዳዮቹ አንዱ ከግድያው ቦታ ሲሸሽ ታይቷል የለበሰውም የሳላፊዎችን ልብስ ነበር።  በተጨማሪም  ክርስቲያኖች እንደሚደበደቡ፣ የንግድ ድርጅቶቻቸው እንደሚቃጠሉና  ንብረቶቻቸው እንደሚዘረፉ ተዘግቧአል።

ተቃዋሚዎች ተሰቀሉ

የሙስሊም ወንድማማችነት እና የፕሬዚዳንት መሐመድ ሞርሲ እስላሚስት አጀንዳ ተቃሚዎች በሃይል እየታፈኑ ነው። ብዙ የአረብ ድረ ገፆች እንደዘገቡት በዚህ ወር መጀመሪያ የሙስሊም ወንድማማችነት ደጋፊዎች ተቃዋሚዎችን ራቁታቸውን በዛፍ ላይ ሰቅለዋል። ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ሲሞቱ ብዙዋቹ ቆስለዋል።  ይህን የመሰለ የሃይል እርምጃ በአገሪቱ ከፍተኛው የእስልምና ስልጣን ያለው ድርጅት በአል አዝሃር (Al-Azhar) የተፈቀደ ብቻ ሳይሆን የታዘዘ ነው። ሼክ ሃሺም እስላም የአል አዝሃር ፋትዋ አባል 14 Aug እንዳለው «ለ24 Aug የታቀደውን ፀረ-ሙስሊም ወንድማማችነት ሰልፍ መቃወም የሃይማኖት ግዴታ ነው» ብሏል። ቀጥሎም ተቃወሟቸው፣ ከመቱአችሁ ምቱአቸው፣ ከገደሉአችሁ በገነት ናችሁ፣ ከገደላችኋቸው የደም ካሳ የለም።

የዜና አውታሮች ፀጥ ተደርገዋል

ወንድማማችነትን እና ወይም ሞርሲን የሚተቹ  የዜና አውታሮችና ባለሙያዎች ድብደባ፣ ሳንሱር  ብሎም መታገድ ደርሶባቸዋል። በ 8 Aug የወንድማማችነት ደጋፊዎች ጥርቅም የዮም 7 የግል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ካህሌድ ሳላህን ደብድበዋል፤ የ 6-October ድርጅት ንብረትን አጥቅተዋል፤  የቴቪ ዜና አንባቢውን ዩሲፍ አል ሃሳኒ ወደ ማሰራጪያው ጣቢያ ህንፃ እንዳይገባ ከልክለዋል። ምንም እንኳን ሞርሲ «የትኛውም ጣቢያ ወይም የዜና አውታር በእኔ ዘመን አይዘጋም» ሲል ቀድም  ብሎ ቃል ቢገባም  ኦካሻ (Okasha)  እና አል ፋሪን (Al Fareen) የቲቪ መስመሮች ከአየር ላይ ተነስተዋል።   ንብረትነቱ የክርስቲያን ግለሰብ የሆነ የግል ጋዜጣ አል ዱስቱር  (Al-Dustour)  ሞርሲን ተሳድቧል፣ በተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች አለመረጋጋትን አባብሷል  በማለት ህትመቱን እንዲወረስ የግብፅ ፍርድ ቤት ወስኖአል። በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ እውቅ ጋዜጦች ብዛት ያላቸው አዳዲስ ዋና አዘጋጆችን ወንድማማችነት አስቀሞጦአል።

ተፏካካሪዎች ተገለሉ

ሞርሲ የስልጣን ትንቅንቅ ከሠራዊቱ ጋር ካደረገ በኋላ በ 12 Aug በወሰደው ሁለት ፈጣን እርምጃዎች  ሙሉ የህጋዊና የአስፈጻሚ  ስልጣን ተቀዳጅቶአል። ሁለት ትላላቅ መሪ ጄኔራሎችን ከስልጣናቸው አስወግዶአል። እነርሱም ፊልድ ማርሻል መሐመድ ታንታዊ  መከላከያ ሚኒስቴርና ፕሬዚዳንት ሙባሪክ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ አገሪቱን ይመራ የነበረ ሲሆን ሌላው ደግሞ ሌ/ጄኔራል ሳሚ አናን የጦር ሃይሎች ኤታማጆር ሹም ነው። ሠራዊቱ በሰኔ ያወጣውን የፕሬዚዳንቱን ስልጣን የሚገድበውን  አዋጅ ሞርሲ  ውድቅ አድርጎታል።  ለአገሪቱ ክርስቲያኖች እነዚህ ለውጦች እጅግ የሚያሳስቡ ናቸው።  ሠራዊቱ በአገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ እንዳይካይሄድ ይቃወም ነበር።  ዳሩ ግን የሠራዊቱ ስልጣን  በከፍተኛ ደረጃ ስለተቀነሰ ሞርሲ ያለምንም ተቀናቃኝ የእስላሚስቱን አጀንዳ ያስፈጽማል።

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በግብፅ ውስጥ በግልጥ የምናየው ሁሉ ነገር ሁለት ዓይነት ጥያቄዎችን በአንባቢዎች ዘንድ ማስነሳት ይኖርበታል፡፡ አንደኛው፡ ከእስልምና እምነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡  የክርስትያኖችንና የሌሎችን ሕዝቦች የመኖር መብት እስልምና የሚረግጠው በሰላም የሚኖሩትን ክርስትያኖች የሚገድለው ለምንድነው? በአሁኑ ጊዜ በግብፅም ሆነ በሌላው ሙስሊማዊ አገር የምናያቸው ክስተቶች፣ ብጥብጦች፣ የየዕለቱ ግድያዎች፣ እራስንና ሌላውን የማጥፋት እርምጃዎች ሁሉ ለሙስሊሞች የሚሰጡት መልአክት ምንድነው በእርግጥ የእስልምና እምነት መርሆ የሰው ልጅ ፈጣሪ ከሆነው ከእግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው እምነት ነው በማለት ለመናገር ያስችላልን? ሁለተኛው፡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች እስልምናን በብዛት ቢቀበሉና በሙስሊም መሪዎች ቢገዙ አሁን በግብፅና በሌሎችአገሮች ውስጥ ከምናየው የተሻለ ነገር፣ ማለትም የጋራ ዕድገት እኩልነት እና ሁሉም ሰው በሰው ልጅነቱ በእኩልነት የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግበት ሙስሊምም ክርስትያንም በአንድነት በፍቅር እየተያዩ የምትኖርባት አገር ሆና ትቀጥላለችን?

የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆች ጥያቄዎቹን ለአንባቢዎች አዕምሮ ያቀርቡታል፡፡ ሆኖም ግን ዋና ዓላማችን ለሰው ልጆች ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን መልእክት ለሙስሊሞችም በፍቅር ማድረስ ነው፡፡ የሰዎች ልጆች ያለ እግዚአብሔር የሚኖሩት ኑሮ በራሳቸውም በሌሎችም ላይ ችግር የሚያመጣ መሆኑን ከእግዚአብሔር ቃል ላይ በመግለጥ፤ ከዚህ ችግር ውስጥ የሚዳንበትን እግዚአብሔራዊ መፍትሄ እንጠቁማለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው እውነት ለዚህ የሰው ልጅ ጥልቅ ችግር መፍትሄውን የሰጠው ሕያው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ይህም መፍትሔ ወደ ሰዎች የመጣው በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ሞት ብቻ ነው፡፡ ሰዎች ከኃጢአታቸው ንስሐ በመግባታ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለኃጢአታቸው የዘላለም ቅጣት የከፈለውን ዘላለማዊ ዋጋ አምነው በእርሱ ስራ በኩል እግዚአብሔር ፊት ቢቀርቡ ይቅርታንና አዲስ ሕይወትን ይቀበላሉ፡፡ የእኛ ፀሎታችንም ዓላማችንም ብዙ ሙስሊሞች ይህንን እውነታ እንዲያዩልን ነው፡፡ እግዚአብሔር በፀጋውና በምህረቱ ይርዳችሁ፡፡

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ