አጫጭር ዜናዎች
በፓኪስታን ዘገምተኛዋ የ11 ዓመት ልጅ ልትገደል ነው!
The Christian Science Monitor: 12 August 2012
ፓኪስታን ፕሬዜዳንት በ11 ዓመቷ ዘገምተኛ ልጅ ስድበ-መለኮት ጉዳይ ውስጥ ተነክሯል፡ የፕሬዜዳንት ዛርዳሪ ጣልቃ ገብነት በመንግስት ውስጥ ያሉትን ለዘብተኛ ፓርቲዎች ጥምረት የስድበ-መለኮት (ብላስፌሚ ሎው) ህግ የማሻሻልን አጀንዳ እንደገና እንዲያነሱ አመላካች ሊሆን ይችላል ሲል የክርስቲያን ሞኒተር ቃል አቀባይ ታሃ ሲዲኪ በ August 20, 2012 ዝርዝሩን እንደሚከተለው ያቀርባል።
ሰኞ Aug. 20, 2012 በእስላማባድ ፓኪስታን ከከተማው ወጣ ብሎ ያለውን የተዘጋ የአንድ የክርስቲን ወጣት ቤት የአካባቢው ሴቶች ተራምደው ያልፉታል። የፓኪስታኒ ባለስልጣኖች የ11 አመት ክርስቲያን ወጣት አስረው የሃገሪቱን ጥብቅ የስድበ-መለኮት ህግ ማፍረሷን መመርመር የጀመሩት እጅግ የተበሳጩ ጎረቤቶቿ ቤቷን ከከበቡና ፓሊስ እርምጃ እንዲወስድባት ከጠየቁ በኋላ ነው ሲል አንድ የፓሊስ መኰንን በእለቱ ተናግሯል።
የሃይማኖት መጽሐፍትን አቃጥለሻል በሚል ተከሳ ካለፈው ሳምንት ጀምራ የ11 አመት ክርስቲያን ወጣት እስር ላይ ትገኛለች። ህይወቷ የሚወሰነው ከመንግስት እየተጠበቀ ያለው የህክምና ዘገባ የአእምሮ በሽተኛ መሆኗን ካረጋገጠ ነው።
አወዛጋቢ በሆነው በፓኪስታን የስድበ-መለኮት ህግ የእስልምናን መጽሐፍትን ያበላሻ የሚቀጣው በሞት ነው። የአካባቢው የዜና ምንጮች ወጣቷ ዝግምተኛ መሆኗን ስለገለጹ የመንግስት ባለስልጣናት በነፃ እንዲለቋት ምክንያት ይሆናቸዋል።
ከቅርብ አመታት ጀምሮ ፓኪስታን የስድበ-መለኮት ክሶችን ለማስተናገድ እየተቸገረች ነው። አገሪቱ በአለም እይታ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ባለችበት ወቅት እንደዚህ አይነት ክሶች እዚህ ከተማረዉና ከአናሳው ወገን ብቻ ሳይሆን በፓኪስታን እየተጧጧፈ ያለውን የሃይማኖት እንቅስቃሴ በጭንቀት ከሚመለከተው ከአለም አቀፍ ማህብረተሰብ ከፍተኛ ውግዘትን ያስከትላል። የአካባቢው ማህበረሰብ በሃይማኖት ዘለፋ በተከሰሰ ሰው ላይ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጁ ስለሆነ በፓኪስታን መሪዎች ላይ ጫና አለባቸው።
በልጅቱ ጉዳይ የፓኪስታን ፕሬዜዳንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ ቶሎ ጣልቃ በመግባትና «ትኩረት» ሰጥቸዋለሁ በማለት ለባለስልጣኖቹ ጉዳዩን እንዲመረምሩ መመሪያ ሰጥተዋል። እዚህ ያሉ አንዳንድ ተንታኞች ከክሱ መልካም ነገር ይወጣል ይላሉ።
«ይህ ክስ በህብረተሰብ ውስጥ እያደገ የመጣውን የእኔ እምነት ብቻ ትክክል ነው የሚለውን ግትር ሃሳብ ሰዎች ስለሚከተሉ የአእምሮ ችግር ያለባትን ህጻን እንኳን ለመታደግ ተስኖአቸዋል» ሲል የታወቀው ጋዜጣ ጸሐፊ ራዛ ርኡሚ ተናግሮአል። ቀጥሎም ሲናገር በቅኝ ግዛት ዘመን በወጣው ሃይማኖትን ዘለፋ ህግ ውይይት ለማድረግ በተደረገው ሙከራ ለውጥ በሚፈልጉ ሙስሊሞች ላይ ማስፈራራትና ሞት ደርሶባቸዋል። «ዳሩ ግን የፕሬዚዳንቱ ጣልቃ ገብነት ጤናማ ምልክት ሲሆን በመንግስት ውስጥ ያሉት ለዘብተኛ ፓርቲዎች ጥምረት ጉዳዩን አንስተው የስድበ-መለኮት ህግ እንደገና እንዲሻሻል ሊያደርጉ ይችላሉ» ብሏል።
ከእስላማባድ ወጣ ብሎ ከሚገኘው ልጅቱ ከምትኖርበት የድሆች መንደር ያሉ ሰዎች እንደሚሉት ጉዳዩ በክርስቲያኑና በሙስሊሙ መካከል ውጥረትን ስለፈጠረ በቁጥር አናሳ የሆነው ክርስቲያን አካባቢውን እንዲለቅ ተገዷል።
«የአካባቢያችን ሁኔታ እስከሚረጋጋ ድረስ ርዋልፕኢንድ (Rawalpindi) ካሉ ዘመዶቻችን ጋር ተቀምጠናል ስት » ሻብናም የተባለች በፓኪስታን ዋና ከተማ በእስላማባድ በሃብታም ቤተሰብ ውስጥ የቤት ሰራተኛ የሆነች ገልፃለች። «ሙስሊም የሆነው አሰሪያችን በስድበ-መለኮት ወይንም ብላስፌሚ ተከሳ ልጅቷ ከታሰረች በኋላ ለህይወታችን አስጊ ስለሆነ ቤቱን እንድንለቅና ከአካባቢው ለጥቂት ቀናት ርቀን እንድንቀመጥ ነግሮናል»።
በቁጥር ስምንት የሆኑ ቤተሰቧ መቼ ወደ ቤታቸው እንደሚመለሱ አላውቅም ነው ያለቸው ሻብና፡፡ በሰፈሯ ያሉ ሙስሊሞች ክርስቲያኖች የሚኖሩበትን አንዳንድ ቤቶችን ለማጥቃት ሙከራ ለማድረግ ቢሞክሩም ፖሊስ ጣልቃ በመግባቱ ሙከራቸው ከሽፎአል፡፡ ይህንንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ሰላም አማካሪ ፖል ባህቲ አረጋግጧል።
በመቶ የሚቆጠሩ ጎረቤቶቿ የልጅቱን ቤት ከከበቡና ፓሊስ እርምጃ እንዲወስድባት ከጠየቁ በኋላ ነበር በAug. 16, 2012 የታሰረቸው። ለህዝቡ የተናፈሰው ወሬ ልጅቱ ካይዳ የእስልምና ጽሑፎችን በአጭሩ የሚጠቅስ የቁርአን የማስተማሪያ ዘዴ መጽሐፍን አቃጥላለች የሚል ነበር።
ዶ/ር ባህቲ እንዳለው «አርብ ከእስላማባድ ወጣ ብሎ ከሚገኝ መንደር ዘገባ ደረሰኝ። ከአርብ ፀሎት በኋላ የአካባቢው የሃይማኖት መሪ 1000 ለሚሆኑ ሰዎች ክርስቲያን ወጣት ስድበ-መለኮትን አድርጋለች በሚል በአካባቢው ያሉ ክርስቲያኖች እንዲገደሉ ጠይቋል። ዳሩ ግን ፖሊስ በፍጥነት ጣልቃ በመግባቱ ህዝቡን ለማረጋጋት ችለናል» ብሏል።
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
የዜናው ምንጭ ICC እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በነሐሴ 22፣ ለአስቸኳይ ዜና ባቀረበው ዘገባ ላይ የ11 ዓመቷና ከወሊድ ጀምሮ በሚመጣና ዳውንስ ሲንድሮም በሚባል፣ የዘገምተኝነት ሕመም ውስጥ ስትሆን በፓኪስታን የሕክምና ዶክተሮች የዕድሜ ምርመራ ተደርጎላት 14 ዓመት ልጅ ናት ተብሎ እንዲወሰን ተደርጓል፡፡ የዚህም ዋናው ምክንያት በወጣት አጥፊነት ለመከሰስና በክሱም መሰረት ቅጣት የምትቀበል ናት ወደሚል መደምደሚያ ለመድረስ ብቻ ነው፡፡ በሚቀጥለው ነሐሴ 25 ቀን ለፍርድ እንደምትቀርብ እንደሚጠበቅ የገለፀው ዜና ልጅቷ በከፍተኛ የድንጋጤ ጭንቀት ውስጥ እንዳለች ቤተሰቦቿም አካባቢውን ለቅቀው እንደተሰደዱ ያስረዳል፡፡
ጠበቃዋ ቾዳሪ በእስር ቤት እንዳለች ከጎበኛት በኋላ ለNPR እንዳለው “የምከራከርላት ተከሳሽ በፍፁም ጥፋተኛ አይደለችም እርሷ ትክክል የሆነውንና ያልሆነውን አትለይም፣ አሁን ያለችው ሙሉ በሙሉ በፍርሃትና በልቅሶ ውስጥ ነው፤ እርሷ በጭራሽ ማንበብና መጻፍም አትችልምም ብሏል” የፋውንዴሽን ፓኪስታን የአገር ዳይሬክተር የሆነው ሃቪየር ፒ ዊሊያምስ ደግሞ እንዳለው ሪምሻን በፖሊስ ጣቢያ አግኝቻታለሁኝ “ሕዝቡ በቁመናዋ ሊያቃጥላት ይፈልጋል፣ እርሷ ምንም ወንጀል የሌለባት ልጅ ናት፤ አሁን ያለችው በከፍተኛ ድንጋጤና ጭንቀት ውስጥ ነው” በማለት ለቢቢሲ ዜና ዘጋቢ ተናግሯል፡፡
የሪምሻን መያዝ ተከትሎ ከ600 እስከ 1000 የሚሆኑ ሙስሊሞች ከፍተኛ ብጥብጥ አስነስተው የብዙ ክርስትያኖችን ቤት አቃጥለዋል ክርስትያኖችም አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡ ሕዝቡ የሚፈልገው እርሷ በሕዝቡ ፊት በቁም እንዳለች እንድትቃጠል ነው፡፡ የአካባቢው መስጊድ ረዳት አስተዳዳሪ የሆነው ሻውካት አሊ “ቅርአንን ያቃጠለ እርሱ እራሱ መቃጠል አለበት በማለት ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ይህ አስገራሚ ክስተት ነው፡፡ ይህ የእስልምናን እምነት ምንነት በግልፅ የሚያሳይ እውነታ ነው፡፡ እስልምና በበላይነት በሚገዛበት አገር ሁሉ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁሉ ተመሳሳይ ነው፡፡ ክርስትያኖች የመኖር መብት የላቸውም፣ በጥላቻ ስድበ-መለኮት አድርገዋል ተብሎ ቢከሰሱ ማንም ሰው ተነስቶ የሞት ፍርድ ሊፈርድባቸው ይችላል፡፡
ይህንንና ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶች የስብዓዊ መብት እና የሰው ልጅ ፍቅርና አክብሮት ላላቸው ሙስሊሞች ከፍተኛ ጥያቄ ማስነሳት አለበት፡፡ እስልምና መቼ ነው ለሰው ልጅ እርህራሄ የሚያደርገው? እስልምና የሰላም የፍትህ የነፃነት እምነት መሆኑን ለመሆኑ መቼ ነው በተግባር የሚያሳየው? ከዚህ በፊት እንዲሁም አሁንም በምንኖርበት ዘመን ስላላደረገ ወደ ፊት ያደርጋል ለማለት አይቻልም፡፡
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ