አዳዲስ መረጃዎች
የካቲት 7፣ 2007 (14 February 2015)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለብዙ ዓመታት መምህር የነበሩት ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ሞገስ ብዙ መጻሕፍትን የጻፉ ምሁር ናቸው፡፡ ጽሑፎቻቸው በምርምር የተደገፉና ብዙ እውነታዎችን ስላነፀባረቁ ብዙዎች ተጠቅመውባቸዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ከጻፏቸው መካከል ይህ ለምን አልሰለምኩም በአሁኑ ጊዜ ያለውን አንገብጋቢ ዓለም አቀፍ ጥያቄ የሚመለከት ነውና ለብዙዎች ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጥ አምነንበታል፡፡ ስለሆን በዚህ ድረገፅ በተከታታይ ለአንባቢዎች የምናቀርበው ሲሆን በዚህ በዛሬው ገፅ ላይ መቅድሙንና መግቢያውን አቅርበናል፡፡
እስልምናና ሽብርተኝነት በሚል ርዕስ በማርክ ኤ. ገብርኤል የተጻፈው መጽሐፍ የእስልምናን እምነት ምንነት ለመረዳት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ ጸሐፊው ማርክ ገብርኤል በእስልምና እምነት ውስጥ ያደገ፣ በግብፅ ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲ በእስልምና እምነት ጥልቅ ትምህርት ተምሮ እስልምናን ያስተምር የነበረ ብቻ ሳይሆን በመስጊድ ውስጥም እምነቱን በኢማምነት ያገለግል ነበር፡፡ በዚህ በምዕራፍ ሦስት ውስጥ የጌታ ኢየሱስ ተከታይ ሊሆን እንዴት እንደበቃ ግዚአብሔር በምህረቱ እንዴት እንደረዳውና ያጋጠመውን ችግሮች ከችግሮችም እንዴት እንደተረፈ ጸሐፊው ያቀርብልናል፡፡
ጥቅምት 15፣ 2007 (25 October 2014)
እስልምናና ሽብርተኝነት በሚል ርዕስ በማርክ ኤ. ገብርኤል የተጻፈው መጽሐፍ የእስልምናን እምነት ምንነት ለመረዳት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ ጸሐፊው ማርክ ገብርኤል በእስልምና እምነት ውስጥ ያደገ፣ በግብፅ ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲ በእስልምና እምነት ጥልቅ ትምህርት ተምሮ እስልምናን ያስተምር የነበረ ብቻ ሳይሆን በመስጊድ ውስጥም እምነቱን በኢማምነት ያገለግል ነበር፡፡ በዚህ በምዕራፍ ሁለት ውስጥ እስልምናን በመጠራጠሩ ብቻ በግል ሕይወቱ ላይ የደረሰውን ግፍ ያስነብበናል፡፡
ጥቅምት 2፣ 2007 (12 October 2014)
እስልምናና ሽብርተኝነት በሚል ርዕስ በማርክ ኤ. ገብርኤል የተጻፈው መጽሐፍ የእስልምናን እምነት ምንነት ለመረዳት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው፡፡ ጸሐፊው ማርክ ገብርኤል በእስልምና እምነት ውስጥ ያደገ፣ በግብፅ ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲ በእስልምና እምነት ጥልቅ ትምህርት ተምሮ እስልምናን ያስተምር የነበረ ሰው ነው፡፡ ጸሐፊው የእስልምናን እውነተኛ ምንነትና በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን ዙሪያ የሚከናወኑት የሽብርተኝነት፣ ጭካኔ የተሞላባቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ከእስልምና እምነት ጋር የተያያዙት ለምን እንደሆነ ያስረዳናል፡፡
ህዳር 23፣ 2006 (02 December 2013)
በተለያዩ ቦታዎችና ክፍለ አገሮች መስጊዶች በብዛት ይገነባሉ፡፡ ግንባታቸውም ጥራት ያለውና ከሌሎች ሃይማኖት ግንባታዎች ልቀውና ከፍ ብለው እንዲታዩም ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡ በባልታዛር እና አብደናጎ የተጻፈው መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና ጥናታዊ ጽሑፍ የመስጊዶችን ሚናና ተፅዕኖን ከማጠቃለያ ሃሳብ ጋር በግሩም ሁኔታ አቅርቦልናል፡፡
ህዳር 10፣ 2006 (19 November 2013)
በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ መስጊዶች እንቅስቃሴና ሚና በእስልምና አገራት ውስጥ ካሉት በጣም ይለያሉ፡፡ የዚህን መሰረታዊ እውነታ ምክንያቶቹን የሚዘረዝረው ክፍል አምስት የዲህሚንም Dhimmi ምንነት አብራርቷል፡፡
ህዳር 3፣ 2006 (12 November 2013)
በመስጊዶች ውስጥ ለሚደረጉት ድርጊቶች መሪዎቹ መርሆዎች ምንድናቸው? “መስጊድ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና” ጸሐፊዎች ባጠኑት ጥናት ውስጥ ጅሀድ አንዱ አንቀሳቃሽ መርህ፣ ሲሆን ሌላው ደግሞ የታቂያ “taqiyya’ መርሆ ነው፡፡ ይህ ክፍል አራት በመስጊዶች ውስጥ የሚሰሩትን እነዚህን ሁለት መርሆዎች በመጠኑ ያሳየናል፡፡
ባለፈው ሳምንት በWORLD News Service የቀረበው ዘገባ በኢራን ውስጥ በክርስትያኖች ላይ የሚደርሰውን የማያቋርጥ የግፍ ጥቃት መጠነኛ እይታ ፈንጥቋል፡፡ ብዙ ፓስተሮች እና አማኞች ክርስትያን መሆናቸው ወንጀል ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የብዙዎች ልጆች ከወላጆቻቸው ተነጥለዋል፣ የአንዳንዶች መታሰር አለም አቀፍ ትኩረት ሲሰጠው ብዙዎች ግን ማንም ሳያውቅ ይሰቃያሉ፡፡
ጥቅምት 23፣ 2006 (2 November 2013)
መስጊዶች ውስጥ እንዲከናወን የታቀደው ምንድነው? ይህ ክፍል ሦስት ታሪካዊ መስጊዳዊ እንቅስቃሴዎችን አቅርቦልን፣ የሸሪዓ ሕግ፣ እንዲሁም እስላማዊ ምሁራን ስለመስጊድ ሚና የሚናገሩትን ያሳየናል፡፡
Religion Today የሚባለው የድረ ገፅ ዜና ጋዜጣ ባለፈው ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን ያቀረበው ዜና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ በግብፅ ዋና ከተማ በካይሮ ውስጥ ጊዛ በሚባለው ስፍራ ባለችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የጋብቻ ስርዓት ሲፈፀም ደስታቸውን ለመግለፅ በተሰበሰቡት ሰዎች ላይ የጥይት እሩምታ ተከፈተባቸው አራት ሰዎች ሞቱ፡፡ www.religiontoday.com/blog/traumatized-survivors-wedding-attack-egypt-look-to-god.html ሙስሊሞች ሰላማዊ ሰዎችን ለምን ያጠቃሉ?
ጥቅምት 15፣ 2006 (25 October 2013)
መስጊድ ምንድነው? የሙስሊሞች መስጊድና የክርስትያኖች ቤተክርስትያን ዓላማና ተግባር ይመሳሰላልን? በመስጊዶች ውስጥ የሚከናወኑት ተግባራት የሚያካትቱት ምንድነው? ይህ ክፍል ሁለት መስጊድን በተመለከተ ልናውቅ የሚገቡንን ነገሮች በመጠቆም በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
በAsiaNews.it የድረ ገፅ ጋዜጣ ላይ የቀረበው Anti-Christian violence and the silence of "moderate" Muslims የሚለው ርዕስ በዓለም ላይ ሙስሊሞች በሰላማዊ ክርስትያኖች ላይ እያደረሱት ስላለው ጥቃት መጠነኛ ዘገባን አቅርቦ፣ ሰላማዊ ነን የሚሉ ሙስሊሞች ታዲያ ለምን ዝም አሉ? የሚል ጥያቄን ያቀርባል፡፡ ሞድሬት ወይንም ሰላማዊ ሙስሊሞች በእርግጥ ለምን ዝም አሉ?
ጥቅምት 9፣ 2006 (19 October 2013)
ከ1930ዎቹ ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ ተከናውኖ የነበረውን ታሪካዊ የጥቁር ሙስሊሞቸ እንቅስቃሴ Black Muslims and the Nation of Islam በሚል ርዕስ በሚከተለው ድረ ገፅ ላይ፡ www.apologeticspress.org/APContent.aspx ዶ/ር Brad Bromling, በመጠኑ አቅርቦታል፡፡ ታሪኩ የሚገርም ከመሆኑም ባሻገር በአሁኑ ጊዜም እየተከናወኑ ስላሉት ብዙ ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች መሰረታዊና ታሪካዊ ፍንጭን ይሰጣል፡፡
The Mosque and its Role in Society በሚል ርዕስ በተጻፈው ትንሽ መጽሐፍ ውስጥ ጸሐፊዎቹ የእስልምና እምነት በሕይወት ላይ ስላለው አጠቃላይ ግንዛቤ ጠቅለል ያሉ ጭብጦችን አቅርበዋል፡፡ እስልምና በእግርጥ ሃይማኖት ብቻ ነውን? ለሚለውም ጥያቄ መሰረታዊና አስገራሚ መልሶችን ፈንጥቀዋል፡፡
ጥቅምት 5፣ 2006 (15 October 2013)
በተከታታይ የምናቀርበውና The Mosque and its Role in Society በሚል ርዕስ የተጻፈው ትንሽ መጽሐፍ መቅድምና መግቢያ ጸሐፊዎቹ ስለመስጊድ በጥልቀት ያጠኑትንና በተከታታይ ስለምናቀርበው እውነታ ፍንጮችን ለመጠቆም የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡ ስለ ሙስሊሞች መስጊድና በውስጦቻቸው ስለሚከናወኑት እንቅስቃሴዎች የምውቀው ምንያህል ነው? ከዚህ መግቢያ ቀጥሎ በተከታታይ የሚቀርቡትን ጽሑፎች ማንበብ በሕይወታችን ውስጥ ለምንወስደው እርምጃ መሰረታዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
መጋቢት 11፣ 2005 (20 March 2013)
“እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ” በሚለው ዓምድ ውስጥ ታሪካዊ ነገሮችን እያቀረብን ነው፡፡ እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ ምን ይመስል ነበር? የሚለውን ጥያቄ መጠየቅና ቆም ብሎ ማሰብ ከሁላችንም የሚጠበቅ ነው፡፡ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጣሊያን አገሪቱን በወረረችበት ጊዜ የብዙ ንፁሃን ደም ፈሶ ነበር፡፡ ፋሽስት ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን ሲወጋ እራሱን ያቀረበው “በኢትዮጵያ የእስልምና አዳኝና ጠባቂ” አድርጎ ነበር፡፡ በፕሮፌሰር ኤርሊች መጽሐፍ “የሙሶሊኒ ግመሎች” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ያንን ትምህርታዊ ታሪክ ርዕሱን እንደያዘ አቀናብረው አዘጋጆቹ አቅርበውታል፡፡
በThe Jerusalem Post ጋዜጣ ላይ የወጣው Islam’s path to Africa የMICHAEL WIDLANSKI www.jpost.com/Opinion/Op-EdContributors/Article.aspx ጽሑፍ እስልምና በአፍሪካ ውስጥ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በጥቂቱ የቃኘና መጪው የአፍሪካ ክፍለ ዓለም ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ነው፡፡ ክፍለ አህጉራችን አፍሪካ የእስምና መናኸሪያ አገር ልትሆን ነውን?
ጥቅምት 18፣ 2005 (28 October 2012)
ቁርአንና ታሪክ የሚለው ጽሑፍ በአምስት ቁርአናዊ ነጥቦች ላይ ተመስርቶ የተቀናበረ ጽሑፍ ነው፡፡ አምስቱ ታሪክ ጠቀስ የቁርአን ዘገባዎች ከታሪክ ከተፈጥሮ እውነታ በመነሳት ምን ግንዛቤ ሊኖራቸው እንደሚችል እንዲሁም ቁርአን ምን ዓይነት ጽሑፍ እንደሆነ አንባቢዎች እንዲገነዘቡ የሚጠቁሙ ናቸው፡፡
ጥቅምት 11፣ 2005 (21 October 2012)
በታዋቂው የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ኤሪሊች ሃጋይ በ2007 ከተጻፈውና Saudi Arabia & Ethiopia [ISLAM, CHRISTIANITY & POLITICS ENTWINED] ከተሰኘው መጽሐፍ ምዕራፍ አንድ ላይ የተቀናበረ ታሪካዊ ጽሑፍ፡፡
በWashington, D.C. የሚገኘው International Christian Concern፤ September 28. 2012 ባወጣው ዜና ላይ አሰቃቂ የሆነ የአንድ ልጃገረድን ደፈራ ዘግቧል፡፡ ይህ በፓኪስታን ክርስትያን ልጆች ላይ የሚደረገው ግፍ እና ወንጀል በጣም አሳዛኝና የልጆቹን ሕይወት የሚያበላሽ ለቤተሰቦች ልብን የሚሰብር ጉዳይ ነው፡፡
መስከረም 15፣ 2005 (25 September 2012)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅራኔ ናቸው ተብለው ከቀረቡት 101 ጥቅሶች ውስጥ ይህ ክፍል ስድስት ዘጠኙንና ከጥያቄ 31-39 ያሉትን ያቀርብልናል፡፡
በርናባስ ፈንድ በነሐሴ 29 ዘገባው ያቀረበውና በግብፅ እየሆነ ያለው ነገር አስፈሪ ነው፡፡ የግብፅ ክርስትያኖች ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚደርስባቸው መከራ ዘግናኝ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ማለቂያ የሌለው እየሆነ መሄዱንም የሚያመላክት ነው፡፡
ነሃሴ 26፣ 2004 (1 September 2012)
በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የነበረው የሙስሊሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ የጀርባ መነሻው ምንድነው? ኢትዮጵያውያንስ ሊመለከቱት የሚገባቸው እንዴት ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ እስልምናን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም በጣም ጠቃሚ ሆኖ ያገኘነው ታሪክ የነፕሮፌሰር ኤርሊች የታሪክ ምርምር ነው፡፡ የቅርቡ ጆርናላቸው ላይ የወጣው ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ ምንነት እንድንመለከት የሚያደርግ ዓይን ከፋች ስለሆነ ለአንባቢዎች እንዲመች አቀናብረን በዚህ ክፍል ሁለት አቅርበነዋል፡፡
እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው ዓምድ ውስጥ፣ ታሪክን አስመልክቶ በየጊዜው ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጥረት ይደረጋል፡፡ በዚህ በክፍል ሦስት የነፕሮፌሰር ኤርሊች ጆርናል ያቀረበው በሁለቱ እስላማዊ ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ያሉትን መሰረታዊ የእምነት ልዩነቶችን ነው፡፡ ይህም አሁን ስላለው የእስላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተጨባጭ ሁኔታና ገፅታ እውነቱን እንድንገነዘብ ይጠቅማል፡፡
The Christian Science Monitor; በ12 August 2012፣ ያወጣውን ዘገባ ጠቅሶ ICC ያቀረበው ዜና ብዙዎችን ያስደነገጠ ሌላው የእስልምና ገሃድ እውነታ ነው፡፡ የአዕምሮ ዘገምተኛዋን ቁርአንን አቃጥላለች ተብላ በአስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ የምትገኝበትን ሁኔታ ከተከታዩ የICC አስቸኳይ ዘገባ ጭምር ለአንባቢዎች ቀርቧል፡፡
ነሃሴ 12፣ 2004 (18 August 2012)
“እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ” ዓምድ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ታሪካዊ ጀርባ ምን እንደሆነ ለማሳየት የተዘጋጀ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እስልምናን በታሪክ ውስጥ እንዴት አስተናገደችው፣ ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር እንዴት ኖረች? የእስልምና ተከታዮችስ በዚች አገር ውስጥ እንዴት ነው የኖሩት? በኢትዮጵያ በታሪክ ሙስሊሞች ምን ዓይነት ሚና ተጫወቱ፣ የነበራቸው አመለካከትና እንዲሁም እንቅስቃሴ ምን ይመስል ነበር? የዚህ ዘመን ሙስሊሞችስ አመለካከትና እንቅስቃሴ ከታሪካዊና ወቅታዊ እውነቶች አኳያ እንዴት ነው ሊገመገም የሚችለው? የሚሉ ሐሳቦችን በዚህ ዓምድ ስር ለማሳየት እንሞክራለን::
International Christian Concern በሐምሌ 6 እንደ ዮሮፕ አቆጣጠር ባወጣው ዜና ላይ በአፍሪካ ክርስትያኖች ላይ ስለሚደርሰው ከፍተኛና የተቀነባበረ ጥቃት አቅርቧል፡፡ ይህ ዓይነቱ ጥቃት ስለምን አስፈለገ የአፍሪካ ክርስትያኖችስ የወደፊት ምን ይሆን?
ሃምሌ 17፣ 2004 (23 July 2012)
የመጽሐፍ ቅዱስ የእርስ በእርስ ቅራኔዎች ከሚባሉት ውስጥ ያሉትን ሰባቱንና በአብዛኛው ከሰዎች ስሞች ጋር የተያያዙትን በተመለከተ ለሚጠየቁት ጥያቄዎች ሎጂካል መልሶችን በዚህ በክፍል አምስት ውስጥ እናገኛለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የመጣ መገለጥ በመሆኑ ምንም ስህተት የሌለበት መሆኑንም ያሳዩናል፡፡
ሃምሌ 8፣ 2004 (14 July 2012)
በቁርአን ውስጥ ምንም የእርስ በእርስ ቅራኔ እንደሌለ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ይህ እውነት ነውን? በቁርአንን ውስጥ ያለውን መልእክት በጥንቃቄ ለመረዳትና ከእርሱም ውስጥ ትምህርት ለመውሰድ የሚመኝ ማንኛውም ሰው ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ጥያቄ የሚፈጥሩ ቅራኔዎችን ማግኘቱ አይቀርም፡፡ ቁርአን የተቃርኖዎች መጽሐፍ የሚለው ጽሑፍ ጥቂቶቹን ተቃርኖዎች ያሳየናል፡፡
ለቃላቶቹ ለዋጭ የለም በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ፣ የእግዚአብሔር ቃል የማይለወጥ መሆኑን የሚያስረዳና በዚህም መርሆ መሰረት ቁርአን እና መጽሐፍ ቅዱስ ሲመረመሩ ምን እንደሚጠቁም ትልቅ ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡
የቱርክ የዴይሊ ኒውስ አምደኛ BURAK BEKDİL ያቀረበው እስልምና ስለምን መድበለ ፓርቲ ሊሆን አይችልም የሚለው ጽሑፍ ለብዙዎች ድብቅ የሚመስለውን የፖለቲካዊ እስልምናን ምንነት እጥር ምጥን ባለ መንገድ ያሳያል፡፡
ሰኔ 10፣ 2004 (17 June 2012)
‘‘እስልምና በኢትዮጵያ ውስጥ ከየት ወዴት?” በዳንኤል የተቀናበረው ይህ ጽሑፍ፣ በአገሪቱ ውስጥ በቅርቡ የተነሳውን የሙስሊሞችን የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ አጠቃላይ እይታ እንዲኖረንና ክርስትያኖችም ሆኑ ሌሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያሳያል፡፡
ሰኔ 3፣ 2004 (10 June 2012)
በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት መካከል አሉ የሚባሉትን ልዩነቶች እንዲሁም ቅራኔዎች የሚመስሉ ነገሮችን በመጠቀም መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥቃት የተሰለፉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን ለመመለስ የተዘጋጀው ይህ አራተኛው ክፍል ልዩነቶች ከሚባሉት ውስጥ በቁጥሮች ላይ ያተኮሩትን በማንሳት አስገራሚ የሆነ ሎጂካዊ መልሶችን ያሳየናል፡፡
የጋርዲያን ዜና ጋዜጣ ኢራን ውስጥ በክርስትያኖች እና በሌሎችም ላይ ስለሚደርሰው ስደትና ግፍ ያቀረበው የሚያዝያ 25 ዘገባ ታዋቂው ጠበቃ፣ ለሰዎች በመከራከሩ ዘጠኝ ዓመት እስራት እንደተፈረደት ነው፣ ይህ ዜና በእስላማዊ አገሮች ሁሉ ስለሚሆነው ነገር ጥቆማን ይሰጠናል፡፡
መያዝያ 27፣ 2004 (5 May 2012)
በቁርአን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ነገሮች አስገራሚነታቸው እያደር እየተገለጠ ነው፡፡ ጉንዳን ስትናገር ንጉሱ ሰለሞን ሰምቶ ፈገግ ማለቱን በተመለከተ የተደረገውን እሰጥ አገባ አዘጋጁ በአጭሩ አቅርቦታል፡፡ ይሁን እንጂ ከጽሑፉ የሚታየው እውነታ ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10.26 ላይ “... የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።” በማለት የተናገረውን በትክክል ያሳየናል፡፡
በርናባስ ፈንድ በማክሰኞ 24 ኤፕሪሊ 2012 ዜናው ላይ በኢራን ስለሚካሄደው ታሪካዊ የሆኑ የክርስትና ቅርሶችን የማጥፋት እንቅስቃሴ እንደሚከተለው አቅርቦአል::
መያዝያ 23፣ 2004 (29 April 2012)
መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ ቅራኔ እንዳለው በመናገር ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ለሕወታቸው ዘላለማዊ ጠቀሜታን እንዳያገኙ የሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ ነው፡፡ አሉ ለሚባሉት 101 እርስ በእርስ ቅራኔዎች ሎጂካዊ መልስን ለመስጠት የተዘጋጀው ይህ ክፍል ሦስት ለስድስቱ ጥያቄዎች ሎጂካዊ መልሶችን ይዞልን ቀርቧል፡፡
እንደ ዮሮፓውያን አቆጣጠር በሚያዝያ 5 ቀን የወጣው የInternational Christian Concern (ICC) አስቸኳይ ዜና በግብፅ በ17 ዓመት ወጣት ልጅ ላይ ስለተፈረደው የሦስት ዓመት እስራት ፍርድ ዘገባን አቅርቧል፡፡
በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ክርስትያኖች እየተደረገ ያለው ግፍ አሰቃቂ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ተወላጆችና በሰው ልጅ መብት መጠበቅ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ስለምን ዝም አሉ? ይህ የICC ዜና በሁኔታው ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ እንዴት ዝም እንዳለ በመገረም ያሰየናል፡፡ አዘጋጁም በመደምደሚያው ላይ ስለ እውነተኛው መታሰር መጠነኛ መግለጫ አቅርቧል፡፡
መያዝያ 5፣ 2004 (13 April 2012)
ክርስትያን ፖስት በማርች 28 ያቀረበው ዜና ላይ የኩዌት ተወላጅ በትዊተር ላይ አቀረበ የተባለውን አስላማዊ ዘለፋና ያጋጠመውን ከባድ ችግር ነበር፡፡ በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት፣ የመናገር መብት እና የሃይማኖት ነፃነት የመሳሰሉትን በግልፅ ያሳያል፡፡
መያዝያ 4፣ 2004 (12 April 2012)
የክርስትያን ማዕከላዊ መልእክት ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቁና የኃጢአት ይቅርታን እንዲያገኙ በተከፈለው ዋጋ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የሚቻል የተደረገው በጌታ ኢየሱስ የመስቀል ሞት አማካኝነት ነው፡፡ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶ የመስዋዕትነት ለምን እንደነበረና “እርሱም የታረደው በግ” ተብሎ መጠራት ለምን እንዳስፈለገው ይች አጭር ጽሑፍ ታስረዳናለች፡፡
መጋቢት 23፣ 2004 (1 April 2012)
በ The Washington Times Friday, March 16, 2012 ያቀረበው ዜና በሙስሊሙ ዓለም እያደር በመንፀባረቅ ላይ ያለውን ሰብዓዊ መብት ረገጣ ነው፡፡ የሙስሊም ሕግ አዋቂዎች በክርስትና ላይ ያላቸውን ጥላቻ በግልፅ ሲናገሩ የታላላቅ ዲሞክራሲ አገራት፤ በተለይም የኦባማ አስተዳደር ዝምታ አስገርሞታል፡፡
ብዙ ሙስሊሞችና መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ የማያምኑ ሊበራሎች መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ የሚቃረን መጽሐፍ ነው ይሉንና አንዳንድ የሚቃረኑ የሚመስሉ ጥቅሶችን ይጠቅሱልናል፡፡ ይህንን በተመለከተ ‘101 Cleared up contradictions in the Bible’ ከተባለውና በአራት ጸሐፊዎች ከተዘጋጀው ጽሑፍ ውስጥ ቅራኔ ለሚመስሉት ለአምስቱ የመጀመሪያ ጥቅሶች የማብራሪያ ምላሾች በዚህ ጽሑፍ ክፍል ሁለት ቀርበዋል፡፡
መጋቢት 9፣ 2004 (18 March 2012)
ብዙ ሙስሊሞች በተደጋጋሚ ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች ውስጥ ዋነኛው ያነጣጠረው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ የሚቃረን መጽሐፍ ነው ይሉንና አንዳንድ የሚቃረኑ የሚመስሉ ጥቅሶችን ይጠቅሱልናል፡፡ ይህንን በተመለከተ ‘101 Cleared up contradictions in the Bible’ የተባለውና በአራት ጸሐፊዎች የተዘጋጀው ጽሑፍ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ ስለሚባሉት 101 የእርስ በእርስ ቅራኔዎች አስገራሚ መልስን ይሰጣል፡፡
ታህሳስ 16፣ 2004 (26 December 2011)
በስድስት የቁርአን ጥቅሶች ውስጥ ባሉትና “በጣም ትንሽ” ነገርን ለመግለጥ በተጠቀሱት ቃላት ላይ ተመስርተው፤ “ቁርአን “ስለአቶም” በጥንት ጊዜ የተናገረ መጽሐፍ ነው፡፡” ስለዚህም ሳይንሳዊ ትንቢት ያለበትና ከአምላክ የመጣ ለመሆኑ ማስረጃ ነው በማለት ለሚከራከሩት ሙስሊሞች `Does the Qur'an Speak about Atoms?’ በሚል ርዕስ በJochen Katz የቀረበው መልስ ጥሩ ትምህርት ሰጪ ነው፡፡
ታህሳስ 2፣ 2004 (12 December 2011)
በአሁኑ ጊዜ ዘመናዊ ሳይንስ በቁርአን ውስጥ ይገኛል የሚል ፈጣን የፕሮፓጋንዳ እንቅስቃሴ በሙስሊሞች ዘንድ ይታያል፡፡ ዋና ዓላማው ቁርአን ከአምላክ የመጣ መሆን አለበትና ወደ እስልምና እምነት ኑ የሚል ነው፡፡ Can "Modern Science" be found in the Qur’an? በሚል ርዕስ በAndy Bannister የቀረበው ጽሑፍ ይህ ምን ያህል ትክክል እንዳልሆነ በስድስት ነጥቦች ውስጥ ያሳየናል፡፡
ህዳር 18፣ 2004 (28 November 2011)
በ1969 ጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጠው ኒል አርምስትሮንግ ሙስሊም ሆነ ተብሎ የተነዛው የፈጠራ ወሬ በብዙ የእስላም አገሮች ጋዜጦች ላይ ለንባብ ቀርቦ ነበር፡፡ ይህ የፈጠራ ወሬ ከተስተባበለ በኋላ አሁንም፣ አሁንም ለሙስሊሞች እንደ እውነት ይቀርባል፡፡ ይህ How Neil Armstrong "became" a Muslim በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ ከበርካታ ማስረጃዎች ጋር ዜናው የውሸት ፈጠራ እንደነበረ ያስረዳናል፡፡
ህዳር 16፣ 2004 (26 November 2011)
ቁርአን ብዙ የሆኑ ሳይንሳዊ ተዓምራቶች እንዳሉት ይነገራል ከእነዚህም መካከል ወደ ጨረቃ ስለሚደረገው ጉዞ ተነገረ የሚባለው ትንቢትና በቁርአን 84.16-21 ላይ ያለው ዋነኛው ነው፡፡ ይህን በተመለከተ Jochen Katz “And the Moon remains … out of reach;How an Islamic dawah miracle self-destructs’ በሚል ርዕስ ያቀረበው ጽሑፍ አስገራሚ ነው፡፡
ህዳር 3፣ 2004 (13 November 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ ስድስት ክፍል ሁለት መሐመድ የእምነቱንና የቁርአንን የተለያዩ ምንጮች እንዴት እንደተጠቀመባቸው አሳይቶን፤ እስልምና ምን ማለት እንደሆነ የምትገልጥ ጥቂት አረፍተ ነገሮችን በያዘች አንዲት አጭር አንቀፅ ያጠቃልላል፡፡
ጥቅምት 25፣ 2004 (5 November 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ ስድስት ክፍል አንድ ከመሐመድ ቀደም ብለው በአረቢያ የሃይማኖት ለውጥ ለማምጣት ተነስተው ስለነበሩት የተሐድሶ መሪዎች መጠነኛ ታሪክ አቅርቦልናል፡፡ የተሐድሶ መሪዎቹ ትምህርትና አመለካከት በቁርአን እንዲሁም በእስልምና እምነት ላይ ያመጣው ተፅዕኖ አስገራሚ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የእምነቱንና የመጽሐፉን ምንጭ ምንነት በግልጥ ያሳየናል፡፡
ጥቅምት 4፣ 2004 (15 October 2011)
በBrother Banda የተጻፈውና An African Asks Some Disturbing Questions of Islam የሚለው ጽሑፍ በአፍሪካና በዓለምም ሁሉ ውስጥ አነጋጋሪ ስለሆነው የባሪያ ንግድ ዋና ተዋናይ ማን እንደሆነና ዘረኝነትንም በዋናነት የሚያካሂደውን ሃይማኖት ግልፅ በሆነ መንገድ ያስቀምጣል፡፡
ነሃሴ 26፣ 2003 (28 August 2011)
የጆን ጊልክራይስት መጽሐፍ ምዕራፍ አንድ ክፍል አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተዓማኒነትን ከጥንታዊና ታሪካዊ ጽሐፎች ላይ እያቀረበ ቁርአን ግን ማስረጃ የሌለው ብቻ ሳይሆን የራሱን የመጀመሪያ ጽሑፎች ማቃጠሉንና ማስረጃ ማጥፋቱን ያሳየናል፡፡
ነሃሴ 20፣ 2003 (22 August 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አምስት ክፍል ሦስት ስለመሐመድ ብርሃን፣ የሙታን ድልድይና ከፐርሺያ እምነት የተወሰዱ ሌሎች ሐሳቦችን ያሳየናል፡፡
ግንቦት 27፣ 2003 (04 June 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አምስት ክፍል ሁለት ስለገነት (መንግስተ ሰማይን) እና ስለሰይጣን በቁርአን ውስጥ የተነገሩት ነገሮች ምንጭ በጥንታዊ ፐርሺያ የነበረው የዞሮአስተርያን እምነት መሆኑን ያሳየናል፡፡
ግንቦት 14፣ 2003 (22 May 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አምስት በጥንት ፐርሺያ የነበረው የዞሮአስተርያን እምነት በቁርአን ውስጥ ስላሳደረው ተፅዕኖ አስገራሚ እውነታዎችን ያሳየናል፡፡ ምዕራፍ አምስት ክፍል አንድ አጠቃላይ መግለጫዎችንና ስለ መሐመድ ወደ ሰማይ መጓዝ ታሪክ ያቀርባል፡፡
መያዝያ 1፣ 2003 (9 April 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አራት ክፍል አምስት፣ በአምስት የተለያዩ ንዑስ ርዕሶች ማለትም በአዳም ሐዘን፣ ሲዖል በሚሄዱት ሰዎች፣ በነፍሳት ሚዛንና በቀሪዎቹ ላይ ክርስትያናዊ የሆኑ ምንጮች የመሐመዳውያንን እምነት እንዴት ቅርፅ እንደሰጡት ያሳየናል፡፡
መጋቢት 24፣ 2003 (2 April 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አራት ክፍል አራት መሐመድ የስላሴን ትምህርት፣ የክርስቶስ ኢየሱስን መሰቀልና ለሰው ልጅ የዘላለም ሕይወት የሚሆነውን የደኅንነት መሰረት መካዱ፣ ምንጫቸው የእግዚአብሔር መገለጥ ማለትም ከእግዚአብሔር የመጡ ትምህርቶች ሳይሆኑ ከመሐመድ በፊት በነበሩ የሐሰት አስተማሪዎች የተሰራጩ ስህተቶች መሆናቸውን በግልፅ ያሳየናል::
መጋቢት 11፣ 2003 (20 March 2011)
ቁርአን ተጠብቋልን? (Is the Quran Preserved?)በሚል ርዕስ በKhalid የተዘጋጀው ጽሑፍ ሎጂካዊ በሆነ መንገድ ያቀረበልን እውነታ ስለ ቁርአንና በውስጡ ስለተጠቀሱት ስለቀደሙት የእግዚአብሔር መገለጦች ግሩም እውነታዎችን ያሳየናል፡፡
መጋቢት 4፣ 2003 (13 March 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አራት ክፍል ሦስት በቁርአን ውስጥ የሚገኘው የጌታ ኢየሱስ ታሪክ ምንጩ ከየት እንደሆነ በአስደናቂ ሁኔታ ያቀርብልናል፡፡
የካቲት 5፣ 2003 (12 February 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አራት ክፍል ሁለት በቁርአን 19ና 3 ላይ ስላለው የማርያም ታሪክ ምንጮችን በግሩም ሁኔታ ያቀርብልናል፡፡
ጥር 28፣ 2003 (5 February 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ አራት ክፍል አንድ በምዕራፍ አስራ ስምንት ውስጥ ስላሉት የዋሻውን አንቀላፊ ወጣቶች ታሪክ በማሳየት ስለ ቁርአን ያለንን ግንዛቤ ከፍ እንድናደርግ ይረዳናል፡፡
ጥር 21፣ 2003 (29 January 2011)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የሳቢያንና የአይሁዶች ሐሳቦችና ልማዶች ተፅዕኖዎች: ክፍል አራት ከጭብጥ ታሪካዊ ማስረጃዎች በመነሳት እንድ ሰው ሊደመድም የሚችለው የቁርአን ምንጩ መሠረት የሌላቸው አፈ ታሪኮችና ተረቶች መሆናቸውን ያሳያል፡፡
ተኅሣሥ 22፣ 2003 (31 December 2010)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ ሦስት ክፍል ሦስት የንግስተ ሰባን ታሪክ ቁራናዊ ምንጭና ሃሩትና ማሩት የተባሉትን የሁለቱን መላእክት ታሪክ ምንጭ በሚገርም መንገድ ያቀርብልናል፡፡
ተኅሣሥ 15፣ 2003 (24 December 2010)
መልካም ገና!
ሙስሊሞች የጌታ ኢየሱስን አምላክነት አይቀበሉም፣ ‹ጌታ ኢየሱስ አምላክ ነኝ በማለት ስላልተናገረ አምላክ ነው ማለት ትክክል አይደለም› ይላሉ፡፡ በመሆኑም ክርስትያኖች የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መቀበላቸው ይገርማቸዋል፡፡ ይቺ አጭር ጽሑፍ ጌታ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚጠቁሙ እውነታዎችን በመጠኑ ታሳያለች፡፡
ተኅሣሥ 9፣ 2003 (18 December 2010)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ ሦስት ክፍል ሁለት በቁርአን ውስጥ የተጠቀሱት የአቤልና የቃየል ታሪክን ምንጭ እንዲሁም የአብርሃምን ታሪክ ምንጭ በሚገርም መንገድ ያቀርብልናል፡፡
ጥቅምት 27፣ 2003 (6 November 2010)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ ሦስት ክፍል አንድ በቁርአን ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ስላደረጉት የሳቢያንና የአይሁድ ልማዶችን ያሳየናል፡፡
ጥቅምት 14፣ 2003 (24 October 2010)
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. የተዘጋጀው የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች መጽሐፍ ምዕራፍ ሁለት በቁርአን ውስጥ ስላሉት የጥንታዊ አረቢያ ሃይማኖትና ልማዶች ተፅዕኖ በግልፅ ያሳየናል፡፡
መስከረም 22፣ 2003 (2 October 2010)
የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች የሚለው የREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D. መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ መግቢያውና ሙስሊሞች በአጠቃላይ ቁርአን ከእግዚአብሔር መጣ የሚል እምነት እንዳላቸው የሚናገር ነው፡፡ ሙስሊሞች በሙሉ ያላቸው ይህ እምነትና መረዳት በሐቀኛ ምርመራ በመመሥረት የቁርአን ምንጭ ምንነት መገለጡ መከተል ያለባቸውን አሁኑኑ እንዲያስቡበት በጣም እንደሚረዳቸው ይታመናል፡፡
ስኔ 9፣ 2002 (16 June 2010)
ሴቶች በንፁህ እስልምና በሚል ርዕስ በM. Rafiqul-Haqq and P. Newton የተዘጋጀው ጽሑፍ ክፍል ዘጠኝ ክፍል አስር ደግሞ የሙስሊም ወንዶች ለሚስቶቻቸው የሚሰጡት እርዳታና የቀን ፍጆታ የሚወሰነው ሴቶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ካላቸው ፈቃደኝነት ጋር በተያያዘ መልኩ መሆኑን ይገልጣል፡፡ በእስልምና የሚታመንበትን የሴቶችን መንፈሳዊ አቋምና የመጨረሻ ማጠቃለያ መደምደሚያን ያቀርባል፡፡
ስኔ 5፣ 2002 (12 June 2010)
ሴቶች በንፁህ እስልምና በሚል ርዕስ በM. Rafiqul-Haqq and P. Newton የተዘጋጀው ጽሑፍ ክፍል ሰባትና ስምንት በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ስለሚታመንበት የጋብቻ ውል ጠቃሚነትና የጋብቻ ጥሎሽ አስፈላጊነት ጉዳይ ትንተና ያቀርባል፡፡
ግንቦት 29፣ 2002 (5 June 2010)
ሴቶች በንፁህ እስልምና በሚል ርዕስ በM. Rafiqul-Haqq and P. Newton የተዘጋጀው ጽሑፍ ክፍል ስድስት ስለ ወንዶች የበላይ ስልጣን እየገለጠ ስለ ሴቶች በእስልምና ያለውን አጠቃላይ አመለካከት ያቀርባል፡፡
መያዝያ 19፣ 2002 (27 April 2010)
በM. Rafiqul-Haqq እና በ P. Newton የተዘጋጀው ‹የሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና (ክፍል አራትና አምስት) › የሚለው ተከታታይ ጽሑፍ፣ እስልምና ስለ ሴቶች ያለውን አመለካከትና ስለ እምነቱም አጠቃላይ የሆነ ግንዛቤን ያካተተ ነው፡፡
መያዝያ 12፣ 2002 (20 April 2010)
በM. Rafiqul-Haqq እና በ P. Newton የተዘጋጀው ‹የሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና› የሚለው ተከታታይ ጽሑፍ፣ እስልምና ስለ ሴቶች ያለውን አመለካከትና ስለ እምነቱም አጠቃላይ የሆነ ግንዛቤን ያካተተ ነው፡፡
መጋቢት 12፣ 2002 (21 March 2010)
መሐመድ ለሴቶች ስላለው ዝቅተኛ አመለካከት ‹በአልጋዎቻቸው ላይ ዝጓቸው እና ደብድቧቸው› በሚለው የDavid Wood ጽሑፍ እስልምና ስለሴቶች ስላለው አመለካከት ግሩም ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡
የካቲት 20፣ 2002 (27 February 2010)
በሲዖል ውስጥ ካሉት ነዋሪዎች ውስጥ እጅግ በጣም አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸውን መሐመድ
መመልከቱን በሚገለጠው ሐዲት መሰረት ላይ የተመሰረተው ጽሑፍ ‹የሲዖል ውስጥ ነዋሪዎች ብዙዎቹ ሴቶች ናቸው›፣
በእስልምና ውስጥ ስላለው የሴቶችና የወንዶች ልዩነት አንድ ማስረጃ ነው፡፡
የእንግሊዝኛው ገፅ ‹ሴቶች በእስልምና› ክፍል ላይ የቀረበው ይህ ‹አላህ ሚስቶችን ረስቷቸዋልን?› የሚለው ጽሑፍ
በወንዶችና በሴቶች መካከል ቁርአን ስላስቀመጠው ልዩነት ያስረዳል፡፡
ጥር 29፣ 2002 (6 February 2010)
ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን ለማወዳደር ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ <መጽሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን ማወዳደር> በሚለው በዚህ አጭር ጽሑፍ ውስጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከቁርአን ጋር ብቻ ማወዳደር ትክክል እንዳልሆነ Samuel Green በግልፅ አቅርቦታል፡፡
ጥር 21፣ 2002 (29 January 2010)
ቁርአን ስለ አምላክ በውስጡ ከሚሰጠው ማስረጃዎች ላይ ግልፅ ሊሆን እንደሚችለው በፍፁም ከእግዚአብሔር የመጣ ሊሆን አይችልም፣ በማለት የBassam Khoury አጭር ጽሑፍ በቁርአን 42.11 ላይ ተመስርቶ ግሩም ትንተናን ያቀርብልናል፡፡
ጥር 9፣ 2002 (17 January 2010)
መሐመድ ነቢይ ሆኖ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢት እንደተተነበየ ብዙ ሙስሊሞች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ አብዛኛውንም ጊዜ የሚጠቀሱት ጥቅሶች የታወቁ ናቸው፡፡ በእነዚህን ጥቅሶች ላይ በመመስረት David Wood ያቀረበው ‹መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ?› የሚለው ጽሑፍ ግሩም የሆነ ማብራሪያን ያቀርብና ብዙ ክርስትያኖች ያላስተዋሉትንና ስለ ነቢዩ መሐመድ የተገሩትን እውነተኛ ትንቢቶችን ደግሞ ገልጦ ያሳየናል፡፡
ታህሳስ 11፣ 2002 (20 December 2009)
በቁርአን 2.97 ውስጥ ያለው ዓረፍተ ነገር፣ ለሚያነበው ሁሉ አስገራሚ ነው፡፡ ጸሐፊው Jochen Katz ይህንን ጥቀስ በሎጂካዊ የቋንቋ ሕግ ትንተና መሰረት ከተነተነ በኋላ የደረሰበት መደምደሚያ ጠቃሚ ትምህርት ሰጪ ነው፡፡ <‹በላቸው› - የሚለው የተምታታ አባባል የተዘበራረቀበት የቁርአን ጸሐፊ!>ን ያንብቡ::
ህዳር 18፣ 2002 (27 November 2009)
በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰው ‹ኢሳ› የመጽሐፍ ቅዱሱ ጌታ ኢየሱስ ነውን? ቁርአን ለ93 ጊዜ ያህል ‹ኢሳ› እያለ የሚጠራው የመጽሐፍ ቅዱሱን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ነውን? Jay Smith የጻፈው ይህ ጽሑፍ የቁራኑን ‹ኢሳ› ከመጽሐፍ ቅዱሱ ጌታ ኢየሱስ ጋር በማነፃፀር የሚያቀርበው እውነት ለእምነታችን የሚጠቅም አስገራሚ ብርሃንን ይፈነጥቃል፡፡
ህዳር 11፣ 2002 (20 November 2009)
ኦሪት ዘዳግም 18.18-19 በመጠቀም መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ትንቢት የተነገረለት ነቢይ ነው በማለት ሙስሊሞች ይናገራሉ፡፡ በDavid Wood የተጻፈው ይህ አስገራሚ <የኦሪት ዘዳግም ምርመራዎች:...> የተሰኘ ትንተና ግን ቀጣዩም ኦሪት ዘዳግም 18.20 መታየት እንዳለበት አመልክቶ ያቀረበው ማስረጃ መሐመድ ሐሰተኛ ነቢይ እንደሆነ ነው፡፡
ቁርአን በሰማይ ካለው የመጽሐፍት እናት በመሐመድ በኩል የወረደና ምንም ስህተት እንደሌለበት ሲነገር ዘመናት አልፈዋል፡፡ ይህንን ሐሳብ አሁንም ብዙዎች ያስተጋቡታል፣ ነገሩ እውነት ነውን? የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ Jay Smith በዚህ በሁለተኛው ክፍል ነገሩ እንደተባለው ሁሉ እንዳልሆነ ከራሱ ከቁርአን የመነጩ ማስረጃንና ውጫዊ ማስረጃዎችንም ያቀርብልናል፡፡
ህዳር 5፣ 2002 (14 November 2009)
ቁርአን በሰማይ ካለው የመጽሐፍት እናት በመሐመድ በኩል የወረደና ምንም ስህተት እንደሌለበት ሲነገር ዘመናት አልፈዋል፡፡ ይህንን ሐሳብ ብዙዎች አሁንም ያስተጋቡታል፣ ነገሩ እውነት ነውን? የዚህ ተከታታይ <የቁርአን ውጪያዊና ውስጣዊ ሁኔታ ሲገመገም> የተሰኘ ጽሑፍ ጸሐፊ Jay Smith ግን ነገሩ እንደተባለው እንዳልሆነ ከራሱ ከቁርአን የመነጩ ውስጣዊ እና ደግሞም ውጫዊም ማስረጃዎችን ያቀርብልናል፡፡
የክርስትያኖችን ቅዱስ መጽሐፍ እንዲሁም ወንጌልን በተመለከተ ቁርአን የተለወጡ ወይንም የተበረዙ ናቸው በማለት በፍፁም አይናገርም፡፡ ይሁን እንጂ ስለወንጌል የተናገራቸው ገሮች ቅራኔዎች አሏቸው፣ እነዚህን ቅራኔዎች የመረመረው <ወንጌል ምን ዓይነት መጽሐፍ ነው?> በሚለው ጽሑፍ ውስጥ Jochen Katz ምጥን ያለች ግሩም መግለጫን አቅርቧል፡፡
ጥቅምት 28፣ 2002 (7 November 2009)
በቁርአን ውስጥ ያሉትን እስላማዊ ሕግጋት ለቅሞ በማውጣት M. J. Fisher, M.Div አንድ መቶ ስድስት ጥቅሶችን በዚህ <እስላማዊ ሕግ> በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ አቅርቦልናል፡፡ በመግቢያውም ላይ የመጽሐፍ ቅዱስንና የእስላማዊ ሕግጋትን ምንጮች በንፅፅር መልኩ ግሩም አድርጎ ጥቆማ ሰጥቷል፡፡
ጥቅምት 19፣ 2002 (29 October 2009)
የእስልምናው ቁርአን ከክርስትያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የወሰዳቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ፣ እስልምናና ክርስትና በጣም የተቀራረቡ እምነቶች ናቸው በማለት አንዳንዶች ይገምታሉ፡፡ ሁኔታውን በትክክል ለመረዳት እንድንችል M. J. Fisher, M.Div. <ክርስትናና እስልምና> በሚለው በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መሠረታዊ ንፅፅሮችን በግሩም ሁኔታ አስቀምጦልናል፡፡
ጥቅምት 4፣ 2002 (14 October 2009)
ስለ ጦርነትና ሰላም ቁርአን በዘጠና ጥቅሶቹ ውስጥ ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ይናገራል፡፡ ያለምንም ተጨማሪ ማብራራት M. J. Fisher, M.Div. ቁርአን ውስጥ ለቅሞ ያወጣቸው እነዚህ ጥቅሶች እራሳቸው ለራሳቸው እና ለእስልምና እምነት ብዙ ይናገራሉ፡፡ ይህን <ጦርነትና ሰላም> የተሰኘ ትርጉም ይዩ፡፡
መስከረም 20፣ 2002 (30 September 2009)
በዚህ ጽሑፍ <ነፃ ፈቃድና - የአስቀድሞ ውሳኔ> M. J. Fisher, M.Div. ቁርአን ውስጥ ያሉ ሃያ ስድስት ጥቅሶችን አስቀምጧል፡፡ ጥቅሶቹም ስለመመረጥና ስለመምረጥ፣ እንዲሁም አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ገነት ነው የሚገባው ወይንስ ሲዖል ለሚሉት የሃይማኖት ወሳኝ ትምህርቶች ምን እንደሚያቀርቡ ያሳየናል፡፡
መስከረም 12፣ 2002 (22 September 2009)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱ ብዙ የብሉይና የአዲስ ኪዳን ሰዎች በቁርአንም ውስጥ በብዛት ተጠቅሰዋል፡፡ እንዴት ተጠቀሱ? የተጠቀሱበት ሁኔታና ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተመሳሳይነት አለው ወይ? ትክክለኛውና እውነት የሚመስለውስ የትኛው ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ለማግኘት መመርመር እንዲቻልና ወደ እውነትም ለመድረስ M. J. Fisher, M.Div. የሚያስገርሙ እውነቶችን በዚህ ጽሑፍ <መጽሐፍ ቅዱሳዊ ገፀ ባሕርያት በቁርአን> አቅርቦልናል፡፡
መስከረም 2፣ 2002 (12 September 2009)
ስለ እስልምና እምነት ጀማሪ መሐመድና ስለ ቁርአን ታሪክ ምን ያህል ታውቃላችሁ? ይህ <የመሐመድና የቁርአን ታሪክ> የተሰኘ የM. J. Fisher, M.Div ጽሑፍ እውነተኛ ማስረጃ ያላቸውን መጠነኛ ታሪካዊ እውነቶችን በግልጥ ያስነብበናል፡፡
ነሃሴ 7፣ 2001 (13 August 2009)
አንድ ሙስሊም የኃጢአት ይቅርታ እርግጠኝነትን በማግኘት የመንግስተ ሰማይ ወራሽ ሆኜአለሁ በማለት መናገር ይችላልን? ይህንንስ ለማለት እምነቱና የእምነቱ መጽሐፍ ቅርአን ይፈቅድለታልን? M. J. Fisher, M.Div. ደኅንነትን አስመልክቶ ቁርአን የሚያስተላልፈውን እውነታ በዚህ <ደኅንነት በቁርአን> በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ ለቅሞ አቅርቦታል፡፡
ነሃሴ 1፣ 2001 (7 August 2009)
በእስራኤልና በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ጥልቅ የሆነ ጥላቻ የመኖሩ መሠረታዊ ምክንያት ምንድነው? ለመሆኑ ሙስሊሞች አይሁዶችን አምርረው እንዲህ የሚጠሏቸው ለምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎች በሰዎች ሁሉ አዕምሮ ውስጥ ሊጉላሉ ይችላሉ፡፡ ቁርአን አይሁዶችን በተመለከተ የሚናገሩ አዎንታዊና አሉታዊ የሆኑ ሰባ አንድ ጥቅሶችን በመልቀም የM. J. Fisher, M.Div <አይሁዶች በቁርአን> የተሰኘው ጽሑፍ መሠረታዊ የሆኑ ግንዛቤዎችን ይሰጠናል፡፡
ሓምሌ 17፣ 2001 (24 July 2009)
ትንቢትና ፍፃሜ በአንድ እምነት ዙሪያ የሚገኙ ነገሮች ናቸው፡፡ ቁርአን እንደ ሃይማኖት መጽሐፍ ትንቢቶች አሉት፣ በዓለም ውስጥ ስለሚሆኑ ክስተቶች ቁርአን የተናገረው ትንቢት የሚገኘው በአንድ ጥቅስ ላይ ብቻ ነው፡፡ M. J. Fisher, M.Div; በዚህ <የዓለም ክስተቶች ትንቢት> በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ የአንዱን ጥቅስ ሐሳብና የትንቢቱን ሁኔታ ያብራራል፡፡
በቁርአን ውስጥ ያሉት የወንጀለኛ መቅጫ ሕጎች ብዙ እና ጭከና የተሞላባቸው ናቸው፡፡ <በቁርአን ውስጥ የወንጀለኛ መቅጫዎች> ደግሞ Fisher አስራ ስምንት የሚሆኑትን የቁርአን ጥቅሶች አስቀምጦልናል፡
ሓምሌ 15፣ 2001 (22 July 2009)
የክርስቶስን የመስቀል ስቅለት በተመለከተ ሙስሊሞች ሁሉ ወጥ የሆነ አመለካከት የላቸውም <በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት - የእስላም ግራ መጋባት!>፡፡ Derik Adams; The Confusion of Islam regarding the Crucifixion of Jesus Christ; በሚለው ጽሑፉ ውስጥ በቁርአን 4.157 ላይ በሙስሊም ሊቃውንት የተሰጡ ትንተናዎችንና አራት ፅንሰ-ሐሳቦችን አቅርቦልናል፡፡
ሓምሌ 10፣ 2001 (17 July 2009)
ጋብቻንና ፍቺን አስመልክቶ ሃያ አምስት የሚሆኑ ጥቅሶች በቁርአን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች M. J. Fisher, M.Div አንድ ላይ ሰብስቦ እንድናነባቸውና እንድናስብባቸው በ<ጋብቻና ፍቺ በቁርአን> አቅርቦልናል፡፡
ሓምሌ 8፣ 2001 (15 July 2009)
በRoland Clarke ከተጻፈው Lighting Up The Darkness የተቀናበረው ይህ ‹መንፈሳዊውን ጨለማ ማብራት› የሚለው ጽሑፍ አንድ ሰው መንፈሳዊ ብርሃንን ለማግኘት እንዴት እንደሚችል ያሳያል፡፡ ጌታ ኢየሱስ እራሱ እንዲሁም የሰበከው ወንጌል ብርሃን እንደሆነም በማስረጃ ያቀርባል፡፡
ሰኔ 27 ፣ 2001 (4 July 2009)
ቁርአን እጅግ በጣም አስገራሚ በሆኑ አባባሎች የተሞላ ነው፡፡ አዘጋጆቹ አስገራሚ የሚሏቸውንና ከቁርአን ውስጥ ያወጧቸውን የጥቅሶች ስብስብ (የቁርአን አስገራሚ ጥቅሶች) አቅርበዋል ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች በማስተዋል ማንበብ ምን መከተል እንዳለብን ለማስተዋል ይጠቅማል፡፡
ሰኔ 21 ፣ 2001 (28 June 2009)
ቁርአን ስለሴቶች ምን ይናገራል? M. J. Fisher, M.Div. ባዘጋጀው በዚህ ጽሑፍ (የሴቶች ሁኔታ በቁርአን) ላይ በቁርአን ውስጥ ስለሴቶች የሚናገሩትን ሃያ ዘጠኝ ጥቅሶች በመልቀም አስቀምጧቸዋል፡፡ አንድ በአንድ እያገናዘቡ ማንበብ ስለምንከተለው እምነት ትክክለኛ ግንዛቤን እንድናገኝ ይረዳናል፡፡
የሙስሊሞቹን አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን? ይህንን ጥያቄ አስበውበት የሚያውቁ ከሆነ ወይንም አስቸግሮዎት የሚያውቅ ከሆነ ይህንን ጽሐፍ (አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን? አጠቃላይ እይታ) ማንበብ ይኖርብዎታል፡፡ በAnswering Islam ውስጥ General Reflection በሚል ርዕስ ስር የሰፈረው ይህ ጽሐፍ ግሩም እይታን ይሰጣል፡፡ ለመሆኑ የሙስሊሞች አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ሊሆን እንዴት አይችልም?
ሰኔ 13 ፣ 2001 (20 June 2009)
ቁርአን የሚለው ቃል ትርጉም ‹ማስታወስ› ነው፡፡ ቁርአን በሙስሊሞች ሁሉ የተከበረ መጽሐፍ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ (ቁርአን ባጠቃላይ ምን ያሳያል?) ጸሐፊ M.J Fisher, M.DIV ቁርአን ስለ እራሱ የሚናገረውን ነገር ከስልሳ አንድ ጥቅሶች ውስጥ በመልቀም ለአስተዋይ አንባቢዎች ግልፅ ለማድረግ ሞክሯል፡፡
ሰኔ 6 ፣ 2001 (13 June 2009)
የሙስሊሞች መጽሐፍ ማለትም ቁርአን ስለመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ነገሮችን ይናገራል፡፡ በM.J Fisher, M.DIV የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በቁርአን ውስጥ የሚለው ጽሑፍ ቁርአን ስለመጽሐፍ ቅዱስ የሚናገራቸውን ሰባ አንድ ጥቅሶች የሚጠቁምና እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
ግንቦት 29 ፣ 2001 (6 June 2009)
ቅዱስ መጽሐፍ በተባለ አንድ መጽሐፍ ውስጥ ብዙ ተረቶችን ብታገኙ ምንድነው የምትሉት? M. J. Fisher, M.Div በቁርአን ውስጥ ያሉትን ተረቶች ለቅሞ በማውጣት Unusual Tales (ያልተለመዱ የቁርአን አባባሎች) በሚል ርዕስ ውስጥ አቅርቧቸዋል፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን በጥንቃቄ ተመልከቷቸውና እና የእምነታችሁን መሰረት መርምሩ፡፡
ቁርአን ስለተፈጥሮና ስለሳይንስ የሚናገረው ነገር ከእግዚአብሔር ለመሆኑ ማስረጃ እንደሆነ ሲነገር ብዙ እንሰማለን፡፡ በM.J Fisher, M.DIV የተቀናበረው ‹ተፈጥሮና ሳይንስ በቁርአን› የሚለው ጽሑፍ ሳይንስ ነክ የሆኑትን ጥቅሶች ለቅሞ አቅርቧቸዋል፡፡ በቁርአን ውስጥ ያሉትና ሳይንሳዊ የተባሉት ነገሮች በሳይንስ የሚረጋገጡና ቁርአን የእግዚአብሔር መልእክት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸውን? ጽሑፉን እንመልከተው እና እናስብበት፡፡
ግንቦት 8 ፣ 2001 (16 May 2009)
ስለ መሐመድ ምን ያህል ታውቃላችሁ? ብዙ ሙስሊሞች መሐመድን የእስላም ነቢይና ትክክለኛ የአላህ መልክተኛ እንደሆነ፤ ከሌሎችም የጥንት ነቢያት የሚተካከል እንደሆነ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ M. J. Fisher, M.Div በ87 የቁርአን ጥቅሶች ላይ ስለመሐመድ የጻፈውን "መሐመድ በቁርአን" አቅርቦታል:: በማስተዋል ያንቡት፡፡
ግንቦት 1 ፣ 2001 (9 May 2009)
ሙስሊሞች መጽፍ ቅዱስን አምርረው ይቃወማሉ፤ ለምንድነው? የእነሱ መጽሐፍ ስለሚያዛቸው ነውን? አይደለም:: ይህንን የሚያደርጉት በቁርአን ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃወሙ የሚመስሉ ጽሑፎችን በስህተት ስለተረዷቸው ነው፡፡ ይህንን እውነት ለማየት የሚከተለውን "አስመሳይ ጥቅሶች" በሚል ርዕስ የተጻፈውን የM.J Fisher, M.DIV ጽሑፍ ማንበብና ከቁርአን የተጠቀሱትንም ጥቅሶችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡
ቁርአን በበርካታና መልስ በሌላቸው ቅራኔዎች የተሞላ ነው፡፡ የመልስ ለእስላም አዘጋጆች በ<የቁርአን ውስጥ ቅራኔዎች> ከዚህ የሚከተሉትን ለሙስሊም አንባቢዎች አቅርበዋል፡፡ አስተዋይና እውነትን ፈላጊ አንባቢ ወደ ማስተዋል እንዲመጣ ይጋብዛሉ፡፡
ሚያዝያ 16 ፣ 2001 (24 April 2009)
በክርስትና እምነት ውስጥ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጠውና የእምነቱ ዋና ማስረጃ ከሚደረገው አንዱ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት ማለትም ትንሳኤ ነው፡፡ የክርስቶስ ትንሳኤ ሎጂካዊ ማስረጃና ማረጋገጫ አለው ወይ? ቁርአን የእግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ሙስሊሞች የሚናገሩት ነገር ሎጂካዊ ማረጋገጫና ማስረጃ አለው ወይ? ለሚሉት ጥያቄዎች David Wood የሰጠውን ትንተና በዚህ "የአውራ ጣት ሕግ" በተሰኘ ጽሑፍ ያንብቡ፡፡ አስደናቂ እውነትን ታገኙበታላችሁ፡፡
ርዓን ስለ መሐመድ የሚናገረውና ብዙ ሙስሊሞች የሚያምኑት እሱ ከእግዚአብሔር የተላከ ነቢይ እንደሆነ ነው፡፡ ነገሩ እውነት ነውን? በእርግጥ መሐመድ እውነተኛ ነቢይና የተናገረውም ነገር ሊታመንበት ይገባልን? ይህ የDavid Wood ጽሑፍ የመሐመድ ሳይኮሎጂያዊና መንፈሳዊ አለመረጋጋት ምርመራ ላይ የሚሰጠው ታሪካዊ እውነት በጣም ይረዳዎታል፡፡
ሚያዝያ 12 ፣ 2001 (20 April 2009)
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለክርስትያኖች ተስፋ በተገባው መንግስተ ሰማይና በቁርአን ውስጥ የተገለጠው ፓራዳይዝ ወይንም ገነት መካከል እጅግ በጣም ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ታዲያ የትኛው ነው እውነተኛ ሁለቱም ትክክል ሊሆኑ ይችላሉን? ይህ የ M. J. Fisher, M.Div. ጽሑፍ (መንግስተ ሰማይ በቁርአን) ይህን እርሰ ጉዳይ በማብራራት ይመረምራል።
በዚህ ጽሑፍ (የቁርአን እርስ በእርስ ተቃርኖ፡ ከማርያም ጋር የተነጋገሩት መላእክት ስንት ናቸው?) Jochen Katz በቁርአን ውስጥ ካሉት የሃሳብ ትቃርኖዎች አንዱን ያሳየናል።
ሚያዝያ 1 ፣ 2001 (9 April 2009)
ቁርአን ስለ ክርስትያኖች ያለውን አመለካከት ያውቃሉን? ክርስትያኖች ትሁታን እንደሆኑ በመንግስተ ሰማይም ልዩ ሽልማት እንደሚጠብቃቸው በመጀመሪያው አካባቢ ይናገርና በስተመጨረሻው ላይ ደግሞ እጅግ ክፉዎች እንደሆኑ ሲዖልም እንደሚገባቸው ይናገራል፡፡ ይህ የM. J. Fisher, M.Div. ጽሑፍ (ክርስትያኖች በቁርአን) እነዚህን ነገሮች ለቅሞ በማውጣት እንድናስተውላቸው ያደርጋል፡፡
የሙስሊሞች ቁርአን ስለ ሲዖል ብዙ ነገሮችን ይናገራል፡፡ ስለዘ ሲዖል ብዙ ነገሮችን አውቆ፣ ከሲዖል የሚዳንበትን መንገድ አንድ ሰው ካላወቀ ስለ ሲዖል ብዙና ዝርዝር ነገሮችን ማወቅ ምንም ጠቀሜታ የለውም። ስለ ሲዖል ማወቅ ከሲዖል ጥፋት በጭራሽ አያድንም፡፡ ይህ የ M. J. Fisher, M.Div. ጽሑፍ (ሲዖል በቁርአን) ስለ ሲዖል ቁርኣን የሚናገረውን ልዩ ልዩ ነገሮች አስፍሯቸዋል፡፡
መጋቢት 28 ፣ 2001 (6 April 2009)
በዓለማችን ላይ እጅግ በጣም ብዙ ሙስሊሞች አሉ፡፡ አንዳንዶች ሙስሊም የሆኑት ከሙስሊም ቤተሰብ በመወለዳቸው እንደሆነ በትክክል ግልፅና የሚታወቅም ነገር ነው፡፡ ግን አንድ ሙስሊም ስለ ሃይማኖቱ ምን ያህል ያውቃል? ስለሃይማኖቱስ ጥያቄዎች የሚሆኑበትን ነገሮች እንዴት ነው የሚያያቸው? እኔስ ሙስሊም ብሆን ኖሮ ምን ማድረግ ነው የሚኖርብኝ? ይህ የ Dallas M. Roak ግሩም ጽሑፍ ሙስሊም ብሆን ኖሮ እያለ አንዳንድ ጥያቄዎችን ያነሳና መልሳቸውን ያሳየናል፤ እናንብበው፡፡
መጋቢት 11 ፣ 2001 (20 March 2009)
መሐመድ ነቢይ እንደሆነና ከእግዚአብሔርም መልእክትን እንደተቀበለ ቁርአንም ሙስሊሞችም ይናገራሉ፡፡ መሐመድ እውነተኛ ነቢይ ለመሆኑ በምን መመርመር ይቻላል? የመጀመሪያው መልስ መሆን ያለበት ቁርዓን የሚሰጠው ውስጣዊ ማስረጃ ነው፡፡ በ Jochen Katz የተጻፈው የመለኮታዊ መገለጥ ድንቁርና?... በቁርዓን ምዕራፍ 3.183 ላይ መሐመድ በተናገረው መገለጥ ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ሲሆን መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ እንዳልሆነ በትክክል የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በማስተዋል እና በጥንቃቄ አንብቡት፡፡
መጋቢት 5 ፣ 2001 (14 March 2009)
የእስልምና እምነት መመሪያ ቁርአን ስለ አላህና ስለ ጌታ ኢየሱስ የሚያስተምረውን ትምህርት መረዳትና ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በ David Wood በተጻፈው "አታላይ አምላክ ብቁ ያልሆነ አዳኝ..." በተሰኘው ጽሑፍ ውስጥ ቁርአን ሙስሊሞች አምላክ ነው የሚሉትን ‹አላህ›ን ታላቅ አታላይ ሲያደርገው፤ ኢየሱስን ደግሞ እንደ-ነቢይም ሆነ እንደ-አዳኝ ብቃት እንዳልነበረው አድርጎ አቅርቦታል።
መጋቢት 2 ፣ 2001 (11 March 2009)
"ለከፍተኛ ዓላማ ተጠራሁ" በ አዛድ ከኢራቅ እና "ሙስሊም በእርግጥ ማወቅ ይችላልን?" በ ዮሴፍ አብርሃም ከግብፅ፤ እነዚህ ሁለት ወንድሞች ወደ ክርስትና እንዴት እንደመጡና በክርስትና ሕይወት ምን እንዳገኙ ይመሰክራሉ።
የካቲት 24 ፣ 2001 (03 March 2009)
ዛሬ ለእስልምና መልስ ፡ አማርኛ ክፍል በኢንተርኔት ይፋ ሲሆን የመጀመሪያ ቀኑ ነው። ወደዚህ ገጽ እንኳን ደህና መጡ! ለጊዘው በግራ በኩል ያለውን ሜኑ በመጠቀም የተለያየ ይዘት ያላቸው፣ አስራ አንድ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ። ወደዚህ ገጽ የሚመጡ ሁሉ የእግዚአብሔርን እውነትና መጠን የሌለው ፍቅር እንዲያገኙ ምኞታችን ነው።
በሳም ሻሞን የተጻፈው "የቁርዓኑ አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ነውን?" በቁርዓኑ አላህ ባህርይና በእግዚአብሔር ባህርያት መካከል ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን በትክክል በመግለጽ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር የቁርአኑን አላህ ሊሆን እንደማይችል ያሳያል፡፡ በ "የቁርአን እርስ በእርስ ተቃርኖ፡ ሙስሊሞች ሁሉ ሲኦል ይሄዳሉን?" ሳም ሻሞን ሱረቱ 19.71 ላይ የተመሠረተ ውይይት በማድረግ አዎ ቁርዓን ሲዖል ከመግባት ማንም (ሙስሊም) አያመልጥም እንደሚል ያሳያል። በ "መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ ነውን?" በሚለው ጽሑፍ ደግሞ ሙስሊሞች መሐመድ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው በማለት የሚያምኑት እምነት ትክክል አለመሆኑን የሚያሳዩ ስድስት ሐሳቦችን ያቀርባል፡: በ ሮይ ኦስነቫድ የተጻፈው "መልካምነት በእናንተ ውስጥ ይኖራልን?" መሠረታዊ ክርስትናን ያስተምራል። ሁለት ወንድሞች ወደ ክርስትና እንዴት እንደመጡ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡ "ከሞት የበለጠ ኃይል" በ ሳሚር ከኢራቅ እና "ከእስልምና ወደ ክርስትና የእምነት ጉዞዬ" በ ዩቼል (Yücel) ከቱርክ።
በ "ቁርአን ስለ ፍርድ ቀን" የመጨረሻውን የፍርድ ቀን በተመለከተ እስልምናም ክርስትናም የሚናገሩት በጣም በጥቂቱ ይመሳሰል እንጂ ጉልህ ልዩነቶች እንዳሏቸው እናያለን፡፡ "ለአላህ የተሰጡ ሰዋዊ ባህርያት" ሙስሊሞች ለእግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ተሰጠ የሚሉት አካላዊ ገለጣን በተመለከተ ያላቸው ነቀፌታ መሠረታዊ ችግሮች እንዳሉት ያሳያል፡፡ "ኢየሱስ" የሚለው ዓምድ ሰማንያ ስምንት የቁርዓን ጥቅሶች በመንካት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ንፅፅር በማድረግ ሙስሊሞች ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸው ግንዛቤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በፍፁም የተቃረነ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ከዚህ በላይ ያሉ ሦስት ጽሁፎች ከ "A Topical Study of the Qur'an From a Christian Perspective" by M.J Fisher, M.Div ምዕራፍ 8፣ 13 እና 21 የተተረጎሙ ናቸው።
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ