የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች
ምዕራፍ ስድስት ክፍል አንድ
በአዳጊው እስልምና ላይ የሃኒፎችና የእነሱ ተፅዕኖ፣ መደምደሚያ
በREV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D
ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ
መሐመድ በዚያን ጊዜ ታዋቂ የነበረው የአረቦች ሃይማኖት ሞኝነትና ምንም ጥቅም የልነበረው መሆኑን የተገነዘበው ተሐድሶ ለማምጣት ይመኙ ከነበሩት ከአገሩ ሰዎች ስለነበር በምንም መንገድ እርሱ የተሐድሶው እንቅስቃሴ የመጀመሪያው አልነበረም፡፡ ከእርሱ የመጀመሪያ የታሪክ ጸሐፊዎች እንደምንማረው ከሆነ እርሱ እንደ ነቢይ ከመታየቱ ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ እጅግ ብዙ ሰዎች በመዲና፣ በጣይፍ እና በሜካ ተነስተው ነበር ምናልባትም በሌሎችም ቦታዎች እንዲሁ እነርሱም የሕዝቡን የጣዖትና የብዙ አማልክት አምልኮውን ያልተቀበሉና እውነተኛውን ሃይማኖትን ለማግኘት ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡ ይህ የእነርሱ የእውነተኛ እምነት ፍለጋ መነሳሳት ከአይሁዳውያን ወይንም ከሌሎች ቦታዎች መምጣት አለመምጣቱ ግን በጣም አጣራጣሪ ነው፡፡ እነዚያ የጠቀስናቸው ሰዎች የታላቁን እግዚአብሔርን አምልኮ (አላህ ታ ዓ ላን) እንደገና ለማደስና በሚገባው ቦታ ላይ ለማድረግ ቆርጠው ነበር፡፡ የእርሱን ቦታ ሙሉ በሙሉ በመውሰድ ላይ የነበሩትን የታናናሾቹን አማልክትና በዚያን ጊዜ የነበሩትን እጅግ አስፀያፊ ስነ ምግባር የጎደላቸውን፤ ከሰብዓዊ ሕሊናና ከሰው ልጅ ሕይወት የሚቃረኑትን ልምምዶች ሁሉ ጭምር ለማደስ ነበር፡፡ እነዚህ የተሐድሶ መሪዎች እንደሚሉት (እንደሚጠቅሱት) እንደ አባታቸው የሚጠቅሱት አብርሃም አንዱንና እውነተኛውን አምላክ ማወቁና ማምለኩን ነበር፡፡ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ ልማድ መሰረት ወይንም በአይሁዶች አባባል ያገኙትና ሁሉም ይፈልጉት የነበረው የአብርሃምን ሃይማኖት ነበር፡፡ ምናልባትም የአይሁዶች ለራሳቸው ብቻ መገለል፤ እነዚህን በአይሁድ ምኩራብ እንደሚገመተው ሁሉ እንዳይደባለቁ ያደረጋቸው ነገር ሊሆን ይችላል ያነሳሳቸው፡፡ ወይንም በሌላ ጎኑ አገር አቀፍና የቤተሰብ ትምክህት ከሌላ አገር መጥተው በአገራቸው የሰፈሩ ሰዎችን ሃይማኖት በፈቃደኝነት እንዳይቀበሉ አግዷቸው ሊሆንም ይችላል፡፡ እንዲሁም ደግሞ እነዚህ አንዳንዶቹ የተሐድሶ መሪዎች በዘመኑ የነበረው የአይሁድ ሃይማኖት ከብዙ የባዕድ እምነት በምንም መንገድ ያልነፃ መሆኑን ተገንዝበው የነበረ ሊሆንም ይችላል፡፡ ክርስትያኖች አይሁዶችን የሚወቅሱባቸው፣ ማለትም መሲሁን አለመቀበላቸውና መግደላቸውን በተመለከተና የመውቀሳቸው እውነታ እራሱ፤ እንዲሁም የአይሁዶች መውደቅ ሁኔታ የእግዚአብሔር ፍርድ ምልክት መሆኑን መጥቀሳቸው፤ እነዚህ የነቁ አረቦች የታልሙዲክ አይሁዲነትን እንዳይቀበሉት ተፅዕኖ ሳያደርግባቸው አልቀረም፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን እውነታው የሚሆነው የተሀድሶዎቹ መሪዎች በቅድሚያ የመጡት እንደ ጠያቂዎች ሆነው እንጂ ወደ አይሁድነት ወይንም ወደ ክርስትና የገቡ ሰዎች ሆነው አልነበረም፡፡ ከእርሱም ዋናቸው በመዲና ይኖር የነበረው አቡ አሚር በመባል የሚታወቀው ነው፣ እንዲሁም ዑማያ ኢብን ዛልት በጣይፍ የነበረው፣ በሜካ ደግሞ ዋራቃ፣ ዑባይዱላህ፣ ዑትማን እና ዛይድ ኢብን አሚር ይገኙባቸዋል፡፡ ሌሎች ግን ያለምንም ጥርጥር ቢያንስም ቢበዛም ከእነዚህ ሰዎች ጋር የሚዛመዱ ናቸው ምንም እንኳን እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ተከታዮችን ባያዙም እንኳን፡፡
በጊዜው ከምንመለከተው ከአንድ ግጥም በስተቀር እነዚህ ሁሉ የተሀድሶ መሪዎች የራሳቸውን እምነት ምንነት በተመለከተ ምንም የተውልን ጽሑፍ የለም፡፡ ስለዚህም እነርሱን በተመለከተ ለምናስቀምጠው ዓረፍተ ነገር ምን ዓይነት ስልጣን ሊኖረን እንደሚችል መናገር በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ የእኛ ዋና እና ተግባራዊ ብቸኛ ስልጣን የሚሆነው የቀደመው የሰዎች ታሪክ ዘጋቢው ስለ መሐመድ የዘገበው ስራ ነው፡፡ የእርሱም ስራ ወደ እኛ የመጣው በኢብን ሒሻም አማካኝነት ነው፡፡ የመጀመሪያው ጸሐፊ በእኛ ዘንድ የመሐመድን የሕይወት ታሪክ አቀናብሯል በመባል በስም የሚታወቀው ዙህሪ ነው እርሱም በሂጂራ 124 ዓመት ሞቷል፡፡ መረጃውንም ያገኘው መሐመድን በግል ከሚያውቁት ሰዎች በመጣለት የቃል መረጃ፤ በተለይም በዑርዋ ነው፡፡ እርሱም የአይሻ ቤተዘመድ አባል ነው፡፡ በብዙ መልኩ ያለምንም ጥርጥር ስህተቶችና ማጋነኖች፣ በዓመታት ውስጥ በእንደዚህ ዓይነት ልማድ ውስጥ ገብተዋል፣ ነገር ግን በእርግጥ አሁን በሌለው በዙህሪ መጽሐፍ ውስጥ በጣም ትልቅ ዋጋ ይኖረው ነበር፡፡ ነገር ግን መጽሐፉ አልተጠበቀም ይህም በጣም አጠራጣሪ እንደሆነው፤ ኢብን ኢሻክ፤ አንዱ የዙህሪ ደቀመዝሙር በ151 ከሂጂራ በኋላ የሞተው የመሐመድን ሕይወት እራሱ በሚያጠናቅርበት ጊዜ ተጠቅሞበት ካልሆነ በስተቀር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ያለምንም ጥርጥር ኢብን ኢሻክ ከሌሎች ልማዳዊ መረጃዎች ያገኛቸውን በጣም ብዙ መረጃዎችን ጨምሯል፤ ይህም እንኳን እውነት ወይንም ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የኢብን ኢሻክ መጽሐፍ እንኳን ሙሉና እራሱን በቻለ መልክ ወደ እኛ አልመጣልንም ምንም እንኳን የእርሱ ብዙው ክፍል በ213 ሂጂራ በሞተው የኢብን ሒሻም የሲራቱል ራሱል ወይንም የሐዋርያው የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ጥቅሶች ውስጥ ተጠብቆ ቢኖርም እንኳን ነው፡፡ እርሱም ተመሳሳይ ርዕስን ከያዙት ጽሑፎች መካከል በጣም ጥንታዊው ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ መሐመድንና የነበረበትን ጊዜ በተመለከተ በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ዋጋ ያለው ነው ምክንያቱም እርሱ በተመሳሳይ ርዕስ ላይ ከተጻፉት ከሌሎቹ ስራዎች በጣም አናሳ አፈታሪክና ማጋነኖች ይዟልና፡፡
ኢብን ኢሻክና ኢብን ሒሻም ስለ አረቢያን የተሐድሶ መሪዎች የሚነግሩን ነገር በተለይም በዚህ ዘገባ ላይ ያለው ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ነው፣ ምክንያቱም በእነርሱና በመሐመድ መካከል ያለውን የትምህርት መመሳሰል በተመለከተ የማመስገን ወይንም የማዳነቅ ምንም ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ ለእነዚህ ጸሐፊዎች የእነርሱ አረፍተ ነገሮች በተቃዋሚዎቻቸው ዘንድ ምንም ዓይነት ጠቀሜታ ላይ የሚውሉ አልመሰላቸውም ስለዚህም እስከሚያውቁት ድረስ እውነቱን ዘርዝረው ምንም ሳያስቀሩ ነው የተናገሩት፡፡ ስለዚህም ሊሆን የሚችለው ነገር በእነርሱ ዶክተሪንና መሐመድ ባቀናበረው ውስጥ ያለው መመሳሰል በእጃችን ያለው መረጃ ከሚነግረን የበለጠ ሊሆን ይችላል እንጂ ያነሰ ሊሆን አይችልም ይህም ከጠቀስናቸው ምክንያቶች የተነሳ ነበር፡፡ ስለዚህም እኛ እነርሱ ያስተምሩት ለነበረውና በጥቂቱም ቢሆን በኢብን ሒሻም ዘገባ ላይ ባስተማማኝ ሁኔታ ልንመሰረትና ከቁርአን ጋር ልናነፃፅረው እንችላለን፡፡
አንባቢዎቻችን ለራሳቸው እንዲወስኑ ለማድረግ እዚህ ላይ የኢብን ሒሻምን ታሪክ ትርጉም በቀጥታ እናቀርበዋለን፣ የሚታየውም ለአብዛኛው ክፍል የተመሰረተው በኢብን ኢሻክ የቀደመው ዘገባ ላይ ነው፡፡
‹ኢብን ኢሻክ የተናገረው፡ ቁራይሾች አንድ ቀን ተሰበሰቡ፤ በነበራቸው ክብረ በዓል ላይ፤ ያከብሩት ወደነበረው ጣዖታቸው፣ መስዋዕት ያቀርቡለት ወደ ነበረው ጣዖት፣ እንደዚሁም በሚቆዩበት ቦታ ላይ ቀርበው እና ከብበው በሚቀመጡበት ቦታ ዙሪያ ላይ ሆነው፡፡ ያም በየዓመቱ አንድ ቀን የሚያከብሩት በዓል ነበር፡፡ ስለዚህም አራት ሰዎች ከእነርሱ በምስጢር ተደብቀው ነበር፡፡ ከዚያም አንዳቸው ለሌላቸው ይነጋገሩ ነበር፤ “አንዳችሁ ለሌላችሁ እውነተኖች ሁኑ ከእናንተም አንዱ የሌላውን ምስጢር ይጠብቅ” እነርሱም “በጣም ጥሩ” አሉ፡፡ እነርሱም ዋራካ ኢብን አሳድ፤ ኡባይዱላህ ኢብን ጃሃሽ፣ እናቱ ዑማይማ የነበረችው የአብዱል ሙታላብ ሴት ልጅ፣ እንዲሁም ኡትማን ኢብኑል ሁዋሪትስ እናም ዛይድ ኢብን አሚር ነበሩ፡፡ እነርሱም ለእርስ በእርሳቸው እንዲህ አሉ፡ ‹በእግዚአብሔር ታውቃላችሁ የእናንተ አገር ሕዘብ በምንም ነገር ላይ ያልተመሰረተ ነው በእርግጥም ከአባታቸው ከአብርሃም ሃይማኖት ተሳስተዋል፡፡ ዙሪያውን ልንከብበው የሚገባን ድንጋይ ምንድነው? አይሰማም አያይምም፣ አይጠቅምም ደግሞም አይጎዳምም፡፡ ኦ ሕዝቦች ሆይ ለራሳችሁ እምነትን ፈልጉ ምክንያቱም በእግዚአብሔር በእርግጥ እናንተ በምንም ነገር ላይ የተመሰረታችሁ አይደላችሁምና” በመሆኑም እነርሱ “ሐኒፊዝምን” ማለትም የአብርሃምን እምነት ለመፈለግ ወደ ሌላ አገር ሄዱ፡፡ ስለዚህም ዋራካ ኢብን ኖፋል በክርስትና ውስጥ ሰጠመ፡፡ ከዚያም እርሱ ከሚያምኑት ሰዎች መካከል ስለመጽሐፎች ጥያቄን አቀረበ ይህም ከመጽሐፉ ሰዎች አንዳንድ እውቀትን እስኪያገኝ ድረስ ነበር፡፡
ዑባይዱላህ ኢብን ጃሃሽ ግንእርግጠኛ ሳይሆን ቀረ ይህም እርሱ ሙስሊም እስከ ሆነ ድረስ ነበር፡፡ እርሱም ከዚያ በኋላ ከሙስሊሞች ጋር ወደ አቢሲኒያ ሄደ ከእርሱም ጋር የእርሱ ሚስት ዑም ሓቢባ አብራ ተጓዘች እርሷም የአቤ ሱፍያን ሴት ልጅ ነበረች እንዲሁም ሙስሊም ሆና ነበር፡፡ ስለዚህም እርሱ በዚያ እንደደረሰ ክርስትያን ሆነና እስልምናን ተወ፣ ስለዚህም እርሱ ክርስትያን ሆኖ እዚያው ጠፋ፡፡ ኢብን ኢሻክ እንደሚከተለው ተናገረ ይህም በመሐመድ ኢብን ጃፋር ኢብን ዙባይር አማካኝነት ከእኔ ጋር አገናዝ እንዲህ አለ፡ “ዑባይዱላህ ኢብን ጃሃሽ ክርስትያን በሆነ ጊዜ በኢቢሲኒያ ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከእግዚአብሔር ሐዋርያ ተከታዮች ጋር ይከራከር ነበር፣ እርሱም እንዲህ ይል ነበር፤ ‹እኛ አጥርተን እናያለን እናንተ ግን በደንግዝግዝ ውስጥ ናችሁ› ማለትም ‹እኛ የጠራ ዕይታ አግኝተናል እናንተ ግን አጥርታችሁ ለማየት ትፈልጋላችሁ ነገር ግን ገና አላያችሁም› እንዲሁም ምክንያቱም ቡችላ አይኑን ከፍቶ ለማየት በሚጣጣርበት ጊዜ እንደሚጭበረበረው ነው፡፡ የአንድ ሰው ዓይንን መከፈት በተመለከተ የተጠቀመበት ቃል ያንን ነው፡፡ ኢብን ኢሻክ አለ፡ የእግዚአብሔር ሐዋርያ ከእርሱ ቀጥሎ የዑም ሐቢባን አገባት የአቡ ሱፍያን ኢብን ሐርብ ሴት ልጅን፡፡ ኢብን ኢሻክ አለ፡ መሐመድ ኢብን አሊ ኢብን ሁሴን የሰጠኝ መረጃ የእግዚአብሔር ሐዋርያ አሚር ኢብንዑሚያ አድ ዳምሪን እርሷን እንዲሰጠው ወደ ንጉስ ላከው፡ ስለዚህም ንጉሱ እርሷን ለእርሱ አጨለት፡፡ ከዚህም የተነሳ እርሷን ለእርሱ አጋባት፡፡ ለእርሷም የጋብቻ ጥሎሽ እንዲሆን ከሐዋርያው ለመቀበል አራት መቶ ዲናርን ወሰነ ኢብን ኢሻክ አለ፡ ነገር ግን ዑትማን ኢብን ሑዋይሪትስ ወደ ቄሳር ሄደ ወደ ባዛንታይን ንጉስ ከዚያም እርሱ ክርስትያን ሆነ ከእርሱም ጋር የነበረው የእርሱ ቆይታ በብልፅግና ነበር ኢብን ኢሻክ አለ፡ ነገር ግን ዛይድ ኢብንን በተመለከተ “አሚር ኢብን ኑፋይል እርሱ እንዳለ ቆየ እናም ወደ አይሁዲነትም አልገባም ወይንም ወደ ክርስትያንነትም፡ እርሱም የራሱን ሕዝብ ሃይማኖት በመተው ከጣዖት አምልኮ እራሱን አርቆ ተቀመጠ፣ ከበከተ እንስሳ ስጋ፣ ከደም እንዲሁም ለጣኦት ከተሰዋ ስጋ እራሱን አራቀ እንዲሁም ሕፃናት ሴት ልጆችን መስዋዕት አድርጎ ማቅረብንም ተቃወመ፣ እንዲሁም እርሱ እንደሚከተለው ተናገረ፡ ‹እኔ የአብርሃምን አምላክ አገለግላለሁ› እንዲሁም የአገሩን ሰዎች በስህተታቸው በመቀጠላቸው ወቀሳቸው፡፡ ኢብን ኢሻክ አለ፡ ሒሻም ኢብን ዑርዋ በአባቱ ስልጣን ተናገረኝ፣ በእናቱም በአስማ በአቡ በከር ሴት ልጅ ስልጣን ተናገረኝ እርሷም አለች፡ “በእርግጥ እኔ ዛይድ ኢብን አሚር ኢብን ኑፋይልን አየሁኝ እንደ አሮጌ ሰው ሆኖ በካኣባ ላይ ተደግፎ እናም እንዲህ አለ፡ ‹ኦ የቁራይሽ ጎሳ ሆይ የዛይድ ኢብን አሚርን ነፍስ በእጆቹ በያዘው ከእናንተ ማናችሁም የአብርሃምን ሃይማኖት አልያዛችሁም ከእኔ በስተቀር› ከዚያም እርሱ እንዲህ አለ፡ ‹ኦ እግዚአብሔር አንተን በጣም የሚያስደስትህ መንገድ የትኛው እንደሆነ ባውቅ በእርሱ በኩል እኔ አንተን አመልክህ ነበር ነገር ግን እኔ አላወቅሁትም›፡፡ ከዚያም ደግሞ እርሱ በራሱ ሁኔታ ያመልክ ነበር፡፡ ኢብን ኢሻክ አለ፡ ከዚያም የእርሱ ወንድ ልጅ ሱኣይድ ኢብን ዛይድ ኢብን አሚር ኢብን ኑፋይል እና ዑማር ባኑል ካታብ የአጎቱ ልጅ የነበረው ለእግዚአብሔር ሐዋርያ እንደሚከተለው አሉት፡ ‹ለዛይድ ኢብን አሚር ይቅር ይባል ዘንድ ፀልይለት› እርሱም አለ፡ ‹አዎ በእርግጥ እርሱ በራሱ እንደ አንድ የሃይማኖት ክፍል ሆኖ ይነሳል›፡፡ ዛይድ ኢብን አሚር ኢብን ኑፋይል ተናገረ የራሱን ሕዝብ ሃይማኖት በመተው እንዲሁም ከዚያ በኋላ ከእነርሱ በእርሱ ላይ ምን እንደሚሆን በተመለከተ የሚከተለውን ተናገረ፡
‹አንድ ጌታ ወይንስ ሺ ጌታዎች፣ እኔ ማምለክ አለብኝ? ነገሮች የተከፋፈሉ አይደሉምን? እኔ አላትን እና ዑዛን ሁለቱንም ትቼአቸዋለሁ፡፡ ስለዚህም ከባዱን ነገር ትግስተኛውን ሰው፡፡ ስለዚህም እኔ ዑዛንና ሁለት ሴቶች ልጇቿን አላመልክም እንዲሁም ደግሞ ለሁለቱ የባኑ አሚር ጣኦታት ግብርን አልሰጥም፡፡ እንዲሁም ጋናም የተባለውንም አላመልክም ምንም እንኳን የእኔ አስተሳሰብ ይዋዥቅ በነበረበት ጊዜ እርሱ በእኛ ላይ ጌታ የነበረ ቢሆንም፡፡ ተደነቅሁኝ በየሌሊቱ በጣም አስደናቂ ነገሮች አሉ፣ በየቀኑም ደግሞ የሚያያቸው የሚገነዘባቸው ድንቅ ነገሮች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ሁኔታው ግብረገብ የጎደለውን ሰው ብዙ ጊዜ ቢያጠፋውም ነገር ግን ሌሎችን ደግሞ አገራቸውን በማዳን ይጠብቃቸዋል፡፡ ስለዚህም ከእርሱ ዘንድ ትንንሽ ልጆችን በማዳን ይጠብቃቸዋልን? ከእኛም መካከል አንድ ሰው ይወድቃል አንድ ቀን ደግሞም ሌላ ቀን ይነሳል፣ ይህም ቅርንጫፍ ከዝናብ በመጠጣት እንደምትረካ ነገር ግን እኔ መሐሪ የሆነውን ጌታን አገለግላለሁኝ ያም መሐሪው ጌታ እኔን ከኃጢአቴ ሁሉ እንዲምረኝ ነው፡፡ ስለዚህም እናንተ የጌታን የእግዚአብሔርን ፍርሃት ጠብቁ እርሱን በምትጠብቁበት ጊዜ ግን እርሱ አይጠፋም እናንተም ንፁሁን የአትክልት ቦታ የእናንተ መኖሪያ ሆኖ ታገኙታላችሁ እንዲሁም ለማያምኑት ደግሞ የሲዖል እሳት ይነድባቸዋል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በሕይወትም ውርደት ነው እነርሱም ይሞታሉ ያም ደግሞ ልቦቻቸው የተጨነቀባቸው እነርሱ ይገናኛሉ፡፡›
በዚህ አጠቃላይ ዘገባ ውስጥ ሁሉ የተመለከትነው ነገር ኢብን ሒሻም ከፍ ባለ ጥንቃቄ የሰጠን ከእርሱ በፊት የነበረው ኢብን ኢሻክ በታሪኩ ውስጥ የሰጠንን እነዚያኑ ቃላቶችን ነው፡፡ ስለዚህም የእነዚህን የተሐድሶ መሪዎችን እምነትና ታሪክ ለመመልከት እኛ አንድ እርግጠኛ የሆነ ነገር አለን፣ በተለይም ዛይድን የሚነካ ታሪኩና ክቡር የሆኑት ጥቅሶቹ በመሐመድ ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ ያለማምድ የነበረው መሆኑ፡፡ ስለዚህም የተወሰነ መጠን ያለው ተፅዕኖ ተለማምዶ የነበረ መሆኑን የሚያሳዩ ምክንያቶችን እንመለከታለን እንዲሁም እኛ በትክክል እንደምንመኘው በመሐመድ ሕይወትና ባህሪይ ላይ በጣም ብዙ ውጤት እንደነበረው ነው፡፡
ኢብን ሒሻም እንደገና በኢብን ኢሻክ ስልጣን ላይ በመመስረት የሰጠን ማስረጃ አል ካታብ የዛይድ አጎት የነበረው የኋለኛውን የሕዝቡን ሃይማኖት በመተው የተነሳ ገስፆት እንደነበረ ነው፣ እንዲሁም በመካ መኖር እስከማይችል ድረስም አሳዶት ነበረ፡፡ እርሱም ወደ አገሪቱ ሌላ ክፍል ተዘዋውሮ የነበረ ይመስላል ነገር ግን በመጨረሻ መኖሪያውን ያደረገው በሂራ ተራራ ላይ ባለው ዋሻ ውስጥ ነበር፡፡ እዚያም ለብዙ ዘመን ኖረ ሲሞትም በተራራው ግርጌ ስር ተቀበረ፡፡ የእርሱም ሞት መሐመድ እራሱን በ612 ዓ.ም የነቢይነት ተልእኮ እንዳለው ከማስተዋወቁ አምስት አመታት በፊት ነበር፡፡ አሁን ኢብን ኢሻክ የሚነግረን ነገር ያ ነገር የቁራይሾች ልማድ እንደነበር፣ “በድንቁርና ዘመን” ከተማን ለቆ በሂራ ተራራ ላይ ለአንድ ወር ያህል መቆየት ማለትም በረመዳን ወር ነበር፡፡ እርሱም እንዳያያዘው በየዓመቱ ንስሀ የሚለማመዱበት ወቅት ነበር፡፡ መሐመድ የዚያን የተለየ ወር ሙሉውን በተከታዮቹ ለሁልጊዜ የፆም ጊዜ ሆኖ እንዲከበር ከዚያ በኋላ መምረጡ የዚያ ባህል ውጤት ያመጣው ተፅእኖ ለመሆኑ በጣም ግልፅ ነው፡፡ በእርሱም ጊዜ ረመዳን በበጋ ወቅት መሆኑ፣ ይህ ከነገር ሁሉ የመቆጠቡ የፆም ወር በማህበረሰቡ ዘንድ ላሉት ሃብታሞች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ እነርሱም ሞቃትና ለጤና ተስማሚ ያልሆነውን ጠባብ የምስራቅ መንገድን እንዲተውና ንፁህና ክፍት ወደ ሆነው ወደ ገጠር አየር እንዲሄዱ አድርጓቸዋል፡፡ እኛም በዚያን ወቅት ምነና በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ስለመጫወቱ ምንም ማስረጃ የለንም፡፡ ስለ መሐመድ ግን በግልጥ የተነገረን ነገር የረመዳንን ወር ሙሉውን በሂራ ተራራ ላይ ባለው ዋሻው ውስጥ ያሳልፍ እንደነበረ ነው፡፡ እርሱም በእርግጥ ይቀመጥ የነበረው ዛይድ ይቀመጥበት በነበረው ዋሻ ውስጥ ነበር እርሱ እንደሚያምነው ከመልአኩ ገብርኤል የመጀመሪያው መገለጥ በመጣለት ጊዜ እዚያ ዋሻ ውስጥ እንደነበረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ውስጥ “ልዩ የሆነ ከዓለም መገለል ነው” ነበረበት ብሎ ነገሩን መመልከት ስህተት ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ መሐመድ ሚስቱ ከዲጃ ከእርሱ ጋር ነበረች ተብሎ ስለተነገረን እርሱ ይከተል የነበረው የራሱን ጎሳ ባህል ብቻ እንደነበር ነው፡፡
ወደ ሂራ ተራራ በሚደረገው በዚህ ዓመታዊ ጉዞ ላይ መሐመድ ከዛይድ ጋር የመነጋገር ማንኛውም ዕድል የነበረው ለመሆኑ እርግጠኛ ነገር ነው፡፡ ለሰውየውም መሐመድ የነበረው አክብሮት በልማድ ውስጥ በግልጥ ታይቷል፡፡ እኛ ከዚህ በፊትም እንዳየነው ለዛይድ ከሞተ በኋላ ፀሎት የተደረገለት ስለመሆኑ ነው፣ ይህ ደግሞ በጣም ጠቃሚ ነጥብ ነው ምክንያቱም ባይዳዊ በቁርአን 9 ቁጥር 114 ላይ ባቀረበው ትንተና ላይ ያቀረበው ነገር መሐመድ በጣም ለሚቀርባትና በልጅነቱ ለሞተችው ለራሱ እናት ለአሚና ደኅንነት እንዳይፀልይ ተከልክሎ እንደነበረ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር አል ዋኪዲ የተናገረው ነገር መሐመድ ለዛይድ የሰላም ሰላምታን እንደሰጠው ነበር፣ ይህም ለሙስሊሞች ብቻ የሚሰጥ ክብር ነው፣ ማለትም በእርሱ ላይ የእግዚአብሔርን ፀጋ አቀረበና አረጋገጠ፤ “እኔም በሰማይ ገነት ውስጥ አይቼዋለሁኝ እርሱም ከኋላው ብዙ ተከታዮችን ይስባል”፡፡ ስፒንገር እንደሚከለተው ተናገረ “መሐመድ በግልጥ የተቀበለው ዛይድ ከእርሱ በፊት የመጣ እንደነበረና የዛይድ ቃላት ናቸው ተብለው የሚታወቁትን ቃላት ሁሉ በቁርአን ውስጥ እናገኛቸዋለን” ለምሳሌም ያህል ቁርአን 3 እና ቁርአን 19፣ ላይ፡፡ መሐመድም ለተራዎቹ ሕዝቦች እንደሚከተለው ይናገር ነበር “ሙስሊሞች ሆናችኋልን?” ወይንም ደግሞ “ለእግዚአብሔር እራሳችሁን ሰጥታችኋልን?” በኢብን ኢሻክ የተነገረን እነዚህ ቃላት በመጀመሪያ ደረጃ ለሕዝቡ በዛይድ በኩል ይነገሩ እንደነበረ ነው፡፡ ከዋና ዋናዎቹ መርሆዎች ውስጥ እያንዳንዳቸው ያገኘናቸው መርሆዎች በዛይድ ተሰጥተው የነበሩ ናቸው እነርሱንም በቁርአንም ውስጥ እናገኛቸዋለን፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለምሳሌ መነሳት የሚችሉት፡ 1. ሕጻን ሴት ልጆችን በሕይወት እንዳሉ በመቅበር የሚደረገው የዚያን ጊዜው የአረቦች የጭከና ባህል መከልከሉ፣ 2. የእግዚአብሔርን አንድነት እውቅና መስጠት፤ 3. የጣዖታትን አምልኮ አለመቀበል እና የአል-ላትን፣ የአል-ዑዛንና የሌሎችን የሕዝቡን አማልክት አምልኮ አለመቀበል፡፡ 4. በገነት ወይንም በፓራዳይዝ አትክልት ውስጥ የሚኖረው የወደፊት ትልቅ ደስታ የተስፋ ቃል፤ 5. ለኃጢአተኞች በሲዖል ውስጥ የተጠበቀው ቅጣት ማስጠንቀቂያ፤ 6. በማያምኑት ላይ የሚኖረው የእግዚአብሔር ቁጣ ገለጣ እንዲሁም ደግሞ፤ 7. ለእግዚአብሔር ስም የተሰጡ መጠሪያ ቅፅሎች ለምሳሌም መሐሪው፣ ጌታው፣ እንዲሁም ይቅር ባዩ፡፡ ከዚህም በላይ ዛይድ እና ሌሎቹም የተሐድሶ መሪዎች ሁሉ ‹ሃኒፎች› ሁሉም ይናገሩ የነበሩት የአብርሃምን ሃይማኖት ይፈልጉ እንደነበረ ነው፡፡ ከዚህም ሁሉ ባሻገር ቁርአን በተደጋጋሚ ምንም እንኳን በተዘዋዋሪ ቢሆንም አብርሃምን እንደ ሃኒፍ አድርጎ ይናገርለታል፣ ይህ ደግሞ የዛይድና የጓደኞቹ የተመረጠ ስያሜ ነበር፡፡
ሃኒፍ የሚለው ቃል መሰረት የተወሰደው ከዕብራይስጥ ነው ትርጉሙም “መሰወር፣ ማስመሰል፣ መዋሸት እና ግብዝ መሆን” ማለት ነው፡፡ በሲሪያክ ቋንቋም ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው፡፡ በአረብኛ ግን የመጀመሪያ ትርጉሙ የሚያመለክተው ነገር “ማንከስ” ወይንም “ትክክል አለመራመድ” ማለት ነው ነገር ግን ሊያመለክት የመጣው የታወቁትን አማልክት ማምለክን ስለማቆም ነው፡፡ በዚህም ስሜቱ በመጀመሪያ እነዚህን የተሐድሶዎ መሪዎችን እንደ ተቀባይነት እንደሌላቸው ለመቃወም የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ኢብን ኢሻም እንደሚነግረን በቁራይሾች የአነጋገር ዘይቤ ግን እርሱ ንስሀ መግባት እና ንፅህና ማለት ነው ከዚህም የተነሳ ይህንን እውነታ ሃኒፊዝም በሚለው ቃል ላይ ተያይዞ እናገኘዋለን፣ ስለዚህም ምናልባትም ሃኒፎቹ በደስታ ተቀብለው የወሰዱት ይመስላል ምክንያቱም እነርሱ ለጣዖታት እና ለእነርሱም እርግማን ያላቸውን ክህደት የሚገልጥላቸው ሆኖላቸዋልና፡፡ የሆነው ሆኖ ይህ አስደናቂ ነበር ሆኖም ግን መሐመድ ይህንን ቃል ለአብርሃም መስጠቱ እንዲሁም ሰዎችን ወደ አብርሃም እምነት ወደ ሃኒፊዝም እንዲመለሱ መጋበዙ እንደዚሁም እርሱ ከሚሰብከው ከእስልምና ጋር አንድ ማድረጉ የሚገርም ነው፡፡ በእርግጥ በዚህ የቃሉ አጠቃቀም መሐመድ በጣም ግልጥ በሆነው መንገድ የገለጠው እርሱ እራሱ ከተሐድሶዎቹ መሪዎች ጋር እንደተጨመረ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ እርሱን የምናገኘው የእነርሱን ትምህርት ወስዶ በቁርአን ውስጥም ማስቀመጡን ነው ስለዚህም የሃኒፎችን ዋና ትምህርት የእስልምና አንዱ ዋናው ምንጭ መሆኑን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም፡፡
ሃኒፎች ብቅ እያለ ለነበረው እስልምና እንደዚህ ዓይነት ተፅዕኖ ማምጣታቸው በጣም ተቀባይነት ያለው ነው፤ ይህም ከቤተሰብም ምክንያት ጋርም ተያይዟል፡፡ በመካ የነበሩት አራቱም ዋና ዋና የተሐድሶ መሪዎች ለመሐመድ ዘመዶቹ ነበሩ ምክንያቱም ከአንድ የዘር ግንድ ‹ከሊዋ› የወረዱ ናቸውና፡፡ ከዚህም በላይ ዑባይዱላህ ለመሐመድ በእናቱ በኩል የአክስቱ ልጅ ነበር፤ ከዚህ በፊት እንዳየነውም ሁሉ መሐመድም የዚህን የተሐድሶ መሪ ሚስት እርሱ ከሞተ በኋላ አግብቷታል፡፡ ሌሎቹ ሁለት ደግሞ ዋራካና ዑትማን በኢብን ሒሻም በተሰጠው የዘር ግንድ ላይ እንደምንማረው ሁሉ የመጀመሪያ ሚስቱ የከዲጃ የአጎት ልጆች ነበሩ፡፡
የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡
ከዚህ በላይ እንዳየነው በእስልምናና በቁርአን ላይ ምንጭ ሆነው ስላገለገሉት የመሐመድ ጎሳና በጊዜው የነቁ የአረብ የተሐድሶ መሪዎች እምነትና እንቅስቃሴ ነው፡፡ ታሪኩ አስገራሚና አሁንም በዚያን ጊዜ እንደነበሩት ሰዎች ጥያቄ የሚጠይቁ እውነት ፈላጊዎች መነሳት እንዳለባቸው የሚጠቁም ነው፡፡
የተሐድሶ መሪዎቹ እውነተኛውን አምላክና አምልኮ ፈልገው ነበር፣ ለዚህም ከጣዖታት አምላኪዎቹ ስደትን ተቀብለዋል፡፡ ያመጡትን አጠቃላይ ለውጥ ስንመለከት ግን ፍለጋቸው ዳር ያልደረሰ ጥማታቸውን ያላረካ ፍለጋ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ምክንያቱም ከዚያ የቀጠለውና እስካሁን ያለው እምነት ለሰዎች የነፍስ ጥያቄ የሚሰጠው ምንም መልስ የለውምና ነው፡፡
እኛ ሰዎች ሕያው የሆነች ነፍስ አለን፣ ነፍሳችን ዘላለማዊ መንፈሳዊ አካላችን ናት፡፡ በነፍስ መኖር የተነሳ እኛ እናስባለን፤ እናቅዳለን፤ ስሜት አለን፣ እናውቃን፣ እንወዳለን፤ እንጠላለን ወ.ዘ.ተ፡፡ ነገር ግን ይች ምስጢራዊ የሆነችውና እኛን ከእንሰሳው ዓለም ሙሉ ለሙሉ ልዩ ያደረገችን ነፍሳችን በኃጢአት ምክንያት ማወቅ ያለባትን አምላኳንና ፈጣሪዋን ማወቅና እርሱን እንደ እራሱ ፈቃድ ማምለክ አልቻለችም፡፡
ይህ ብቻ አይደለም የዘላለም የሲዖል ፍርድ አሁንም ያለባት ወደፊትም የሚጠብቃት ሆናለች፡፡ ለዚች ለነፍሳችን ዋናውና ትልቁ ነገር እንደገና ልግለጠው ዋናው አስፈላጊ ነገር ከፈጣሪዋ መታረቅና እርሱ ያዘጋጀላትን መንግስት ለመውረስ አዲስ ተፈጥሮን ከእርሱ እጅ መቀበል ነው፡፡ ይህንን እውነት ማንኛውም የምድር ሃይማኖት ሊሰጥ ወይንም ሊያስገኝ አይችልም፡፡
ይህንን ለማስገኘት የሚችለው እራሱ እግዚአብሔር ለሰዎች ከቸርነቱ የተነሳ የሚሰጠው የነፃ የፀጋ ስጦታ ነው፣ ይህም ስጦታ የተገለጠው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ለብሶ መምጣትና በመስቀል ላይ መሞት ብቻ ነው፡፡
ይህንን አስደናቂ የአዲስ ሕይወት ስጦታ ከእግዚአብሔር እጅ በነፃ ለመቀበል ኃጢአታቸውን ተናዝዘው በእምነት ለሚመጡት ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልዩ ልዩ ቦታዎች ላይ እናነባለን፣ እንደቃሉም ብዙዎች አዲስ ሕይወት ከእርሱ ተቀብለዋል፡፡
የዚህ ገፅ አዘጋጆች ዋና ዓለማና ለአንባቢዎች የሚያበስሩት የምስራች ይህንን ታላቅ የነፃ ስጦታ ከእግዚአብሔር ዘንድ መቀበል የሚችሉበትን ግንዛቤ እንዲያገኙ መጽሐፍ ቅዱስ በማግኘት እንዲያነቡና ወደ ቤተክርስትያን እንዲሄዱ ነው፡፡
እግዚአብሔር በምህረቱና በፀጋው ይርዳችሁ፡፡
የትርጉም ምንጭ: THE ORIGINAL SOURCES OF THE QUR'AN
ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ: የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች
ለእስልምና መልስ አማርኛ ዋናው ገጽ