አጫጭር ዜናዎች 

ጥቁር ሙስሊሞችና የእስላም መንግስት
በ Brad Bromling, D.Min
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

አሜሪካዊው Louis Farrakhan በሕዝብ ትኩረት ውስጥ ከገባበት 1984ቹ አካባቢ ጊዜ ጀምሮ አከራካሪ ሰው ነበር፡፡ የአንዳንዶችን ልብ አስደስቷል፣ የብዙዎችን የብርሃን ሕይወት አስፈሪ አድርጓል፣ ሌሎችን ደግሞ አሰናክሏል፡፡ የአፍሪካን-አሜሪካንን ማህበረሰብ “በሚሊየን ሰው ሰላማዊ ሰልፍ” በዋሽንግተን ዲሲ እንዲሳተፉ ስጋብዝ 400 000 ሰዎች ምላሽ ሰጥተው ነበር ይህም ቁጥር ማርቲን ሉተር ኪንግ በ1963 ከጠራው ቁጥር እጥፍ ነበር፡፡ የእርሱ ጥር እንደ ዶ/ር ኪንግ አልነበረም ምክንያቱም የተባለው ሁሉ ነገር ያተኮረው እና የተሰጠው ለአላህ ብቻ ነበርና፡፡

ነገር ግን ፋራካን ከጠቆመው በላይ ሌሎች ጥቂት ሰዎች በአሜሪካ ውስጥ የእስልምናን መኖር አስገንዝበዋል፡፡ ብዙዎች በእርግጥ የማያውቁት የነበረው ነገር ፋራካን እስልምናን ወክሎ እንዳልነበረ ነው፡፡ እርሱ የእስላም መንግስት እንቅስቃሴ መሪ ነበር፣ ያ እንቅስቃሴ በተለየ መልኩ የተፈጠረው በአሜሪካ ብቻ ነበር ስረ መሰረቱም በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መክፈቻ ላይ ነው ይህንን ለማንበብ የሚከተለውን መረጃ ተመልከቱ (Bijlefeld, 1993; Gudel and Duckworth, 1993; Ahlstrom, 1972; Morey, 1992).

በ1930 በዲትሮይት አሜሪካ የልብስ ነጋዴ የነበረውና Wallace D. Fard (a.k.a. Wali Farad Muhammad) የሚባለው በጥቁሮች መካከል እስላማዊ ጣዕም ያለውን መልክእር መስበክ ጀመረ፡፡ ፋርድ እራሱ የ“Noble Prophet Ali Drew,” ተከታይ ነበር፡፡ ያ ነቢይ ይባል የነበረው ሰውም የMoorish Science Temple of America. ዋና መስራች ነበር፡፡ የድሪው መልእክት የክርስትያን መርሆዎች፣ የእስላማዊ ሐሳቦች እና የጥቁር ብሄረተኝነት ሐሳቦች ድብልቅ ነበር በመሆኑም ለተጨቆኑት ማህበረ ሰቦች ተስፋን አቅርቦላቸዋል፡፡ ድሪው በ1929 ከተገደለ በኋላ ፋርድ ከመካ ጋር ግንኙነት እንዳለው መናገር ጀመረ፣ ወዲያውም ጥቁር አሜሪካውያንን ክርስትናን(የነጮች ሃይማኖትን) እንዲክዱና የእስልምና ሃሳቦችን እንዲቀበሉ መጥራት ጀመረ፡፡ በዲትሮይት ውስጥም የእስልምና ቤተመቅደስን ከፈተ ከዚያም በ1934 8000 የሚያክሉ ተከታዮች ነበረው፡፡ ፋርድ በሚስጢር ከጠፋ በኋላ በ1934 የእርሱ በጣም ዝነኛ ደቀመዝሙሩ ኤላይጃ መሐመድ (ሲወለድ ኤላይጃ ፑል ይባል የነበረው) የእርሱን እንቅስቃሴ ወደ ፊት አራመደው፡፡

ኤላይጃ መሐመድ የተናገረው ነገር አላህ በፋርድ አካል ውስጥ ተገልጦ እንደነበርና እርሱም እራሱ የአላህ ነቢይ እንደነበረ ነው፡፡ ነጮች ሰዎች ሰይጣኖች እንደሆኑና ከእርሱ ጋር መደባለቅ ትክክል እንዳይደለ ይሰብክ ነበር፡፡ በእርሱም አመለካከት ጥቁር ሰዎች በነጮች ላይ በአርማጌዶን ጦርነት ላይ የመጨረሻውን ድል እንደሚቀዳጁ ነበር፡፡ እርሱም ድሃዎችና በስደት ላይ ለነበሩት ጥቁር ሕዝቦች የመብትሰ ስሜት እንዲኖራቸው ሐሳቡን ያሰርፅ ነበር፡፡ ጥቆች የነጮች እኩሎች ብቻ ሳይሆኑ አንድ ቀን ዓለምን ይገዛሉ ይል ነበር፡፡

በ1947 ላይ የወንጀል እስረኛ የነበረው Malcolm X (born Malcolm Little) የኤላይጃ መሐመድ መልእክትን ሰማና አመነበት፣ ከእስር ቤትም በ1952 ሲለቀቅ የአሜሪካ ጥቁር ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ ተደባለቀ፡፡ መሐመድን በተመለከተ የተምታታ ሁኔታ ውስጥ እስከ ገባበት እስከ 1963 ድረስም የቡድኑ ዋና ተናጋሪ አገልጋይ ሆኖ ነበር፡፡ ቆይቶም ወደ መካ ከተጓዘ በኋላ Malcolm X ወደ ኦርቶዶክስ እስላምነት ተቀየረና የዘረኝነት ጥላቻ ውስጥ መሳተፉን አቆመ፡፡ ከአስራ አንድ ወራት በኋላም ተገደለ፡፡

መሐመድ በ1975 በሞተበት ጊዜ በልጁ Wallace Deen, ተተካ፣ ዋላስ ዲን በጥቁር ሙስሊሞችና በኦርቶዶክስ እስላም መካከል አንድነት እንዲፈጠር ጥረትን አደረገ፡፡ ይህ አካሄድ ግን በፋራካን ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም፣ እርሱም በኤላይጃ መሐመድ ትምህርት መኖርን መርጦ ነበር፡፡ ስለዚህም በ1977 ፋራካን ከጥቁር ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ተለይቶ ወጣ፣ ወደ አስተማሪው ትምህርት ተመለሰና “Nation of Islam” የሚለውን ተግንጣይ ቡድን መሰረተ ይህ ስም በኤላይጃ መሐመድ አገልግሎት ላይ የዋለው ስም ነበር፡፡

ከፋራካን ውጭ ዋላስ ዲን መሐመድ ጥቁር ሙስሊሞችን ከኦርቶዶክስ እስላሞች ጋር ወደ ሙሉ አንድነት አመጣቸው፡፡ ይህ ቡድን ከእስላም መንግስት ቡድን ጋር መምታታት የለበትም ምክንያቱም የእስላም መንግስት አሁንም በዓለም አቀፍ ሙስሊሞች ዘንድ እንደ ሐሰት ትምህርት ቡድን የሚወሰድ ነውና፡፡

የኤላይጃ መሐመድ አንዳንድ የሚረብሹ አመለካከቶችን በተመለከተ በእስላም መንግስት ጽሑፍ ውስጥ በ Sidney Ahlstrohm: በሚገባ በጥቅልል እንደሚከተለው ቀርቧል፡

“የእነርሱ የመጨረሻው ዘመን ትምህርት የሚለው እግዚአብሔር ወደ ምድር እንደመጣ፤ ከዚህ ሕይወት በኋላ ምንም  ዘላለማዊ የሚባል ሕይወት እንደሌለ፣ መንግስተ ሰማይና ሲዖል ሁለቱ ተቃራኒ የዚህ ምድር ሕይወት ሁኔታዎች ብቻ እንደሆኑ፣ ከዚህ በኋላ (በ 2000 ዓም የሚጀምረው) የዚህ አሁን የያዝነው የነጮች “ምትሃት” ስልጣኔ፣ ክርስትናን እምነት ጨምሮ ማብቂያ እንደሆነ ነው፡፡ ከዚያም የሚቀጥለው የጥቁር ሕዝቦች ነፃ መውጣትና የእነርሱ የከበረ ግዛት በዓለም ሁሉ ላይ መሆኑ ነው” (Sidney Ahlstrohm 1972, p. 1068).

የሚሊየን ሰው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በፋራካን እንደቀረበው የእስላም መንግስት መልክእት ይመስል የነበረው የማህራዊ ደህንነትና እርቅ ነበር፣ እርሱም ለጥቁር ማህበረሰብ የቀረበ ጥሪ ነበር ለስነ ምግባራዊና ለስነ ስርዓታዊ የላቀ ደረጃ ላይ ሆኖ መገኘት እንዲታገሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ፋራካን የተሰበሰቡትን ሰዎች አደንዛዥ ዕፅ መውሰድን እንዲያቆሙ፣ ሴትኛ አዳሪነትን እንዲተው፣ ዓመፅን እንዲያቆሙ፣ እራሳቸውን “በመንፈሳዊነት፣ በስነምግባር በዕውቀት፣ በማህበረሰብ በፖለቲካ በኢኮኖሚ” ለማሻሻል እንዲጥሩ ጥሪ አቅርቧል (1995)፡፡ እነዚህ ዘረኝነት ያለፉ ትልልቅ ድምፅ ያላቸው ስጋቶች ናቸው፡፡ የወንጀለኝነት ብዛት ቢቀንስ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምርታማነት ቢኖር እንዲሁም በሕይወት ጥሩነት ላይ አጠቃላይ መሻሻል ለአፍሪካን አሜሪካውያን ቢሆን ሁሉም ሰዎች የሚደሰቱበት ምክንያት ይኖር ነበር፡፡

የእስላም መንግስት ችግር ይሁን እንጂ ሁለት አቀፍ ነው፡ ሀ. የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አይደለም፤ ለ. በጣም ያተኮረው በነጮች የበላይነት ስጋት ላይ ነው፡፡ በዚያ የሚሊየን ሰው ሰላማዊ ሰልፍ ንግግር ላይ ፋራካን ያቀረበው መከራከሪያ ዩናይትድ ስቴት አሜሪካ መሰረቷ የበሰበሰ መሆኑን ነው ምክንያቱም የተመሰረተችው በነጮች የበላይነት ላይ መሆኑ ነው፡፡ እርሱም ለምሳሌ የተናገረው ነገር፡

“የአሜሪካ መንግስት ሕገ መንግስት ማህተም የመስራቾቹን አባቶች አስተሳሰብ የሚያንፀባርቅ ነው፣ ማለትም ይህ የነጮች አገርና ለነጮች ሕዝቦች የታሰበች አገር ነበረች፡፡ የአሜሪካ መጀመሪያ ሕዝቦች (ቀይ ህንዶች የሚባሉት) ጥቆሮች፣ ሌሎቹ ሁሉ ነጮች ያልሆኑት የሸክም ተሸካሚዎች እንዲሆኑ ነው ለእነርሱ እውነተኛ ዜጋዎች ለሚሏቸው” (1995፡፡)

በግልፅ ማንም ሰው በመጠነኛም የአሜሪካን ታሪክ መረዳት እኳን ሰዎች በማህበረ ሰቡ ውስጥ ካላቸው የአናሳ ቦታ የተነሳ የሚኖራቸውን የንዴት ስሜትና ብስጭት ማንም ሰው ሊረዳው ይችላል፡፡ ትምክህት አደገኛና የሚያሰቃይ ነገር ነው፡፡ የትምክህት ውጤቶች አልጠፉም፣ እርሱ ያደረሳቸው ቁስሎች አሁንም በጣም ትኩስ ሆነው በብዙ ቦታዎች ላይ እንዲሁም በብዙዎች ሕይወት ውስጥ ይታያሉ፡፡ የእነዚህ ችግሮች መልሶች ግን በቁርአን ውስጥ አይገኙም ወይንም በኤላይጃ መሐመድ ትምህርቶች ውስጥ በፍፁም የሉም፡፡ Cornel West በትክክል እንዳለው፡

“የአንድ ሰው ዓይን መሆን ያለበት በሚያስከትለው ዋጋ ላይ እንጂ በሚጨቁነው ሰው ላይ መሆን የለበትም፡፡ በአጭሩ የኤላይጃ መሐመድ ዕቅድ ወይንም ፕሮጀክት የተያዘው በበላይነት ጨዋታ ላይ ነው - ይህም ጨዋታ እርሱ በሚቃወመው በነጮች የበላይነት ዘረኝነት ላይ ሲሆን እርሱም በእራሱ የጥቆሮች የበላይነት ትምህርት ውስጥ ተኮርጆ ይገኛል፡፡” (1993፣ ገፅ 100)፡፡

በዘረኝነት ጥላቻ እየተፍረከረከች ላለችው ለዚች ዓለም ብቸኛው ተስፋ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፣ መፍትሔው፤ ጥቁር ኢየሱስ፣ ነጭ ኢየሱስ ማለት ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱሱ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ እርሱም እንደ ሁላችንም ሁሉ የሰው ልጅ ነው፣ ነገር ግን ከዚህ ውጭ እርሱ የእግዚአብሔርም ልጅ ነው፡፡ እርሱ ለሰዎች ልጆች በፈቃዱ እረሱን በመስጠት እና መስዋዕት በመሆን በሁላችንም መካከል ያለውን የጥል ግድግዳ በእራሱ አፍርሶታል፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በተለያዩ አገራት ታሪክ ውስጥ በዘር አማካኝነት የታየው ጭቆናና መከራ እጅግ በጣም ዘግናኝ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ያለው ጽሑፍ በአሜሪካ ውስጥ ስለነበረው የነጮች የበላይነትና በየጊዜው በጥቁሮች ስለተደረጉት መራራ ትግሎች ያስታውሰንና በተለይም እስልምና ከጥቁሮች ጋር እንዴት ተቆራኝቶ እንደነበረ ይጠቁመናል፡፡

ይሁን እንጂ የዘረኝነትን ጭቆና ቀንበር ሰብሮ የሚጥልና ሰዎች ነጭና ጥቁር ሳይባሉ ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚያደርግ እንቅስቃሴም ሆነ ሰው አመጣሽ ሃይማኖት በዓለም ላይ እስከ አሁን ድረስ አልታየም አይኖርምም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ግልፅ ነው፣ የተደረጉት ጥረቶች ሁሉ፣ ሁሉም በሰዎች የተዘጋጁና ከሰው የኃጢአተኝነት ልብ ውስጥ የወጡ እራስ ወዳድነት፣ ትምክህት እና ትዕቢት፣ ክፋት ጥላቻና ምቀኝነት ዘረኝነት ሁሉ የሞላባቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ነገሩ በዚህ ብቻ አያበቃም ሰዎች ዛሬ የተቃወሙትንና የነቀፉትን ነገር እነርሱም እራሳቸው ቦታውን ሲያገኙ ስለሚያደርጉት ነው፡፡ የኤላይጃ መሐመድ አሜሪካዊ እንቅስቃሴ ጥቁር ሙስሊሞች ኣሜሪካንን ተቆጣጥረው ነጮችን መግዛትና የጥቁሮችን የበላይነት ማረጋገጥ እስከ ሆነ ድረስ ከነጮቹ ዘረኝነት ልዩ ያደረገው ምን ነገር አለው?

መፍትሔው ምንድነው? መፍትሔው ሁሉን የሚያውቀው እግዚአብሔር የሰራውና ያቀደው የሰው ስራ የሌለበት ከራሱ የመነጨው እምነት ብቻ ነው፡፡ እርሱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግልፅ በሆነ መንገድ ቀርቧል፡፡

እግዚአብሔር ባዘጋጀው በዚያ መንገድ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡ በመጀመሪያ የሚያገኙት ነገር አዲስ ልብና የኃጢአት ይቅርታ ነው፡፡ የተለወጠው አዲሱ ልብ ወዲያውኑ ከዘረኝነት የፀዳ፣ ከትምክህት የራቀ፣ ትህትና ያለው ለሰው ልጅ ሁሉ እኩል አመለካከት የሞላበት በመሆን በትክክለኛው መንገድ ያለማዳላት ለሰዎች ሁሉ እኩል የሚያስብ ይሆናል፡፡

ይህ ልብ ከእግዚአብሔር ብቻ የሚገኝ፣ ዘላለማዊ ተስፋ፣ እውነተኛ ሰላምና ደስታ የሞላበት ነው፡፡ ይህንን አዲስ ልብ ለማግኘት ሰዎች ሁሉ መጓጓትና መናፈቅ አለባቸው፡፡ አዲስ ልብ እንዲኖራችሁ የምትፈልጉ ከሆነ በጣም ሳይዘገይባችሁ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀምሩ ከዚያም መዝሙረ ዳዊት (51).10 ላይ ዳዊት እንደፀለየው፣ በእምነት በእግዚአብሔር ፊት በመቅረብ ከልባችሁ አዲስ ልብ ፍጠርልኝ በማለት እግዚአብሔርን በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ለምኑት እርሱም ይሰጣችኋል፣ እውነተኛ ደስታንና ሰላምንም ታገኛላችሁ፡፡

REFERENCES (የመረጃ ምንጭ)

The Mosque part 1 (pdf)              The Mosque part 1 (word Document)

Ahlstrom, Sidney E. (1972), A Religious History of the American People (New Haven, CT: Yale University Press).

Bijlefeld, Willem A. (1993), “Black Muslims” The New Grolier Multimedia Encyclopedia [CD-ROM].

Farrakhan, Louis, (1995), Transcript from Minister Louis Farrakhan’s remarks at the Million Man March [Online], URL edition.cnn.com/US/9510/megamarch/10-16/transcript/

Gudel, Joseph P. and Larry Duckworth (1993), “Hate Begotten of Hate,” The Christian Research Institute [Online], URL www.iclnet.org/pub/resources/text/cri/cri-jrnl/crj0010c.txt.

Morey, Robert A. (1992) The Islamic Invasion (Eugene, OR: Harvest House).
West, Cornel (1993), Race 

 

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ