አጫጭር ዜናዎች

ሁሉንም ቤተ ክርስቲያን ደምስሱ!!

የሳውዲ ታላቁ የእስልምና ህግ አዋቂ በክርስትና ላይ ሲያነጣጥር የኦባማን ዝምታ! የዋሽንግተን ፖስት አርብ ማርች 16, 2012  በዋና ርእስነት አቅርቦታል።

ጳጳሱ በአውሮጳ ያሉት ሁሉም መስጊዶች ይደምሰሱ ቢል ከፍተኛ ውግዘት ይሰማ ነበር። የዜና አውታሮችም ማብራሪያን ለማግኘት ቤተክርስቲያኒቱን ያዋክቡ ነበር። ኋይት ሃውስ ጉዳዩ አስጊ መሆኑን የሚገልጽ መግለጫ ለማውጣት ሲጣደፍ፥ በመካከለኛው ያሉ ረብሸኞች በሀዘን ራሳቸውን ይገድሉ ነበር። በተቃሪኒው  በእስልምና አለም ከፍተኛ ተደማጭነት ያለው የህግ አዋቂና መሪ ሁሉም ቤተ ክርስቲያን ይደምስሱ ብሎ ትእዛዝ ሲያስተላልፍ  የታየው ዝምታ ግን አስደንጋጭ ነው።

ሼክ አብዱል አዚዝ ቢን አብዱላህ  የሳውዲ ታላቁ የእስልምና ህግ አዋቂ  በማርች 12, 2012  በአካባቢው  የእስላም አገሮች ቤተ ክርስቲያን እንዳይታነጽ የሚከለክል ህግን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ሲመልስ የተናገረው፡ «በክልሉ ያሉትን ሁሉንም ቤተ ክርስቲያናት መደምስስ አስፈላጊ ነው» በማለት ነበር። እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰበትም ምክንያት ነቢዩ መሐመድ ከመሞቱ በፊት በአልጋ ላይ እያለ «በአረብ ምደረ ሰላጤ ሁለት ዓይነት ሃይማኖቶች አይኖሩም» ብሎ ባወጀው ታሪክ ላይ እንደሆነ ነው። ይህንንም መሰረት በማድረግ በሳውዲ ቤተክርስቲያን መክፈት ክልክል ነው፤ እስከቅርብ ጊዜ ድረስም ኢይሁዲዎች  ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ ተከልክለው ነበር። የሌላውም እምነት አማኝ  ማምለክ የሚችለው በድብቅ ብቻ ነው።

ይህ የህግ ውሳኔ በእስልምና አለም ከፍተኛ ተደማጭነት ካላቸው መሪዎች አንዱ ከሆኑት ሲሆን፤  በስሩና በአለም ውስጥ ላሉ የእስልምና አማኞች የሚያስተላልፈው መልእክት ቤተ ክርስቲያንን መደምሰስ የተፈቀደ በቻ ሳይሆን ግዴታም መሆኑንም ጭምር ነው።

የኦባማ አስተዳደር ይህን ዓይነት ጠብ ጫሪነት ዝም ማለቱ ጥፋትን በራስ ላይ መጋበዝ ነው። ኋይት ሃውስ እስላሞችን ለመድረስ የእስላም ወዳጅ አገር መሆኑን ለማራመድ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲው በዋናነት አስቀምጧል። የእስልምና አክራሪዎች በክልሉ የተነሳሳዉን የፖለቲካ ማእበል  እየመሩ ነው። ከዉጭው ዓለምም ጋር ያላችውን ግንኙነት እየፈታተሹ ነው። አክራሪ የሻሪያ ህግን እስከየት ድረስ በግዴታ ለመጫን መቻል አለመቻላቸዉን  እየተመለከቱ ነው። ታላቁ የእስልምና ህግ አዋቂ በሚባለው ሰው የተላለፈውን ይህን ዓይነት የጠብ ጫሪነት መልእክት ዝም ማለት ሌሎች ቡድኖች በጭፍን እምነታቸዉ እንዲቀጥሉ፤ ፀረ ክርስቲያን የኃይል እርምጃ ካለምንም ተጠያቂነት እንዲወስዱ ያበረታታቸዋል። 

እስላሙን ዓለም ለመድረስ የተደረገው የኦባማ ጥረት  የተጠበቀውን በጐ ፈቃደኝነት አላመጣም። ይህም የሆነዉ ትክክለኛ አቌም ከመውስድ ይልቅ የተዛባው አመለካከት እንዳለ እንዲቀጥል በማድረጉ ነው። የእስልምናው ዓለም የአመራር አባላት ከዘር ማጥፋት ጋር የሚነፃፀር ሃይማኖትን የማጥፋት  ጥሪ ሲያደርጉ የነፃው ዓለም መሪዎች ምላሽ መስጠት አለባቸው ካልሆነ ግን በመከተል የሚመጣውን ጭቆና ህጋዊ የማድረግ አደጋ ላይ መውደቃቸው አይቀርም። የእስልምናው ሕግ አዋቂ እንዲወደን ኋይት ሃውስ ፍላጐት ቢኖረውም እንኳን ሕግ አዋቂው ለሚናገረው ነገር አሜሪካ በጭራሽ አታጐነብስም፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

The Washington Times Friday, March 16, 2012 ቀርቦ የነበረው የዜና ትንታኔ የሚያሳየው አስገራሚ እውነታ ለአንባቢ ሁሉ በጣም ግልጥ ነው፡፡ የሙስሊም ሕግ አዋቂዎችና አስተማሪዎች ለሌላው እምነት ተከታይ እና ለሰው ልጅ የሰብዓዊ መብት ማለትም የፈለገውን እምነት የመከተል መብቱ ተቃራኒ የሆነ አቋም እንዳለቸው ያሳያል፡፡

ከዚህም የተነሳ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙት ክርስትያኖች እጅግ አሰቃቂ በሆነ መከራ ውስጥ ይገኛሉ፣ በአሁኑ ጊዜ የሚታየው የአረብ አገሮች ሰንሰለታዊ የሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በከፊልና በሚስጢር ያነጣጠረው በክርስትያኖችም ላይ ነው፡፡ ከላይ የቀረበውን የእስላም ሕግ አዋቂ አስተያየት አስመልክቶ የበርናባስ ፈንድ ባወጣው ዘገባ ላይ በክርስትያኖች ላይ የሚደርሰው ስቃይ የተነሳሳው በኩዌቱ ሚኒስቴር በኦሳማ አል-ሙናዋር አማካኝነት እንደሆነ ነው፡፡ እርሱም ከአገሪቱ ውስጥ ቤተክርስትያናትን ሁሉ ለማስወገድ የሚያስችልን ዕቅድ ለፓርላማ እንደሚያስገባ ነበር፡፡ ጥቂት ቆይቶ እንደተናገረው ደግሞ ያሉት ቤተክርስትያናት አይነኩም ነገር ግን እስላማዊ ያልሆነ ቤተ እምነት እንዳይገነባ ይከለከላል በማለት ነው፡፡

የሙስሊሙ ዓለም በክርስትያኖችና በክርስትና እምነት ላይ እንዲህ ዓይነት ጥላቻን ለምን ሊኖረው ቻለ? ክርስትያኖችንና የሌላውን እምነት ተከታዮች ማሳደድና የፈለጉትን የማምለክ የሰብዓዊ መብታቸውን እንዳይጠቀሙ ማድረግ ለምን አስፈለገ? በሙስሊም አገሮች ውስጥ ሰዎች የሚፈለጉትን ለምን የማምለክ መብት አይኖራቸውም? የመሳሰሉት ጥያቄዎች በአንባቢዎቻችን ሁሉ ሊጠየቁ የሚገባቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡

የሙስሊሙ ዓለም መሪዎች በየጊዜው ለሚያደርሱት አሰቃቂ ስደት የምዕራቡ ዓለም ጆሮ ዳባ ልበስ እንዳለ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚል ይመስላችኋልን? የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆች ግን እግዚአብሔር ዝም እንደማይል እንደሚፈርድ ፍርዱም ብዙም እንደማይርቅ ያምናሉ፡፡ በዚህም እምነት ላይ በመሆን ለአንባቢዎቻች ሁሉ የሚያቀርቡት ጥሪ ወደ እግዚአብሔርን መልካምነት እንዲመጡና በክርስቶስ በኩል ከእርሱ እጅ ይቅርታንና አዲስ ሕይወትን እንዲቀበሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ: EDITORIAL: Destroy all churches

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ