አጫጭር ዜናዎች 

ከጥይት ጥቃት የተረፉት ሰርገኞች
Religion Today
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

በፈንጆቹ ጥቅምት 20/2013 በኛ ጥቅምት 10/2006 ይካሄደ በነበረው ሰርግ ላይ በሙስሊሞች አማካኝነት በደረሰው የተኩስ ጥቃት የ12 ዓመት ልጇ ተገድላ እርሷ የቆሰለችው እናት በካይሮ ከተማ ዳርቻ ላይ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ሐሙስ ጥቅምት 24 በምሬት እና በሐዘን ውስጥ ሰጥማለች፡፡

የ30 ዓመት ዕድሜ ያላት ሆዊዳ ራፋት አዜር፣ ቀኝ እግሯን ኦፕራሲዮን ሆና ቀንና ሌሊት ሳትነቃ ከቆየች በኋላ ጥቅምት 24 ሐሙስ ዙሪያዋን የከበበቧት ቤተሰቦቿ በመጨረሻ ባገኙት ብርታት ልጇ ማርያም ናቢል ፋሀሜ አዘር፤ ሌሎች ሶስት የሰርጉ ተሳታፊዎችን የገደለው ተኩስ እንደገደላት ለማናገር መቻላቸው ነበር፡፡ ከሰዓታት በኋላ አዜር ከኦፕራሲዮኑ ድንዛዜና ስቃይ ከጎን ወደ ጎን እየተገላበጠች አጠገቧ የከበቧት አምስት ሴቶች ለማፅናናት አልቻሉም ነበር፡፡

በፀጥታው ጊዜ ወደ ፊት ትኩር በማለት ተመልክታ ምንም ዓይነት የስሜት ገፅታ ሳታሳይ እና በባዶነት ቆይታ በድንገት ከትራሱ ላይ እራሷን ቀና በማድረግ ወደ ጣራው ተመልክታ የልጇን ስም እየጠራች ማልቀስ ጀመረች፡፡

“ማርያም!” ኦ እግዚአብሔር ሆይ ለምን ከእኔ ላይ ወሰድካት? ሁለት ልጆችን ሰጠኸኝ! እና ለምን አንዷን ከእኔ ወሰድክብኝ?” በጣም አለቀሰችና እንደገና ወደ እልጋው ውስጥ ተመልሳ ዘፍ አለች፡፡ ቀጥሎም እንደሚከተለው “እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁኝ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ እንዲህ ያለውን ስቃይ ልሸከመው አልችልም” በማለት አጉተመተመች፡፡

የአዜር ሴት ልጅ ከተገደሉት ሁለት ሴቶች ልጆች መካከል አንዷ ነበረች፣ በጊዛ በሚገኘው በቅድስት ማርያምና የመላእከት አለቃ ሚካኤል  የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ውስጥ ይካሄድ በነበረው የሰርግ የሃይማኖታዊ የጋብቻ ስርዓት በመጠባበቅ በነበሩ ሰዎች ላይ የአውቶማቲክ ጠመንጃ እሩምታ ተኩስ ተነዛባቸው፡፡ በአልዋራቅ አካባቢ በሚገኘው ቤተክርስትያን ውጭ የሰርጉን ስርዓት ደስታ ለመካፈል ሕዝቡ ቆሞ እየተጠባበቀ ነበር፡፡ ሌላዋ የተገደለችው ልጅ የ8 ዓመቷ ማርያም አሸራፍ መሲሃ ነበረች፣ እርሷም የሞችቷ የ12 ዓመቷ የአጎት ልጅ ነበረች፡፡ ጥቃቱም የተደረገው ከስልጣኑ በተነሳው በፕሬዜዳንት መሐመድ ሙርሲ ደጋፊዎች በተቀሰቀሰው ፀረ ክርስትያን ዓመፅ ነው፡፡ የሙስሊም ወንድማማች አባላትና ደጋፊዎች ለፕሬዜዳንት ሙርሲ መውደቅ ምክንያት የሆኑት ክርስትያኖች ናቸው በማለት ክርስትያኖችን ይወነጅላሉ፡፡

የ62 ዓመቷና የወንዱ ሙሽራ እናት ካሚላ ሔልሚ አቴያ፣ ከቤተክርስትያኑ ደረጃ ውጭ ሞታለች፡፡ የ46 ዓመቱ ሳሚር ፋህሜ አዜር ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ወይንም እዚያ ከደረሰ በኋላ ወዲያውኑ ሞቷል ልክ እንደ ሴቶቹ ልጆች እንደ ቤተሰቡ መረጃ ከሆነ እርሱ የሆይዳ አዜር ባለቤት ወንድም ነው፡፡

ከቤተክርስትያን ውጭ የጋብቻውን ጊዜ እየተጠባበቀ ባለው ሕዝብ ላይ የጥይት እሩምታ ከወረደባቸው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ የጋብቻው ስርዓት ተፈፅሟል፡፡ ተጋቢዎቹም ጥቁር የሐዘን ልብስን ለብሰው ነበር፣ የሙሽራው ወንድም ለMorning Star News የተናገረው ነገር የስርጉን ስርዓት የተሳተፉት ሦስት ሰዎች ናቸው በማለት ነበር፡፡

ከአራት ቀናት በኋላ ዘመዶች ለሆይዳ አዜር ልጇ እንደተገደለች ሲነግሯት በጣም በሐዘን ደቅቃለች ነገር ግን እንደዚህ ዓይነት ነገር እንደሚሆን ገምታ ነበር፤ ምክንያቱም በሆስፒታል አልጋ እየታከመች እያለች ተደጋጋሚ ሕልምን ብዙ ጊዜ እንዳየች ለዘመዶቿ ነግራለች፡፡ እርሷም ሞቿ የ12 ዓመት ልጇ ከሞት በኋላ ነጭ ልብስን ለብሳ እርሷም ደህና እንደሆነችና ስለ እርሷ እንዳትጨነቅ ለእናቷ እንደነገረቻት ነግራቸዋለች፡

የተጠቁት እምነት

በማዓዲ በሚገኘው በወታደራዊው ሆስፒታል አምስተኛው ፎቅ በሙሽራዎቹ ቤተሰቦች ተሞልቷል፣ ልክ እንደ አዜር እነርሱም ሁሉም ያመኑበት ነገር ወደ እግዚአብሔር ከመመልከት ውጭ ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌላቸው ነው፡፡

የሆይዳ አዜር የልጇ ሞት ጭከና እንደሆነው ሁሉ፣ የሙሽራይቱ ዘመድ ለሆነው ለእርሷ ባል ለ40 ዓመቱ ለናቢል ፋህሜ አዜር እና ቆስሎ በሆስፒታል ላለው ስለ ሴት ልጁ ሞት ሊነግሩት በፍፁም አልደፈሩም፡፡ የወንድሙን እና የወንድሙን ልጅ መሞት ከሰማበት ጀምሮ ናቢል አዜር ለመናገር እለቻለም፡፡ ከቁስሉ አሁንም እያገገመ ነው ቤተሰቦቹ የፈሩት የልጁን መሞት ከሰማ ያብዳል ወይንም ይሞታል በማለት ነው፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ባሉት ጋዜጦችና ቴሌቪዥኖች ዜናዎች ሁሉ ላይ የልጁ ፎቶ እየታየ ስለሆነ ማንኛውም ጋዜጣ ወይንም ቴሌቪዥን ወይንም መጽሔት ወደ እርሱ እንዳይቀርብ ተክልክሏል ሬዲዮም ሆነ ኢንተርኔት በእርሱ ዙሪያ ፀጥ እንዲል ተደጓል፡፡

የእርሱ እምነት ይህንን አሰቃቂ ሁኔታ እንዴት እንደሚጋፈጠው እየተጠበቀ ነው፣ የሌሎቹ እምነት በጣም ግልፅ ሆኗል፡፡ በሐኪም ቤቱ ውስጥ ያሉትና በብዛት ከጥቃቱ በጥይት እግራቸውን የቆሰሉት ወንዶቹ ናቸው፡፡ አንዱ ልዩ የሆነው ጉዳይ አንገቱን በጥይት የተመታው የ33 ዓመቱ የአሽራፍ አያድ አቲያ ጉዳይ ነው፡፡ ተዓምራዊ በሆነ መንገድ ጥይቷ ጉሮሮውን የደም ስሩን ወይንም የሰረሰር አጥንቱን ሳትነካ በስጋው ውስጥ ያለምንም ችግር አልፋለች፡፡

ማክሰኞ እለት እርሱ ምንም እንኳን በሕመም ውስጥ ቢሆንም እየሳቀ እርሱ በሕይወት በመኖሩ ምን ያህል እድለኛ መሆኑን ገልጧል፡፡ እንዲህም ብሏል “እኔ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁኝ ሕይወቴን ስላዳናት”

አፋዊ ክርስትያን እንደነበረ እራሱ የገለፀው የ40 ዓመቱ አዋድ ቦትሮስ ካሊል እንዳለው፣ ተኩሱ እርሱ ምን ያህል እምነት የጎደለው መሆኑን አሳይቶታል፡፡ እርሱም ቀኝ እግሩን በጥይት ተመትቷል፡፡ ጥይቱም ከእግሩ በላይ በቅልጥሙ ውስጥ ገብቶ ሦስት የደም ስሮችን በጥሷል ስለዚህም አሁን መራመድ አይችልም፡፡ የቤተክርስትያን አገልግሎቶችን መሳተፍ መሞት በሆነበት አገር ውስጥ እርሱ የተናገረው፡ አሁን መንፈሳዊነትን “ማሳደግ እንዳለበት ነው”፡፡ “እኔ በጥይት በተመታሁበትና እንደ ሞተ በሆንኩበት ጊዜ የሰዎችንና የእግዚአብሔርን ፍቅር በዙሪያየ ከቦኝ አየሁኝ ከዚያም አሁን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብኝ አወቅሁኝ” በማለት ነው፡፡

የእርሱም ዓይነት አስተያየት በሆስፒታሉ የሕሙማን ክፍል ውስጥ ባሉት በሁሉም ለማለት ይቻላል ተስተጋብቷል፡፡

ከቆሰሉት መካከል በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ውስጥ ከነበሩትና ከቆሰሉት መካከል ሁለቱ ልጆች የ13 ዓመቷ ማሪና መጊድ ጆርጅ ስትሆን ጥይቱ እጇን ጎድቶታል፡፡ ሌላው ደግሞ የ7 ዓመቱ ፍሎባተር አሽራፍ ሲሆን ሆዱን ስለተመታ በጣም በጣርና በአደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡

ከተጠቁት ውስጥ ብዙዎቹ በጥይት መመታታቸውን እንዳላወቁት ወይንም ተኳሾቹንም እንዳላዩአቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ተኳሾቹን በሞተር ሳይክል ላይ ሆነው ሲተኩሱ እንዳዩአቸው ነው፡፡ ተኳሾቹ እንዳይታዩ ለማድረግ ራሶቻቸውን በስካርቭ ተጠቅልለው እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ከሞተር ሳይክሉም ላይ በመሆን ከተኳሾቹ አንዱ ከጠመንጃው ውስጥ ያሉትን ጥይቶች በሙሉ እንደጨረሳቸው ቀጥሎም ሌላ ዙር እንደገና እንደጨመረና በሕዝቡ ላይ ተኩሶ እንደረጨው ነው፡፡ እነርሱንም የተከተለ ሌላ መኪና የትራፊክ መንገዱን ዘግቶ ነበር ይህም ሰዎች እንዳያመልጡ ለማድረግ የነበረ ሲሆን መኪናውና ሞተር ሳይክሉም ግዳጃቸውን ከፈፀሙ በኋላ ወዲያው ወደ ዋናው መንገድ በመብረር በሌሎች መኪኖችና ትራፊክ ውስጥ ተደባልቀው አምልጠዋል፡፡

የአዜር ቤተሰብ አባላት የተናገሩት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አማኞች  በጥቃት ላይ ያሉ ሕዝቦች መሆናቸውን ሲሆን ጥቃቱ ግን እምነታቸውን እንዳጠናከረው ነው፡፡

ተኩሱ በተጀመረበት ወቅት ቄስ ሶዋሪስ ቦሽራ በቤተክርስትያኑ ቤተመጻሕፍት ውስጥ ነበሩ፡፡ ጥቃቱ በአካባቢው ባሉ ክርስትያኖች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው በማለት ቄሱ ተናገርው ይህም ከብዙ ስሜቶች ጋር ሲሆን እኛም በጥቃት ውስጥ ነው ያለነው በማለት በመግለፅ ነው፡፡ የጥቅምት 20 ጥቃት፣ የከዚህ በፊት ዕልቂት ጥቃቶችና የወደፊት መጪ የዕልቂት ጥቃቶች የምንጠብቃቸው ናቸው በማለት ቄሱ ተናግረዋል፡፡

“ክርስትና በስደት ነው የተመሰረው” በማለት ተናግረው “ክርስቶስ ሰዎች ክርስትያኖችን ገድለው የእግዚአብሔርን ፈቃድ አገለገልን የሚሉበት ሰዓት ይመጣል በማለት ተናግሯል፣ ያ የክርስቶስ ቃል አሁን እየተፈፀ ነው” ብለዋል፡፡

ከጥቃቱ ጥቂት ቀናት በኋላ የቤተክርስትያን መሪዎች ፖሊስን ወንጅለዋል፣ ምክንያቱም በወቅቱ ጥበቃ ባለማድረጋቸው ነበር፡፡ በቤተክርስትያናት ላይ ከሚደርሰው የማያቋርጥ ጥቃትና ሽብር የተነሳ የፖሊስ ጥበቃ በቤተክርስትያን አካባቢ በግብፅ ተለምዷል፡፡ በዚያን ዕለት የጥበቃ ፖሊሶች በሰዓቱ አልነበሩም ወይንም ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት ስፍራውን ለቀው ሄደው ነበር የሚሉ መረጃዎች አሉ፡፡

ብዙዎች ግን ብቁ ጥበቃ መደረጉ ምንያህል ጥቃቱን እንደሚያድን ወይንም ሊገድበው እንደሚችል ይጠራጠራሉ ነገር ግን የአሁኑ ጥቃት ከጥበቃ ፖሊሶች ግዴለሽነት እንደነበረ ወይንም ሙሉ ለሙሉ አለመኖር እንደሆነ ምርመራ እንዲደረግ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በትክክል ባይረጋገጥም ጥቅምት 21 ቀን ጥቃቱን በተመለከተ የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የተነገረ መረጃ አለ፡፡


ጥቃቱ

በዚያን ምሽት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር) በዓይን ምስክሮች መሰረት ተባባሪው መኪና በቤተክርስትያኑ ሕንፃ ፊት ለፊት ያለውን መንገድ ከትራፊክ መተላለፍ ዘጋው፣ ይህም ሞተር ሳይክሉ ወደ ቤተክርስትያኑ መግቢያ ተጠግቶ ከአንድ አውቶማቲክ ጠመንጃ ላይ ተኳሾቹ በሕዝቡ ላይ ጥይትን በሚያርከፈክፉበት ጊዜ ነበር፡፡

ከተገደሉት አራት ክርስትያኖች በተጨማሪ 17 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፣ ሁለት ሙስሊም ወንዶችና እና አንድ ሙስሊም ወንድ ልጅም እንዲሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዜና ጋዜጣ “ሳምንታዊው ዋታኒ” መሰረት ሁለት ልጆች የገቡበት ሳይታወቅ ጠፍተዋል፡፡

ከተገደሉት ወይንም ከቆሰሉት መካከል ከሦስቱ ሙስሊም ወንዶች በስተቀር ሁሉም ማለት ይቻላል፣ የሙሽራው ወይንም የሙሽራይቱ ቤተሰቦች ናቸው፡፡ ሐሙስ ዕለት ማታ የ17 ዓመቱ መሐመድ ኢብራሂም፣ በመንገድ ላይ ቆሞ ይመለከት የነበረውና ከሙስሊሞቹ አንዱ በጥቃቱ የቆሰለው ሆስፒታል እንዳለ ሞቷል፡፡

በግብፅ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ላይ እየተደረገ ካለው የማይታወቁ ሰዎች ጥቃት የነሐሴ 6 የተኩስ ግድያን እና የ10 ዓመት ልጅ ጅሲካ ቦሎስ የሞተችበትን ጨምሮ ለግድያዎቹ ማንም ሐላፊነት እወስዳለሁ ያለ ቡድን የለም እንዲሁም ማንም በቁጥጥር ስር አልዋለም፡፡

ጥቃቱ ከተፈፀመ ከሁለት ቀናት በኋላ የጥቃቱ ሰለባዎችና በተለያዩ ሆስፒታሎች እየታከሙ የነበሩት ወደ ወታደራዊ ሆስፒታሎች እንዲዛወሩና እንዲታከሙ መንግስት ትዕዛዝን አስተላልፎ እዚያ እየታከሙ ነው፡፡ በግብፅ ሁሉ ውስጥ ወታደራዊ ሆስፒታሎች ከሌሎቹ ብዙዎች ሆስፒታሎች ጥራት ያላቸውና ጥሩ ሐኪሞች የሚገኙባቸውና የተሻለ የሕክምና አሰጣጥ ደረጃ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡

በሐምሌ ወር ፕሬዜዳንት መሐመድ ሙርሲ ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ከደረሱት ጥቃቶች የሰርጉ ጥቃት የቅርቡ ነው፡፡ ወታደሮች የሙርሲ ደጋፊዎች የሰልፍ ካምፕን ካፈረሱ በኋላ በክርስትያኖች ላይ የደረሰው እስላማዊ ጥቃት 60 ቤተክርስትያናትን ብዙ በክርስትያን የሚመሩ የንግድ ቤቶችን በግብፅ ሁሉ ውስጥ አጥቅቷል፡፡ መጠነ ሰፊ ጥቃቱ ከቆመ በኋላም ድንገተኛ እና አልፎ አልፎ ያልታሰቡ ወደ ሆኑ ዓይነት ጥቃቶች ተቀይሯል፡፡

ሐምሌ 6 ቀን ሚና አቦድ ሻርዌን (ቀደም ሺል ሳሩቢም በመባል የሚታወቀው) የኦርቶዶክስ ቄስ በሰሜን ሳይናይ በኤል አሪሽ በጥይት ተገድሏል፡፡ ከቀናት በኋላም የታዋቂው ክርስትያን የንግድ ሰው የማግዴ ላሜ ጭንቅላቱ የተቆረጠ አካል በሼክ ዙዋይድ ከተማ ተገኝቷል እርሱም በሰሜን ሳይናይ ነው፡፡ ድንገተኛው ጥቃት በቦሎስ የተኩስ ግድያ፤ እንዲሁም በመስከረም 30 በሚንያው ጳጳስ በአንባ ማካሪዮስ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራዎች፣ በክርስትያኖች ላይ የሚካሄደው ጥቃት ቀጥሏል፡፡

እነዚህም የመጡት በእስላሚስቶች በሚጠለፉትና በየሳምንቱ መጥፋታቸው ሪፖርት ከሚደጉት የግብፅ ኦርቶዶክሶች ዜና ውጭ ነው፡፡ ጠለፋዎቹ የሚደረጉት የመመለሻ ገንዘብን ለማግኘት ከሚኖር ተስፋ ነው ይባል እንጂ የሚደረገው ጠለፋ መጠን መብዛቱ የሚያመለክተው፤ የሚደረገው ነገር ሁሉ ከክርስትያኖች ጥላቻ የተነሳ እንደሆነ ነው፡፡

በበጋው ጊዜ እስላሚስቶች በመሐከላዊ ግብፅ ውስጥ ያለችውን ከተማ ዴልጋን ተቆጣጥረዋል፣ በዚያም በየለቱ የሚደረገው ነገር ክርስትያኖችን በማስፈራራትና በማስጨነቅ እንዲሁም የጂዝያ ቀረጥን እንዲከፍሉ በማስገደድ ነው፡፡ መስከረም 16 መንግስት በስተመጨረሻ ጣልቃ ገብቶ ወታደሩ ከተማዋን ተቆጣጥሮታል ከእስላሚስቶችም እጅ ነፃ አውጥቷታል፣ ይህም ከብዙ ቀናት ጦርነት በኋላ ሰላምና መረጋጋት በከተማዋ ላይ ሰፍሯል፡፡


የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

የግብፅ የኦርቶዶክስ እምነት ጥንታዊና ከእስልምና እምነት በፊት የነበረ ነው፡፡ እስልምና በግብፅ ከመስፋፋቱ በፊት ክርስትያኖች እንደማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሃይማኖት ጭቆና ሳይኖርባቸው እነርሱም የሌላውን እምነት ሳያጠቁ ኖረዋል፡፡ በጥንታዊው የግብፅ ክርስትና ላይ እንደዚህ ዓይነት ጥቃት እየተከሰተ ከሆነ፣ ለእስልምና እምነት ክርስትያኖችና ሌላው ሕዝብ የሚሰጠው ግምት እና አመለካከት በጣም ጥሩ ሊሆን እንደማይችል ማንም መገመት ይችላል፡፡

ጥቅምት 20 በሰርጉ ላይ የደረሰው ጥቃት ለምን ደረሰ? እስላሞች  ሰላማዊ ሰዎችን ስለምን ያጠቃሉ? የሰው ልጅ ሁሉ ያለምንም የዘር የፆታ ልዩነት እንዲሁም የሃይማኖት እምነት ሰብዓዊ መብቱ ሁሉ ተጠብቆለት መኖሩ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለምንድነው የማይዋጥላቸው? የጋብቻ ስርዓትን ለማየትና ደስታቸውን ለመግለፅ የሄዱ ሰዎች፣ ልጆችና ተመልካቾች መገደላቸው፣ የሟቾች ሰዎች ቤተሰቦች በሐዘን መነከራቸው ለእስላሞች ደስታ ሰጪ የሆነው ለምንድነው? የዚህ ገፅ አዘጋጆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ቢችሉም፣ አንባቢዎች በጥልቅ እንዲያስቡባቸውና እራሳቸው መልሱን እንዲፈልጉ ይጋብዛሉ፡፡

በመቀጠልም ከሰርጉ ጥቃት በኋላ የኦርቶዶክሱ ቄስ የተናገሩትን የጌታ ኢየሱስን ትንቢታዊ ቃል ማስታዎስ እንፈልጋለን፡ “ክርስትያኖችን የሚገድሉ፣ ክርስትያኖችን በመግደላቸው የአምላክን ፈቃድ የሚፈፅሙ የሚመስላቸው ጊዜ አሁን እየሆነ ነው፡፡” አዎን የትንቢቱ ፍፀሜ ቢሆንም እንኳን ንፁሃን ሰዎች በየቤተ አምልኮታቸው መገደላቸው የአምላክ ፈቃድ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱሱ የክርስትያኖች እግዚአብሔር የፍቅር፣ የይቅርታ የሰላም አብሮ የመኖር አምላክ እንጂ ግፍ እንዲፈፀም ጭከናን እና ሰብዓዊ ያልሆኑ ነገሮችን በሰዎች ላይ እንዲከናወኑ የሚፈቅድ አምላክ አይደለም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው” ይለናል፣ በተጨማሪም “ዓለምን እንደዚህ ወዶ ሰዎች የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸው እንጂ እንዳይጠፉ ልጁን ጌታ ኢየሱስን ላከው” ይለናል፡፡

ይህ የእርሱ ፍቅር ወደ እግዚአብሔር እንድንመጣ እርሱን እራሱን እንድናውቀውና መንግስቱን እንድንወርስ የሚደረግልን የፍቅር ግብዣ እንዲሁም የእውነተኛ ፍቅር መግለጫ ነው፡፡ ይህንን ፍቅር ልናገኝ የምንችለው በንስሐ ወደ ፊቱ በመቅረብና ይቅርታን በመጠየቅ ክርስቶስ ስለ ሕዝቡ በከፈለው የኃጢአት መስዋዕትነት ላይ ስንታመን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡


Reference (የመረጃ ምንጭ): http://www.religiontoday.com/blog/traumatized-survivors-wedding-attack-egypt-look-to-god.html

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ