አጫጭር ዜናዎች
ኢራንያዊው ጠበቃ መሀመድ አሊ ዳድክሃ የዘጠኝ አመት እስራት ተፈረደበት
ጋርዲያን ሚያዝያ 25 2004 (May 3, 2012)
ታዋቂው ኢራናዊው ጠበቃ የዘጠኝ ዓመት እስር ተፈረደበት!
መሐመድ አሊ ዳድካ የተባለው ኢራናዊው ጠበቃ በኢራን ውስጥ ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ ላሉት ብዙ ሰዎች ጥብቅና ቆሞላቸው በመከራከር የታወቀ ነው፣ በስህተት አስተማሪነት ለታሰረው ሞቱን በመጠባበቅ ላይ ላለው ክርስትያን አገልጋዩ ፓስተር ዩሱፍ ናደርካኒንም ጠበቃው አሊ ዳድካህ ጥብቅናን ቆሞ እየተከራከረ ነበር፡፡
ጋርድያን ጋዜጣ በድረ ገፁ ላይ (http://www.guardian.co.uk/world/iran-blog/2012/may/03/iran-lawyer-mohammad-ali-dadkhah-sentenced) እንዳስቀመጠው በስህተት ትምህርት ተከሶ የሞት ፍርዱን በመጣባበቅ ላይ ላለውና በዓለም ዙሪያ ዋና አነጋጋሪ ርዕስ ስለሆነው የክርስትያን ፓስተር ጉዳይ እየሰራ ያለው ታዋቂው ጠበቃ ለዘጠኝ ዓመታት የእስር ፍርድ ተወስኖበታል፡፡
ከኢራን ዋና ከተማ ከቴህራን ለጋርዲያን ጋዜጣ ሲናገር መሐመድ አሊ ዳድካ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከማስተማር ወይንም ጥብቅና ከመቆምም ለተጨማሪ አስር ዓመታት እንደታገደ እንደሚከተለው በማለት ተናግሯል፡-
«የተፈረደብኝ ድርጊቴ የብሄራው ደህንነትን ስለሚጻረር፣ የተከለከሉ መጽሐፍትን በቤት ስለሰበሰብኩ እና መንግስትን የሚቃወም ፕሮፓጋንዳ ስለአሰራጨሁ» ተብሎ ነው ብሎአል። ከቅርብ አመታት ጀምሮ የኢራን ባለስልጣኖች ይህን የመሰለ የተድበሰበሰ ክስ ጠበቆችንና የመብት ተከራካሪዎችን ለመወንጀል ይጠቀሙበታል።
ዳድካህ አወዛጋቢ በሆነው የ2009 የአገሪቱ ምርጫ በኋላ በተነሳው ግርግር ለታሰሩ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ጥብቅና ቆሞአል። እንዲሁም ዓለም አቀፍ ውግዘት ላስከተለውና (http://www.guardian.co.uk/world/feedarticle/9871357), በእምነት መቀየር ወንጀል ተከሶ የሞት ፍርድ ለተፈረደበት ለ32 ዓመት እድሜ ላለው ለፓስተር የሱፍ ናድርካኒ የግል ጠበቃ ነው፡፡
መሐመድ አሊ ዳድካህ ፍርዱ እንዴት እንደነበር የገለጠው እንደሚከተለው ነው፡ «እኔ በቴህራን ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ያለውን አንዱን ባለጉዳዬን ዳቩድ አርጃንጊን ወክየ በተገኘሁበት ዳኛው ጠርቶ በእኔ ላይ የተወሰነው የዘጠኝ አመት እስራት የፀና መሆኑንና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ እስር ቤት እንደምላክ ነገረኝ» ሲል ለጋርዲያን ገልጾአል።
ከዳድካህ ባለጉዳዮች አንዱ ህመምተኛውና አንጋፋው ኢራንያዊው የፖለቲካ ሰውና የፖለቲካ እስረኛ ኢብራሂም ያዝዲ ይገኙበታል። ያዝዲ በሚመራውና በመንግስት በታገደው ተቃዋሚ ቡድን ከኢራን የነፃነት እንቅስቃሴ ፓርቲ ጋር ተባብረሃል ተብሎ ስምንት አመት ተፈርዶበታል።
ሌሎች የታወቁ ኢራንያውያን ጠበቆችም አብዱልፋታህ ሶልታኒን ጨምሮ የረጅም እስራት ተፈርዶባቸዋል። ባለፈው ማርች አብዱልፋታህ ሶልታኒን ላይ የ18 አመት እስራት ተወስኖበታል። እንደ ሶልታኒ ዳድካህ የኢራናዊ የኖቤል የሰላም ተሸላሚና በ2009 ከአገርዎ የተሰደደችው የሽሪን ኢባዲ የስራ ባልደረባ ነበር።
ሌላው እጅግ የተሞገሰው ታዋቂ ጠበቃ በታዳጊዎች ኢራናውያን ላይ ስለሚሰጠው የሞት ቅጣት በመቃወም የሚሰራውና በዚህም ስራው በአለም አቀፍ እውቅና ያገኘው ናስሪን ሶቱዴህ በቴህራን አደገኛው በኢቪን እስር ቤት ውስጥ ይገኛል። ስለታሰሩ የስራ ባልደረቦቻቸው ጥብቅና የቆሙ የሕግ ባለሙያዎች ደግሞ በቅርብ ዓመታት ውስጥ እየተያዙ ነው፡፡
ዳድካህ በእባዲ የሚመራ የኢራን የሰብአዊ መብት ተከላካይ ማእከል (DHRC) የመብት ተሞጋች ድርጅት ተባባሪ ነበር። ሌሎች ከ (DHRC) ጋር የተባበሩ ሰዎች የ39 አመት እድሜ ያለዉን ናርጌስ ሞሃመዲን ጨምሮ በእስር ላይ ናቸው (http://www.guardian.co.uk/world/iran-blog/2012/apr/26/iran-activist-narges-mohammadi-jailed). ።
የሰብአዊ መብት ተሞጋችች ተከላካይና ተመልካች የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ፌዴሬሽንና (FIDH) የአለም ፀረ ‘የስቃይ ቅጣት’ (torture) ድርጅት (OMCT) የጥምር ፕሮግራም በዕለተ ሐሙስ በዳድካህ ላይ የተወሰነዉንና መንግስት በስልት በ(DHRC) አባላት ላይ የሚያደርገውን ማጉላላት አውግዟአል።
«ብዙ የ(DHRC) አባላት አወዛጋቢ ከሆነው ከሰኔው 2009 ምርጫ በኋላ ያለአግባብ እስርና በፍርድ እጦት እየተንገላቱ ነው። እንደመግለጫው አባባል ከሆነ አቶ ዳድካህ ከታሰሩት የ(DHRC) አባላት አምስተኛው ይሆናል ማለት ነው፡፡
«በ(DHRC) ላይ እየተካሄደ ያለው ወከባና አባላቱን ፀጥ ለማሰኘት የሚደረገው ሙከራ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ይሄዳል የሚል ከፍተኛ ፍርሃት አለን» ሲል የ FIDH ፕሬዚዳንት ሶዩሃይር ቤልሃስን ተናግሮአል።
«የሰብአዊ መብት ተሞጋቾችን ፀጥ ለማሰኘት በኢራን ያሉ ባለስልጣኖች ረጅም እስራት በመወሰን፣ አገር ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግና ከሙያ ገበታቸው በማገድ ከፍተኛ ጫናና የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው። የዚህ ዋና ዓላማ መላውን ህብረተሰብ በማስፈራራት ፀጥ-ረጭ ለማሰኘት» ነው በማለት የOMCT ዋና ፀሐፊው ጀራልድ ስታብሮክ አክሎበታል።
ከዚህ በተለየ ሁኔታ ደግሞ ሌላ ፓስተር የ33 አመት ያለው ፋርሺድ ፋትሂ መንግስት ወደ ክርስትና የተቀየሩትን የማሳደድ እቅድ ሌላው ሰለባ ሆኖአል። የኢራን ክርስትና ዜና ወኪል እንዳለው አብዮታዊ ፍርድ ቤት በፓስተሩ ላይ የስድስት አመት እስራት ፈርዶበታል።
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
ከዚህ በላይ በኢራን ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር የተመለከትነው አጭር ዜና፣ ታላቅ ግፍ የሚሰራው በክርስትያኖች ብቻ ላይ ሳይሆን ክርስትያኖችን በሕግ ፊት ለመወከል በሙያቸው በተሰማሩም ሰዎች ላይ ጭምር እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው በኢራን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአረብ አገሮች ማለትም እስልምና የበላይነት ባለባቸው አገሮች ውስጥ ሁሉ ነው፡፡
ይህ ሁኔታ ለዓለም ሁሉ የሚያስተላልፈው አጠቃላይ መልእክት ይኖራልን ካለስ ምንድነው?
በእርግጥ አጠቃላይ መልእክት አለው፣ መልእክቱንም በሦስት ፈርጀን እንደሚከተለው ለመመልከት እንችላለን፡፡
አንደኛው፡ የሙስሊሞች አምላክ እንደ ክርስትያኖች አምላክ ለሰዎች ነፃነትን የማይሰጥ መሆኑን፡፡
ሁለተኛ፡ ሙስሊሞች የክርስትናን እምነት እውነተኛ መልእክትን በጣም የሚፈሩት መሆኑን፡፡
ሦስተኛ፡ እስላማዊ አገሮችና እምነቱ እራሱ ተከታዮቻቸውን መያዝ የሚችሉት በማስፋራራትና በኃይል ብቻ መሆናቸውን ያሳያል፡፡
ክርስትና ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነው፣ ማንም ተገዶ ወይንም ተስፈራርቶ ክርስትያን አይደረግም፡፡ ሰዎች ክርስትያኖች ለመሆን በቅድሚያ የራሳቸውን የተፈጥሮ ማንነት እና የፈጣሪን ባህርያት ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ፈጣሪ ቅዱስ ነው፣ ፈጣሪ ፍፁም ነው፣ ፈጣሪ በፍርድ አያዳላም፡፡ እውነተኛው ፈጣሪ በኃጢአትና በግፍ ስራዎች፣ በጥላቻዎች ሰዎችን አስገድዶ በማሳመን ስራ ላይ በፍፁም አይደሰትም፣ እንደዚህም ዓይነት መልእክቶችን በቅዱስ ቃሉ ላይ አላሰፈረም፡፡
እውነተኛው ፈጣሪ ለማንኛውም ሰው እውነተኛ የሆነ የፍቅር አመለካከት አለው፡፡ እውነተኛው ፈጣሪ ሰዎች በተፈጥሯቸው ኃጢአተኞች ስለሆኑ በራሳቸው መልካምም ሆነ ክፉ ስራ የዘላለም መንግስትን መውረስ እንደማይችሉ፣ የኃጢአትም ቅጣቱ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ የራሱን ልጅ ጌታ ኢየሱስን የሰውን ስጋ ለብሶ በመምጣት ለሰዎች ኃጢአት የቅጣትን ዋጋ እራሱ ተቀጥቶ እንዲከፍልላቸው ላከው፡፡
ዓላማውም ሰዎች በእርሱ በኩል ከፍፁምና ቅዱስ እግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁና በዚህም ምድር እያሉ እውነተኛ ሰላምንና እረፍትን እንዲያገኙ በመጨረሻም የዘላለምን ሕይወት እንዲወርሱ ነው፡፡
ጥሪ ለሙስሞች!
በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች እንደምትከታተሉት ሁሉ፣ በሰዎች ልጆች ላይ እጅግ የሚዘገንኑና ሰብዓዊ ያልሆኑ ነገሮች በእላማዊ አገሮች ውስጥ እየተፈፀሙ ነው፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች ጥያቄ ትጠይቃላችሁን? የሰው ልጅ ፈጣሪ አምላክ የእንደዚህ ዓይነት ግፍ ምክንያት ሊሆን ይችላልን? የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ግን የተለየ መልእክት አለው አንብቡትና የእግዚአብሔርን መልእክት አስተውሉ ወደ እርሱም የምትመጡበትን ትክክለኛ መንገድ ይጠቁማችኋል፡፡
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ