የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች

ምዕራፍ አምስት ክፍል አንድ

በቁርአንና በእስልምና ልማድ ውስጥ የዞሮአስተሪያን ነገሮች

REV. W. ST. CLAIR TISDALL, M.A., D.D

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

2. የመሐመዳውያን ገነት ከሁሪሱ ጋር

ከእነዚህ ጋር የጊልማንና የጂኒዎችን፣ የሞት መልአክን እና የዳራቱ ካይናትን ነገር አንድ ላይ እናመጣለን፡፡ ቁርአን ገነትን በተመለከተ ስለሚሰጠው ገለጣዎች ምሳሌ የሚከተለውን እንጠቅሳለን፡-

‹በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ጌቶች አሉት ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? የቀንዘሎች ባሌቶች የሆኑ (ገነቶች አሉት) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በሁለቱ ውስጥ የሚፈሱ ሁለት ምንጮች አሉ፡፡ ከጌታቸሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በሁለቱ ውስጥ ከፍራፍሬዎች ሁሉ ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አልሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? የውስጥ ጉስጉሳቸው ከወፍራም ሐር በኾኑ ምንጣፎች ላ የተመቻቹ ሲኾኑ (ይንፈላሰሳሉ) የሁለቱም ገነቶች ፍሬ (ለለቃሚ) ቅርብ ነው፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎቸእ በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጃንም ያልገሰሳቸው ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? ልክ ያቁትና መርጃን ይመስላሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? የበጎ ስራ ዋጋ በጎ እንጂ ሌላ ነውን? ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? ከሁለቱም ገነቶች ሌላ ሁለት ገነቶች አልሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? ከልምላሜያቸውም የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? በውስጣቸው ሁለት የሚንፈዋፉ ምንጮች አልሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? በውስጣቸውም ፍራፍሬ ዘምባባም ሩማንም አልለ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልከ ውቦች (ሴቶች) አልሉ፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? ከነሱ በፊት ሰውም ጃንም አልገሰሳቸውም፡፡ ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲኾኑ (ይቀመጣሉ)፡፡ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላለችሁ? የግርማና የመከበር ባለቤት የኾነው ጌታህ ስም ተባረከ፡፡› ቁርአን 55.46-78፡፡

እንደገናም በቁርአን 56.11-38 ላይ የምናገኘው በገነት ውስጥ የሚገኘውን ደስታ ተመሳሳይ ዘገባን ነው ‹እነዚያ ባለሟሎች ናቸው በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲኾኑ ከፊተኞቹ ብዙ ጭፍሮች ናቸው፡፡ ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው በተታቱ አልጋዎች ላይ ይኾናሉ፡፡ በርሷ ላይ የተመቻቹና ፊት ለፊት የተቅጣጩ ሲኾኑ በነሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ ከጠጅ ምንጭም በብርጭቆዎችና በኩስኩስቶች በጽዋም (በነሱ ላይ ይዞራሉ)፡፡ ከርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም አይሰክሩምም፡፡ ከሚመርጡትም ዓይነት በእሸቶች፡፡ ከሚሹትም በኾነ የበራሪ ሥጋ (ይዞሩባቸዋል)፡፡ ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎች አሏቸው፡፡ ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡ በውስጥዋ ውድቅ ንግግርንና መወንጀልንም አይሰሙም፡፡ ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡ የቀኝም ጓዶች ምንኛ (የከበሩ) የቀኝ ጓዶች! በተቀፈቀፈ (እሾህ በሌለው) ቁርቁራ ውስጥ ናቸው፡፡ (ፍሬው) በተነባበረ በሙዝ ዛፍም፡፡ በተዘረጋ ጥላ ሥርም፡፡ በሚንቧቧ ውሃ አጠገብም፡፡ ብዙ (ዓይነት) በኾኑ ፍራፍሬዎችም የማትቋረጥም የማትከለከልም የኾነች፡፡ ከፍ በተደረጉ ምንጣፎችም (ሴቶችም መካከል)፡፡ እኛ አዲስ ፍጥረት አድርገን (ለነሱ) ፈጠርናቸው፡፡ ደናግሎችም አደረግናቸው፡፡ ለባሎቻቸውም ተሸሞርሟሪዎች እኩያዎች (አደርግናቸው) ለቀኝ ጓዶች (አዘጋጀናቸው)፡፡›

እዚህ ላይ የምንመለከተው ነገር አብዛኛው የነዚህ ገለጣዎች ከፐርሺያውያንና ከሒንዱዎች የገነት ሐሳቦች ላይ የተወሰዱ መሆናቸውን ነው፡፡ ብዙዎቹ በጣም የማይጥሙት ዝርዝሮች እና ፅንሰ ሐሳቦች የመሐመድ የራሱ የስሜታዊነት ተፈጥሮ ውጤቶች መሆናቸው ጥርጥር የሌለው ነገር ቢሆንም፡፡

የቆንጆዎቹ ሐሳብ የመጣው ስለ ፔራካስ በተነገረ ከጥንታዊ የፐርሺያ አፈታሪክ ነው፣ እርሱም በዘመናዊ የኢራን ሕዝቦች ፓሪስ ተብሎ ይጠራል፡፡ አፈታሪኩም እነዚህ ዞሮ አስተሪያንስ የገለጧቸው ሴት መናፍስት በአየር ውስጥ የሚኖሩ እና ከከዋክብትና ከብርሃን ጋር በጣም የተቀራረቡ ናቸው ይላሉ፡፡ እነርሱም በጣም ቆንጆዎች ስለሆኑ የሰዎችን ልብ ይሰርቃሉ፡፡ በአረብኛው ቁርአን ውስጥ ለእነርሱ የተጠቀሰው ቃል ‹ሁር› የሚለው ቃል የገነት ቆንጆዎቹ የተገለጡበት ቃል በአጠቃላይ ከአረብኛ የመጣ ቃል ነው እናም ‹ጥቁር አይን ያላቸው› ማለት ነው፡፡ ይህም ሊሆን የሚችል ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ምናልባትም በአብዛኛው የፐርሺያውያን ቃል ይመስላል ከአቨስቲክ ቃል ‹ሃቫር› እንዲሁም ከፓላቪ ‹ሁር› ከሚለው ምናልባትም የመጣ ይሆናል፣ እንደዚሁም በዘመናዊ ፐርሺያ ‹ኩር› በመጀመሪያ የሚለው ‹ብርሃን›፤ ‹ብሩህነት›፤ ‹ፀሐያማ› እናም በመጨረሻው ‹ፀሐይ›፡፡ አረቦቹ የነዚህን ብሩህ እና ‹ፀሐያማ› ሴቶችን ፅንሰ ሐሳብ ከፐርሺያኖች በተበደሩበት ጊዜ ምናልባትም በጣም ሊገልጣቸው የሚችለውንም ቃል ተበድረዋል፡፡ አረቦችም ትርጉሞችን በቋንቋቸው ሊገልጥ የሚችልን ቃል መፈለግ ልማዳቸው ነበረ ይህም ልክ እንደ ‹አስፓራገስ› በእንግሊዝኛ የ‹ስፓሮው ግራስ› እንደሆነውና እንደሚለው ማለት ነው (ኢትዮጵያዊ ምሳሌ ማስቀመጥ)፣ ‹ሪንጌድ› ‹ሩናጌት› ‹ጊራሶል› የ‹ኢየሩሳሌም› የሚበላ የአበባ እንቡጥ፣ ወይንም ሌላ ደግሞ በግሪክ የአረብኛው ቃል ዋዲ፤ ግሪካዊ በመሆን በ‹ዖኣሲስ› መልክ እንደተቀመጠው፣ እና ከ‹አውኦ› መጣ እንደሚባለው፣ እነዚህ ሁሉ ያለምንም ጥርጥር በlucus a non lucendo መርሆ መሰረትን ተጠቅመዋል (ይህ መርሆ የሚገልጠው የበፊቱ ቃል ትርጉም እንዲሰጥ የኋለኛውን ቃል የመጠቀም መርሆ ነው)፡፡ ፊርዳውስ እራሱም በቁርአን ውስጥ ለፓራዳይዝ ወይንም ገነት ከዋሉት ቃላት አንዱ ቢሆንም እራሱ የፐርሺያ ቃል ነው ከዚያም ቋንቋ የመጡት ብዙዎቹ ቃላት ከዚህ በላይ በተረጎምነው አንቀፅ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ‹ሁር› የሚለውን ቃል አመጣጥ ማረጋገጥ ያን ያህል እውነተኛ ጠቃሚነት ያለው ነገር አይደለም፡፡ ቃሉ እንዲገልጣቸው የታቀዱት አካላት በተለይም የአርያን ምንጭነት ያላቸው ናቸው ልክ እንደ ጊልማን፡፡ ሒንዱዎች በሁለቱም መኖር ያምናሉ ስለዚህም ሁሪስን በሳንስክሪት ውስጥ አፕሳራሳስ እንዲሁም ጊልማንን ጋንዳርቫስ በማለት ጠርተዋል፡፡ ምንም እንኳን ምድርን ብዙ ጊዜ ቢጎበኙም እነርሱ የተገመቱት በሰማይ እንደሚኖሩ ነው፡፡ 

በፓራዳይዝ (ገነት) በሁሪስ የሚደረገው አቀባበል ሁኔታ እጅግ በጣም ብዙ ደፋር የመሐመዳውያን ወጣት ተዋጊዎችን በጦርነት ውስጥ በድፍረት ለመሞት እንዲሮጡ እንዳደረጋቸው የሙስሊም ታሪክ አዋቂዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ይህ እምነት በጦር ሜዳ ፊት ለፊት ካለው ቁስላቸው ጋር የሞቱት ስለሚሸለሙት ሽልማት ከሚናገረው ከጥንታዊው የአሪያን ሐሳብ ጋር በጣም ይመሳሰላል፡፡ ምክንያቱም ማኑ በ‹ዳርማሳስትራ› እንደሚከተለው ብሏልና፡-

‹የምድር ጌቶች በጦርነት የተጋደሉት እርስ በእርስ ለመገዳደል የሚመኙት እንዲሁም ፊቶቻቸውን ሳያጥፉ ከዚያ በኋላ በጉብዝናቸው አማካኝነት ወደ ሰማይ ይሄዳሉ› እንደዚሁም በ‹ናሎፓክያናም› ውስጥ እኛ የምናገኘው ኢንድራ ለጀግናው ናላ እንደሚከተለው ሲናገር ነው፡ ‹ፍፁም የምድር ጠባቂው ሆይ (ንጉሱ) የምድርን ማንኛውንም ተስፋ የጣሉት ተዋጊዎች በጊዜው በጦር መሳሪያ አማካኝነት ወደ ኋላ ፊታቸውን ሳይመልሱ የጠፉቱ ለእነርሱ የማይጠፋው ዓለም ይሆንላቸዋል› ማለትም የኢንድራ መንግስተ ሰማይ ይሰጣቸዋል፡፡ እንደዚሁም ይህ ሐሳብ በሕንድ ብቻ የተወሰነ አይደለም የእኛም የሰሜን የጥንት አባቶች (ጸሐፊው እንግሊዞችን መጥቀሱ ነው) በአሕዛብነት ጊዜያቸው የሰማያዊ ‹ቫለኪሬስን› ወይንም ‹የታረዱትን መራጮች› ያምኑ ነበር፡፡ እነርሱም የጦር ሜዳዎችን ይጎበኛሉ የታረዱትንም ወደ ‹ዖዲን› ሰማይ ተሸክመዋቸው ይሄዳሉ ወደ ‹ቫልሃላ› ወደ ‹ወደታረዱት አዳራሽ› የጀግኖች ተዋጊዎች መንፈስ ወዳለበት በጦርነት ወደ ወደቁት ይወስዷቸዋል፡፡

ጂኒዎች ክፉዎችና መጥፎ ዓይነት መናፍስት ናቸው እነርሱም ታላቅ ኃይል ያላቸውና በብዙ የሙስሊሞች ዓለም ውስጥ የስቃይ ምንጮች ናቸው፡፡ እነርሱም ልክ እንደ መልአክትና እንደ ሰይጣናት በጣም ብዙ ጊዜ በቁርአን ውስጥ እንደተጠቀሱ፣ የሰለሞን አገልጋዮች እንደሚባሉ፣ ከእሳት የተሰሩ እንደተባሉ ሁሉ አይተናል፡፡ ጂኒ የሚለው ቃሉ እራሱ  ፐርሺያዊ ይመስላል ምክንያቱም ነጠላው ቃል ጂኒ የአቭስታው ጃይኒ ማለትም የኃጢአተኛዋ (የሴት) መንፈስ ነውና፡፡

የመሐመዳንን አፈታሪክ ምንጭ በመመርመር ጥያቄ ውስጥ ሚዛንን በተመለከተ ቀደም ሲል በልማድ ውስጥ ያገኘነውና አሁን  በሚራጅ ልማድ ውስጥ ደግሞ አዳም ወደ ሰማይ ሲመለከትና በግራ እጁ በኩል ‹ጥቁር ነገሮችን› (አል አሰዊዳ) ሲያይ ሲያለቅስ፣ ነገር ግን በቀኝ በኩል ወዳሉት ዘወር ብሎ ሲመለከት ደግሞ ሲደሰት እንዳየው መሐመድ አይተናል፡፡

ጥቁሮቹ ምስሎች ገና ያልተወለዱት ዘሮቹ መናፍስት ናቸው፡፡ እነርሱም በአጠቃላይ የተጠቀሱት ‹የሚኖሩት አቶሞች› (አዱ ዳራቱል ካይናት) ተብለው ነው፡፡ እነርሱም በ‹አብርሃም ኪዳን› (ማለትም የዚያ ተረት ዋና ክፍል ከተወሰደበት) ላይ ከተጠቀሱት የተለዩ ናቸው፣ በእርግጥ በኋለኛው መጽሐፍ፣ አብርሃም የሞቱትን ዘሮቹን መንፈሶች አይቷል፡፡ በመሐመዳን ልማድ ውስጥ ግን እርሱ ያየው ገና ያልተወለዱትን ሲሆን እነርሱንም ያየው እንደ ‹የሚኖሩ ንጥረ ነገሮች (አቶሞች)› ነው፡፡ በመሐመዳን ልማድ የሃይማኖት ስራ ውስጥ እነዚህ አካላት የሚታወቁበት ስም ያለምንም ጥርጥር አረብኛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሐሳቡ የመጣ የሚመስለው ከዞሮአስተሪያን ነው ከእነርሱም ውስጥ እነዚህ አካላት ይጠሩ የነበረው በአቨስታውያን ‹ፍራቫሺስ› በመባል ሲሆን   በፓላቪ ደግሞ ‹ፈሩሃርስ› ተብለው ነው፡፡ አንዳንዶች ያ ምናልባት ፐርሺያውያን ከጥንት ግብፃውያን  የወሰዱት ነው በማለት ይመኛሉ ነገር ግን ይህ በጣም የማይሄድ ይመስላል፡፡ ይህ ይሁን ወይንም አይሁን ሙስሊሞች  ‹ነፍስ ቀድሞ ትኖር ነበር› ለሚለው እምነታቸው ዞሮአስተሪያኖች ላላቸው ‹የሰዎች ነፍስ ቀድሞ (ከመወለድ በፊት) መኖር› እምነት ባለዕዳዎች ናቸው፡፡

አይሁዳውያን እንደሚያደርጉት ሁሉ ሙስሊሞችም ስለ ‹የሞት› መልአክ ይናገራሉ፡፡ ምንም እንኳን አረቦቹ ስሙን ‹ሰማኤል› ሲሉና፣ አይሁዶቹ ደግሞ ‹አዝራኤል›  ብለው ቢጠሩትም እንኳን የኋለኛው ስም (የሙስሊሞቹ) አሁንም አረባዊ ሳይሆን ዕብራዊ ነው፡፡ ይህም እንደገና የሚያሳየው አይሁዶች ብቅ እያለ በነበረው እስላም ላይ ስከተሉትን መጠነ ሰፊ ተፅዕኖ ነው፡፡ የዚህ መልአክ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለመጠቀሱ አይሁዶችና ሙስሊሞች ስለ እርሱ የሚናገሩት ነገር ከአንድ ሌላ ምንጭ የተወሰደ የመሆኑ ነገር እርግጠኛ ነው፡፡ ይህም ምናልባትም ከፐርሺያ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም አቨስታ የሚነግረን አስቶቪዶቱስ ወይንም ቪዳቱስ ስለሚባል መልአክ ነውና እርሱም ‹ከፋፋዩ› ይባላል፡፡ የእርሱም ተግባር አካልን ከመንፈስ መለያየት ነው፡፡ አንድ ሰው በውሃ ውስጥ ከወደቀ፣ ወይንም ለሞት ከተቃጠለ ወይንም ከጠለቀ ዞሮአስተሪያኖች የያዙት ይህ ሞት ከእሳቱ ወይንም ከውሃው የተነሳ አይደለም ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ለሰዎች ልጆች ጥሩዎች እንጂ ጎጂዎች አይደሉም ተብለው ስለሚታመኑ ነው፡፡ ይህንን የሚያደርገው የሞት መልአክ ቪዳቱስ ነበር፡፡

3. የአዛዚል ከሲዖል ውስጥ ማረግ

አዛዚል እንደሙስሊም ልማድ ከሆነ የሰይጣን ወይንም የኢብሊስ የመጀመሪያው ስም ነበር፡፡ ስሙ ዕብራዊ ነበር እንዲሁም በሌዋውያን የመጀመሪያ ጽሑፍ ላይ ይገኛል (ሌዋውያን 16. 8፣ 10፣ 26)፡፡ ነገር ግን የዚህ ንግግር ጅማሬ ሙሉ በሙሉ አይሁዳዊ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ዞሮአስተርያን ነው፣ ይህም በሙስሊሞችና በዞሮአስተሪያውያን መካከል ያለው ንፅፅር እንደሚያረጋግጠው ነው፡፡

በቂሳሱል አንቢያ (ገፅ 9) የምናነበው ‹ታላቁ እግዚአብሔር አዛዚልን ፈጠረው፡፡ አዛዚል ታላቁን እግዚአብሔርን አመለከ ለአንድ ሺ ዓመታት በሲጂን ውስጥ፡፡ ከዚያም እርሱ ወደ ምድር መጣ፡፡ በእያንዳንዱም ታሪክ ውስጥ እርሱ ታላቁን እግዚአብሔርን ለአንድ ሺ ዓመታት አመለከ  በመሬቱ ላይ እስከመጣበት ድረስ፡፡ ‹ሰዎች የሚያርፉበት ከፍተኛው ታሪክ፣  ከዚያ በኋላ ከኢሜራልድ የተሰሩ ጥንድ ክንፎችን እግዚአብሔር ሰጠው በእነዚያም እርሱ ወደ መጀመሪያው ሰማይ ይወጣባቸዋል፡፡ እዚያም ለአንድ ሺ ዓመታት አመለከ ከዚያም ወደ ሁለተኛው ሰማይ ለመድረስ ቻለ፡፡  እንደዚያ እያለ ይቀጥላል በእያንዳንዱ ደረጃ ለአንድ ሺ ዓመታት እያመለከ በእያንዳንዱ ወደ ላይ ከፍ ባለበት ደረጃ ሁሉ ላይ በእያንዳንዱ ሰማይ ላይ ካሉት የመላእክት ነዋሪዎች ዘንድ ልዩ የሆነ ስምን እየተቀበለ ወጣ፡፡ በዚህ ዓይነቱ አፈታሪክ በአምስተኛው ሰማይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አዛዚል በመባል ተጠራ፡፡ ከዚያም እርሱ ወደ ስድስተኛውና ሰባተኛው ሰማይ ወጣ  ከዚያም እጅግ ብዙ የሆነ አክብሮትን አቀረበ ስለዚህም በምድርም ወይንም በሰማይ እርሱ እራሱ ያልሰገደበት ቦታ ነጠላ ነጥብ የሰውን እጅ መዳፍ የሚያክል እንኳን ቦታ አልቀረውም፡፡ ከዚያም በኋላ የተነገረን ነገር ለአዳም አልሰግድም ባለው ኃጢአት የተነሳ ከፓራዳይዝ ተባሮ እንደተጣለ ነው፡፡ የአራይሱል ማጂሊስ የሚነግረን ኢብሊስ በመባል ተጠርቶ ለሦስት ሺ ዓመታት ቀርቷል፣ በነዚህም ዓመታት በፓራዳይዝ (በገነት) በር ላይ ሆኖ በአዳምና በሔዋን ላይ አንድ ጉዳትን ለማድረስ ተስፋ በማድረግ ላይ ነበር፣ የእርሱ ልብ በእነርሱ ላይ ክፋትን የተሞላና መጥፎ ምኞት ነበረውና፡፡

አሁን ዞሮ አስተሪያውያን ‹በቡንዳሂሽኒህ›  የስሙ ትርጉም ‹ፍጥረት› በሆነው የፓላቪ ስራ ውስጥ  ስለሰጡት ተመሳሳይ ዘገባ እንመልከት፡፡ በፓላቪ የክፉው መንፈስ አሪማን ተብሎ ይጠራ እንደበረ መገንዘብ ያስፈልጋል እርሱም የመጣው አንሮ ሜንዩስ (‹አጥፊው አዕምሮ›) ከሚለው ሐሳብ ነው፣ ይህም አቨስታ በመባል የሚታወቅበት ስያሜ ነው፡፡

ስለዚህም ‹በቡንዳሂሽኒህ› የመጀመሪያና ሁለተኛ ምዕራፎች ውስጥ የምናነበው ነገር፡-

‹አሂርማን በጭለማ ውስጥ ነበር አሁንም ነው ከእውቀት በኋላ አደጋ ለማድረስ ፈለገ፣ እንዲሁም በጥልቁ ውስጥ ... ያንንም ጎጂነት እና ያንን ጨለማ ደግሞም የጨለማው ግዛት (ክፍል) በማለት የሚጠሩት ቦታ ነው፡፡ ዖርማዝድ በሁሉን አዋቂነቱ ያወቀው አሂርማን በሕይወት እንደሚኖር ነው ምክንያቱም እርሱ፡ ‹ያም አሂርማን ‹እራሱን እስከ መጨረሻው ድረስ የሚያስደስተው እና የሚያደባልቀው ከቅናት ጋር ነው፣ እነርሱም (ዖርማዝድና አሂርማን) ለሦስት ሺ ዓመታት ያህል በመንፈስ ነበሩ፡፡ አሂርማን በእርሱ የሚሆነውን በማወቅ ዘገባ ውስጥ የዖርማዝድን መኖር አያውቅም ነበር፡፡ በመጨረሻም ከጥልቁ ውስጥ ወጣ በብሩህም ቦታ ላይ ሆነ እርሱም የዖርማዝድን ብሩህነት ካየ በኋላም በጎጂነት ምኞቱና በቅናት ሁኔታው ለመጥፋት በጣም ተግቶ ነበር›፡፡

በእርግጥ እኛ በሁለት አምላክ (አንድ ክፉና አንድ ደግ አምላክ) አምላኪዎቹ በዞሮአስተሪያኖችና አንድ አምላክ አምላኪዎች ናቸው በመባል በሚታሰቡት በሙስሊሞቹ መካከል ባሉት አፈታሪኮች ከውጭው ቅርፅ አንዳንድ ልዩነቶችን እናገኛለን፡፡ ስለዚህም በቀደመው (በዞሮአስተሪያንስ) የክፉው መርሆ የዖርማዝድ ፍጡር አይደለም እንዲሁም (አሂርማን) የእርሱንም መኖር ከመጀመሪያውም አያውቅም በኋለኛው (በሙስሊሞቹ) ግን እርሱ የእግዚአብሔር አንዱ ፍጡር ሆኖ ይታያል፡፡ በመሐመዳውያን ተረት ውስጥ እርሱ ቀስ በቀስ ወደ ላይ እያረገ ወጣ በአምልኮውና (በመሰጠቱ) በዞሮአስተሪያውያን ውስጥ ግን መሰጠት ወይንም አምልኮ ምንም እንደሚያመጣ አልተቆጠረም፡፡ ነገር ግን በሁለቱም ሁኔታ ክፉው መንፈስ የኖረው በጨለማና በድንቁርና ሲሆን ወደ ብርሃንም መጥቷል በሁለቱም ዘገባ ክፉው እራሱን ያስቀመጠው የእግዚአብሔርን ፍጥረታት በክፉ ፈቃድና በቅናት  ለማጥፋት በመስራት ላይ ነው፡፡ በዞሮአስተሪያውያን አስራ ሁለት ሺ ዓመታቱ ሐሳብ መሠረት በክፉና በመልካም መካከል የተካሄደው ጦርነት በአራት የሦስት ሺ ዓመታት ክፍለ ጊዜዎች የሚከፋፈል ነው፡፡ ለዚህም የሚሆነን ማገናዘቢያ የሚገኘው አዛዚል ሦስት ሺ ዓመታት አዳምን ለማጥፋት (ለመጉዳት) የጠበቀበት ጊዜ የሚባለውን አንብበናል፡፡

ይህንን ርዕስ ከመተዋችን በፊት ፒኮክ በሁለቱም በመሐመዳንም በዞሮአስተርያንም ተረቶች ውስጥ ከክፉ መናፍስት ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑን መጥቀስ አስገራሚ ይሆናል፡፡ በቂሳዑል አኒቢያ የተነገረን ነገር ኢብሊስ በፓራዳይዝ በር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ተቀምጦ ነበር ይህም አዳምንና ሄዋንን በኃጢአት ለመፈተን መግባት የሚችልበትን ዕድልን እየጠበቀ ነበር፣ ፒኮክ ደግሞ በግምቡ ላይ ተቀምጦ ነበር፣ ከመጠበቂያዎቹ በአንዱ አናትም ላይ ነበር፣ እርሱንም (ክፉውም እርሱን) በጣም በተሰጠ ሁኔታ የታላቁን እግዚአብሔርን የከበረ ስም እየደጋገመ ሲጠራ አየው፡፡ በእንደዚህ መሰጠት ውስጥ በመሆኑ በመደነቅ ፒኮኩ ይህ በጣም የተሰጠ ማን እንደሆነ ጠየቀ፡፡ ኢብሊስም መለሰ ‹እኔ ከእግዚአብሔር መላእክት አንዱ ነኝ እርሱ ይክበር ከፍ ይበልም› አለው፡፡ እርሱም ለምን እዚያ እንደተቀመጠ (በፒኮክ) ሲጠየቅ የሚከተለውን መለሰ፡ ‹እኔ ወደ ፓራዳይዝ (ገነት) እየተመለከትሁ ነው እንዲሁም ለመግባት እፈልጋለሁኝ›፡፡ ፒኮክም እንደ ጠባቂ ስለነበር እንደሚከተለው መለሰለት ‹አዳም በውስጥ እስካለ ድረስ ማንንም እንዳስገባ ምንም ትዕዛዝ የለኝም› አለው፡፡ ነገር ግን ኢብሊስ እንዲያስገባውና እንዲፈቅድለት ለእርሱ መማጃን ሰጠው፤ ፀሎትንም እንደሚያስተምረው፤ እርሱንም ቢደጋግመው የማያስረጅ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር ላይ ከማመፅ የሚጠብቀውንና ከፓራዳይዝ በፍፁም እንዳይወጣ የሚያደርገውን ፀሎት እንደሚያስተምረው ቃል ኪዳንን ገባለት፡፡ በዚህም ጊዜ ፒኮክ ከመጠበቂያው ላይ በርሮ በመውረድ ለእባቡ የሰማውን ሁሉ ነገረው፡፡ ይህም ለሔዋን  ከዚያም ለአዳም መውደቅ ምክንያት ሆነ፡፡ ስለዚህም ታላቁ እግዚአብሔር አዳምን፣ ሔዋንን ፈታኙን እና እባባን ከፓራዳይዝ (ከገነት) ወደ ምድር አስወጣቸው፣ ፒኮክንም ከእነርሱ ጋር ወደ ታች ወረወረው፡፡

ዞሮአስተሪያኖች በአሂሪማንና በፒኮክ መካከል ግንኙነት እንዳለ እንደሚያምኑ ማስተዋልም እዚህ ላይ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በብዙ ሁኔታዎች ላይ የተጠቀሰው የአርመኒያን ጸሐፊ ኢዘኒክ በእርሱ ጊዜ ስለነበሩት ዞሮአስተሪያኖች የነገረን ነገር ‹እነርሱም አሂርማን ተናግሯል ብለው የተናገሩት፡ ‹እኔ አንዳች መልካምን ነገር ለማድረግ አልችልም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን አደርጋለሁ› አለና ይህንንም ለማረጋገጥ እርሱ ፒኮክን ሰራ› የሚሉትን ነው፡፡

በዞሮአስተሪያን ተረት ውስጥ ፒኮክ የአሂርማን ፍጡር ከሆነ በመሐመዳን ታሪክ ውስጥ ኢብሊስን መርዳቱና ከፓራዳይዝ ውስጥም ከእርሱ ጋር መጣሉ አያስደንቀንም፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በቁርአን 55 እና 56 ላይ ስለ መንግስተ ሰማይና ሲዖል የተገለጡት ሃሳቦች ከየት መጡ? ምንጫቸው እግዚአብሔር ነውን ወይንስ ማንና ምን? ለሚሉት ጥያቄዎች መልሱ ከዚህ በላይ ግልጥ ነው፡፡ ጥቂት የአይሁድ ምንጭነት ቢኖራቸውም ሁሉም ሐሳቦች የተወሰዱት ከዞሮአስቲያንስ የፐርሺያ ትምህርት ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጡ ጽሑፎችና ዘገባዎች በግልጥ አይተናል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ከዚህ የሚከተለውን ጥያቄ ሊጠይቅ ይችላል፣ የምከተለው እምነት ከጥንት የጣዖት አምላኪዎች አፈታሪክ ላይ የተወሰደ ከሆነ እንዴት ከእግዚአብሔር መጣ ብዬ እቀበለዋለሁ? ከእግዚብሔር ካልሆነስ መጨረሻዬ ምን ይሆናል? የጥንት ፓጋን ተረትን ከእግዚአብሔር የመጣ ነው በማለት ማመኔ በመንግስተ ሰማይ ተቀባይነት ሊያስገኝልኝ ይችላልን? መልሱ አይችልም ነው፡፡

በዚህ ምድር ላይ አምነን የምንከተለው እምነት ዘላለማዊ ውጤት አለው፣ ስለሆነም በቀላሉ ልንመለከተው አይገባንም፡፡ ሰዎች ወደ ትክክለኛው እምነት እንዲመጡ እግዚአብሔር ይፈልጋል፣ ትክክለኛውንና ለጤነኛ አዕምሮ የሚመቸውን እውነተኛም የሆነውን ማንነቱን እግዚአብሔር እራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግልጥ አድርጎልናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ዘላለማዊ ጠቀሜታ ካገኙት ሰዎች መካከል የዚህ ገፅ አዘጋጆች ይገኙበታል፡፡ ስለዚህም አንባቢዎች መጽሐፍ ቅዱስን ፈልገው በማግኘት እንዲያነቡና ክርስቶስ ኢየሱስ ስለምን ወደ ምድር መምጣት እንዳስፈለገው እንዲመረምሩ ይጋብዛሉ፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ይወዳል ወደ ዘላለም መንግስቱ እንዲመጡ የሚያስችለውን መንገድ በሞቱና በትንሳኤው ከፍቶልናል፡፡ ወደ እርሱ በፀሎት ኑና   ይቅር እንዲላችሁና ወደ መንግስቱ እንዲያስገባችሁ ጠይቁት ለምን በውጪ ትቀራላችሁ? እግዚአብሔር በፀጋው ኃይል ይርዳችሁ! አሜን፡፡

የትርጉም ምንጭ: THE ORIGINAL SOURCES OF THE QUR'AN 

ሙሉ መጽሐፉ በአማርኛ:  የቁርአን የመጀመሪያ ምንጮች

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ