መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና

በባልታዛር እና አብደናጎ

ክፍል ሁለት

ምሳሌዎች ከቅርብ ዘመን ታሪኮች

ስለዚህ ከተለመዱት የመስጊድ ማኅበራዊ-ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ-ትምሕርታዊ ተግባራት ባለፈ ፖለቲካዊ ሚናውንም መመልከት ያስፈልገናል። እስላማዊ ምሑራን ስለ መስጊድ ፖለቲካዊ ሚና የተናገሩትን ለማጤን ከዚህ በታች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያየ ስፍራ የተከሰቱ ታሪኮችን አስቀምጠናል።

ካይሮ፦ መሐመድ በመዲና ከሚገኘው መስጊዱ ሰራዊቱን ለጀሀድ እንደላከው ሁሉ የአል አዛህር መስጊድ ምሑራን አብደላ አል ሻርቃዊና አሕመድ አልዳርዴር ግብፃውያኑን ከፈረንሳዮች ቅኝ አገዛዝ ይቃወሙ ዘንድ መርተዋቸዋል። በ1919 በብሪታኒያ ላይ በተካሄደው አመፅ ጊዜም የአል አህዛር መስጊድ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል። የብሪታንያ ኃይሎች ምሑራኑ ወይም ተማሪዎቻቸው ቀጣይ እርምጃ መውሰዳቸውን እንዲያቆሙ ሲሉ ከአል አህዛር መስጊድ ውጪ በተጠንቀቅ መጠባበቅ ነበረባቸው።

ሀሰን አል ባና እና የእርሱ ሰዎች እንዲሁም ጋማ ኢስላሚያ በጀሀድ በከፍተኛ ሁኔታ ከመሳተፋቸው የተነሳ የግብፃውያን መንግስት አያሌ መስጊዶችን ለመዝጋት ተገድዶ ነበር።

ትራንስጆርዳን፦ በ1936 በፍልስጤም በሚገኘው የአል ኢስቲቅላል መስጊድ የቃሲም አብዮት ተመርቆ ተከፈተ። ሁሉም የምስጢር ተቋማቶቻቸው እንዲሁም አያሌ ኮሚቴዎቻቸው የተመሠረቱት እና ሥራቸውን ያከናውኑ የነበረው በዚሁ መስጊድ ውስጥ ነበር።

ዌስት ባንክ እና ጋዛ፦ የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ኢንቲፋዳ ይፈጠሩ ዘንድ ዋነኛውን ሚና የተጫወተው መስጊዱ ነበር። በኢየሩሳሌም የሚገኘው የአል አቅሳ መስጊድ ሰባኪዎች የሆኑት ካቲቤዎች በአይሁዳውያን እና በእስራኤል አገዛዝ ላይ ጀሀድ ለማነሳሳት ማዕከላዊ ሚና ነበራቸው።

በኖቬምበር 30፣ 2003 በግል የዜና አገልግሎት እንደተዘገበው አብዛኞቹ በዌስት ባንክ እና በጋዛ የሚገኙ መስጊዶች በአርብ ዕለት ስብከቶቻቸውና በሀማስ እና ኢስላሚክ ጀሀድ በሚታተሙት ጥላቻን በሚያሰርፁ በራሪ ወረቀቶችና ልዩ ልዩ ሕትመቶች አማካይነት በእስራኤል ላይ የሚደረገው ጥቃት ማዕከላዊ አንቀሳቃሾች ናቸው። ዘገባው በተለይ የሚያተኩረው የአጥፍቶ መጥፋት ተልዕኮ እጩዎችን በማደራጀት እና በመመልመል ተምሳሌት እና መሪ ሆኖ በሚያገለግለው በራማላህ መስጊድ በሚገኘው አሊ ላይ ነው። እንዲያውም፣ ከዋነኞቹ አንቀሳቃሾች መካከል አንዱ የሆነውና ተፈላጊው አሸባሪ በራማላህ በሚገኘው በአብደል ናስር መስጊድ ውስጥ ተሸሸጎ ነበር። በአሁኑም ኢንቲፋዳ ቢሆን መስጊዶች ዋነኛውን ሚና መጫወታቸውን ቀጥለዋል።

የፊንስበሪ ፓርክ መስጊድ እና ሌሎቹም፡ በሎንደን በፊንስበሪ ፓርክም ሆነ በኒው ጀርሲ መስጊዶች የሚካሄዱት ስነ-ስርዓቶችና ዝግጅቶች አዲስ አይደሉም። ከውጪው የአቡ ሀምዛ እንዲሁም የሼክ ዑመር አቤል ራህማን ግላዊ የጥፋተኝነት ድርጊት ብቻ መስለው ይታዩ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ጉዳዩን በጥልቀት ከፈተሸነው በሌሎች ብዙ ስፍራዎችም ተመሳሳዩ ነገር መደጋገሙን ማስተዋል እንችላለን። ስለዚህ የኢራቅ መስጊዶች ዋነኛ ሥራ በእስልምና ጠላቶች ላይ በተለይም በአሜሪካውያን እና በአውሮፓውያን ላይ ጥቃትና ግድያን ማነሳሳት ነው። እስላማዊ ማንሰራራት ተብሎ የሚታሰበውና የሚጠራው ሁኔታ ያለ መስጊድ ተሳትፎ እውን ሊሆን በፍፁም አይችልም።

በግብፅ፣ በፓኪስታን፣ በሕንድ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በናይጄሪያ፣ በሱዳን፣ በአልጄሪያ፣ በባንግላዴሽ እንዲሁም በየትኛውም ስፍራ ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። በየትኛውም ስፍራ ያሉ መስጊዶችን ብትመለከቱ በመጀመሪያው መስጊድ አማካይነት የተቀረፀላቸውን ሚና እየተጫወቱ ነው። ከተለያየ ወቅት እና ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡት ምሳሌዎች የዚህን መደምደሚያ ተአማኒነት ያብራራሉ።

የመስጊድ ፓለቲካዊ ሚና በሸሪዓ እንደተገለፀው

መስጊድንና የሚጫወተውን ፖለቲካዊ ሚና በተመለከተ በሼክ ዩሱፍ አል ቃርዳዊ በ ኦክቶበር 29፣2001 የተደነገገው ፋትዋ የሚከተለውን አስፍሯል፦

. . . በነብያችን ሕይወት ውስጥ ሰዎች የተቀደሰና ዓለማዊ ወይም ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ብለው የሚጠሩት ልዩነት አልታየም፤ ነብያችንም ለፖለቲካ ወይም ለሌሎች የተያያዙ ጉዳዮች ከመስጊድ ውጪ የሚሄድበት ስፍራ አልነበረውም። ይህንንም ያደረገው ሃይማኖቱ እና ዓለም ይህንን ልማድ ይከተሉ ዘንድ ነው።

ነብያችን በሕይወት በነበረበት ጊዜ መስጊድ የአዋጅ ማዕከሉ፣ የሀገሪቱ ዋና ቀጣና የነበረ ሲሆን፤ ተተኪዎቹና መንገዳቸው ቅን የነበረ ከሊፋዎችም መስጊድን ፖለቲካዊ ለሆነውም ላልሆነውም ተግባራቸው ዋነኛ ስፍራ አድርገው ተጠቅመውበታል። ፖለቲካ እንደ ሳይንስነቱ ምርጥ የትምሕርት ዓይነት ሲሆን እንደ ሥራና የሙያ ዘርፍነቱም የተከበረ ነው። እጅግ አስደናቂው ነገር ከራስ እስከ ጥፍራቸው የተዘፈቁበት ፖለቲከኞች ራሳቸው ናቸው መስጊድ የፖለቲካ ግንኙነቶችን አመዛዝኖ ተሳታፊ መሆን ይገባው እንደሆነ የሚጠይቁት። በእስልምና ዘንድ ፖለቲካ በራሱ መልካም ወይም ክፉ ነገር አይደለም። እንደ ሙስሊምነታችን የመሠረተ-እምነታችን እና የአምልኳችን ክፍል ስለሆነ የሃይማኖታችን አካል ነው። መላውን ሕይወት የሚሸፍን ዘይቤ ሲሆን. . . ትክክለኛው እስልምና የመስጊድን ተልዕኮ በተመለከተ የሚያምነው ከፖለቲካ መነጠል እንዳለበት ሳይሆን በሃይማኖታቸው እና በዓለማቸው ውስጥ መልካም የሆነን ነገር እንዲያፈሩ የሚያዝዛቸው እንዲሆንና ሰዎች በመስጊድ አማካይነት እውነትን እና መልካምነትን እንዲማሩ ነው። ስለዚህ መስጊድ ሕዝቡን የመምራት እና ስለ አሳሳቢ ጉዳዮች በማሳወቅ ጠላቶቻቸውን እንዲመለከቱ የማድረግ ሚና ሊጫወት ይገባዋል። ከጥንት ጀምሮ መስጊድ ስለ አላህ ስም ተብለው በሚደረጉና የዚህን ሃይማኖት ጠላቶች እና ወራሪዎች ለመቀልበስ በሚደረጉ ጀሀዶች ውስጥ ሚና ነበረው። ከነብያቶች ሀገር ከፍልስጥኤም የወጣው የተባረከው ኢንቲፋዳ የተጀመረው በየትም ሳይሆን በመስጊድ ውስጥ ነው፤ የመስጊድ አብዮት ተብሎ የሚታወቀው የመጀመሪያ ጥሪው የቀረበውም ከመስጊድ ማማ ላይ ነው። መስጊድ በአፍጋኒስታኑ ጀሀድም ሆነ በእያንዳንዱ እስላማዊ ጀሀድ ውስጥ የተጫወተው ሚና የማይካድ ነው።
(ይህን ፋትዋ በሚከተለው የመረጃ ገፅ ሊያገኙት ይችላሉ። www.qaradawi.net/site/topics/article.asp; www.islamonline.net/servlet/Satellite )

 

የቃርዳዊ ፋትዋ የተመሠረተው በእስላማዊው ሸሪዓ ላይ ሲሆን ጥቃትን በመቃወም ስም ለሚደረገው አመፅ ግልፅ አመራርን የሚሰጥና ቁርጥ ባለ ንግግር ለድርጊቱ የሚያቻኩል ነው። ቃርዳዊ እንደሚለው ከሆነ መስጊድ እንደዚያ ያለ ስፍራ ነበረ፤ እንዲያም ሆኖ ይቀጥላል፣ ማማዎቹም የጀሀድ ጥሪ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ። ግን ለምን?

መላው ዓለም መስጊድ ነው

መሐመድ ምድር ለእርሱ ንፁህ (እንደ መንፃት ሥርዓታቸው) እና መስጊድ ሆና እንደተሰጠችው የተናገረ ሲሆን፤ በሌላ ዘገባ እንደ ተነገረው ደግሞ ዓለም በሞላ ለእርሱ የማያስፈልገው ነገር የተወገደላት እና ንፁህ መስጊድ ሆና ታውጃለታለች። ይህ የመሐመድ አባባል የተዘገበው ስመ-ጥር የሐዲስ ምሑራን እና የተከበሩ ባለሥልጣናት በሆኑት በቡካሪና በሙስሊም አማካይነት ነው። (ይህ የሚገኘው በሐዲስ #31901፣ ካንዝ አል ኡማል ላይ ነው።)

ይህንን ቃል በቃል ስንረዳው መሐመድ እና ተከታዮቹ መላውን ዓለም ድል ነስተው፤ አጥርተውት ከየትኛውም ዓይነት ካፊር (ከሀዲ) ያፀዱታል ማለት ነው። ስለዚህ የመስጊድ ተልዕኮ ወይም ተግባራት ለፀሎት እና የሃይማኖት ተግባራት ከመዋል ባለፈ ምድርን በእስላማዊው አገዛዝ ስር ለመጣል የሚዘረጋ አካላዊና ተግባራዊ ሚና ይጫወታል።

ሙስሊሞች እስልምና ዓለም-አቀፍ ተልዕኮና ለሰው ዘር ሁሉ የሚታወጅ መልዕክት ያለው ዓለም-አቀፍ ሃይማኖት እንደሆነ ያምናሉ።

(ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው፡- «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ። (እርሱም) ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ የኾነ ነው። እርሱ እንጂ ሌላ አምላክ የለም። ሕያው ያደርጋል። ይገድላልም። በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ። ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት።» (ቁርአን 7.158)

አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም። (ቁርአን 34.28)

ቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ)» በላቸው። ለእነዚያም መጽሐፍን ለተሰጡት ሰዎችና ለመሐይሞቹ፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው። ቢሰልሙም በእርግጥ ተመሩ። እምቢ ቢሉም በአንተ ላይ ያለብህ ማድረስ ብቻ ነው። አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው። (ቁርአን 3.20)

እስልምና “የአላህ ብቸኛ ሃይማኖት” ነው ተብሎ ዓለም-አቀፋዊነት እንዳለውና ሙስሊሞችም ዓለምን ሁሉ በእስልምና አገዛዝ ስር ማምጣት እንደሚገባቸው ያምናሉ።

ለእስልምና በመገዛት ላይ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ወደ እስልምና የመለወጥ ምርጫ ይሰጣቸዋል፤ አለዚያ በየወቅቱ በሕዝብ ፊት የሚከፈል ከፍተኛ ግብር የመክፈል ግዴታ ይጣልባቸዋል። ይህንን ግብር በሚከፍሉበት ወቅትም የማያምኑ በመሆናቸው ምክንያት ግብር ተቀባዩ በእጅጉ ያሸማቅቃቸዋል። ከፖለቲካው አንፃር ሙስሊም ያልሆኑት ሰዎች እኩል መብት የማይኖራቸው ሲሆን እንደ ቅጥር፣ የመኖሪያ ቤት፣ የሥልጣን ሁኔታ እንዲሁም ተመሳሳይ ጉዳዮችም ላይ ሙስሊም ከሆኑት ጋር አንድ ዓይነት መብት የላቸውም። ይህ እስላማዊ ስርአት ሲሆን ክርስቲያኖች በቁጥር አነስተኛ በሆኑባቸው እስላማዊ ሀገራት ሁሉ ለ14 ክፍለ ዘመናት ያህል ልማድ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ አገዛዝ የእስልምና ፖለቲካዊ ቁጥጥር ተቀዳሚና ዋነኛ ዕውቅና የሚያገኝበት መንገድ ስለ ሆነ የበላይነቱ ተጠብቆ መቆየት ይኖርበታል።

በቀጣይነትም ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ስፍራ በመሆን የበላይነት የሚሰጣቸው መስጊዶች በሁሉም ስፍራ ይገነባሉ። በእስላማዊ ሀገራት ውስጥ ሌሎቹ እምነቶች መታወጅ የማይችሉ ናቸው፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን ያሉ የአምልኮ ስፍራዎችም ከመገንባት ይታገዳሉ፣ በዚያም ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ስለሚደረግባቸው ተግባራቸው የተገደበ ይሆናል።

በዚህ ዓይነት መልኩ መስጊድ የሕዝቡ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ መታወቂያና ምልክት ይሆናል።

አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው። እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች በመካከላቸው ላለው ምቀኝነት ዕውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጅ አልተለያዩም። በአላህም አንቀጾች የሚክድ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው። (ቁርአን 3.19)

በሰማያትና በምድር ያሉ ሁሉ፤ በውድም በግድም ለርሱ የታዘዙ ወደርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ (ከሓዲዎች) ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? (ቁርአን 3.83)

ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈፅሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው። (ቁርአን 3.85)


ምድርን ለማንፃትና በእስልምና አገዛዝ ስር ለማድረግ ሰዎቹ በጀሀድ እንዲሳተፉ መሐመድ አዘዘ። የዚህ ድርጊት ዋነኛ ምክንያትም እስልምና ዓለምን እስላማዊ የሆነና ያልሆነ ብሎ መክፈሉ ነው።

ለዚህ ሁኔታ የተሰጠው አጠራር ዳር አል ኢስላም የሚል ሲሆን፣ ትርጉሙም የእስልምና ቤት ወይም መኖሪያ ማለት ነው።

እስላማዊ ላልሆኑ የዓለም ክፍሎች የሚሰጠው ዳር አል ሀርብ የተሰኘ ስያሜ የጦርነት ቤት ወይም መኖሪያ ማለት ነው። ነገር ግን መላው ዓለም ሁሉ ለመሐመድ መስጊድ ሆኖ ስለ ተሰጠ ሊነፃና የእስልምና የበላይነት ፍፁም ወደ ሆነበት አገዛዝ ሊለወጥ ይገባዋል።

ለእስልምና መሰራጨት አስተዋተፅ ያደረጉ መሠረታዊ ገንቢዎች

እስልምና በእስላማዊ መሬቶች (ዳር አል-ኢስላም፣ የእስልምና ቤት፣ ሙስሊሞች ፖለቲካውን የተቆጣጠሩበት ስፍራ) ላይ የሚኖሩ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን የሚያስተዳድሩበትን መንገድ እና ሕጋዊ ዘይቤ ያዘጋጁ ሲሆን፣ እነኚህ ሰዎች የሙስሊሙን ኅብረተሰብ በማይነኩበት ሁኔታ ለደህንነታቸው ከለላ የሚመስል ነገር ተደርጎላቸው በተለየ ነገር ግን መድልዎ በሚታይበት ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ።

ሆኖም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ፖለቲካውን በተቆጣጠሩበት ስፍራ (ዳር አል-ሀርብ፣ የጦርነት ቤት) የሥራ ድርሻው የተለየ ነው። ዳር አል-ሀርብን ወደ ዳር አል-ኢስላም የመለወጥ የፍፃሜ ግብ ቢኖራቸውም እንኳ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፃተኛ በሆነበት ሀገር እንዲያድግ የማድረግ ተቀዳሚ ግብን ያስቀድማሉ። ዓይነተኛ የመድረሻ ግብ የሚሆነው የተወሰኑትን ዓይነት የሸሪዓ ሕጎች (ለምሳሌ፦ የአለባበስ ስነ-ሥርዓቱን፣ በጋብቻ እና በውርስ ላይ ያለውን የሸሪዓ የቤተሰብ ሕግ) ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በዚህኛው ክፍል እስልምና ሊሰራጭ እና እንዲህ ባሉ ስፍራዎች ሊዋሀድ የሚችልባቸውንና የዋና ዋናው ሂደት ማዕከል መስጊድ የሚሆንባቸውን ገንቢ አካላት እንመለከታለን። እነዚህ ገንቢ አካላት (ሀ) ለጀሀድ የሚደረግ ጥሪን፣ (ለ) እስላማዊ ወዳልሆኑ መሬቶች መሰደድን እና (ሐ) የሙስሊም ማኅበረሰቦችን ድብቅ አጀንዳ ሸፍኖ ለማቆየት የተቂያ ን መሠረተ-እምነት ተግባራዊ ማድረግ ናቸው። “ገንቢ አካላት” ብለን የምንጠራቸው የእነዚህ አካሄዶች ቅደም ተከተል እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ የሚወሰን በመሆኑ ነው። መሐመድ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ተነፃፃሪ ጥንካሬ ላይ በመመሥረት እንደየአስፈላጊነቱ ፈጣንና ዝግተኛ አካሄዶችን ተጠቅሟል።

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

ብዙ ሰዎች ስለ መስጊዶች ያላቸው አመለካከት አሁን በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከምናገኘው በጣም የተለየ ነው፡፡ ስለዚህም መስጊድ የሃይማኖት እምነት ማዕከል ይመስላቸዋል እውነታው ግን ከዚያ በጣም የራቀ ነው፡፡

ዝርዝር ውስጥ ሳንገባና የተባለውን ሳንደግም አንባቢዎችን የምንጋብዘው፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወደ ሆነች ቤተክርስትያን እንዲመጡና በዚያ ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት እና እንቅስቃሴ በቅንነት እንዲመለከቱና ነገሮችን በማስተዋል እንዲያመዛዝኑ ነው፡፡

ቤተክርስትያን የፖለቲካ መድረክ ልትሆን አትችልም፣ ለዚያም ዓይነት እንቅስቃሴ አልተመሰረተችም፡፡ ቤተ ክርስትያን በ1ጢሞቴዎስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 15 እና 16 ላይ እንደተገለፀው፤ “ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” ናት፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊዋ ቤተ ክርስትያን፣ የእውነት መሰረት የሚገኝባት ቦታ ናት፡፡ እውነት የሆነው እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፣ ምን ዓይነት ባህርይ እንዳለው፤ እንዲሁም ለሰዎች ልጆች የገለፀው የፍቅር ዓላማ የሚነገርባት ቦታ ናት፡፡

ቤተ ክርስትያን የእውነት መሰረትነቷ የሰውንም ልጅ መሰረታዊ ችግር የምትገልጥ ስለሆነች ነው፡፡ ሰው ምንድነው? የሰው ልጅ አሁን የሚያሳየውን ባህርይ ማለትም፣ ጥላቻ፣ ግድያ፣ ምቀኝነት፣ ስርቆት፣ ፍቺ፣ ውስጣዊ ስቃይና ሰቆቃ ባለው ሕይወት ውስጥ የሚኖረው ለምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎችን መልስ ትሰጣለች፡፡ ሰዎችም በግላቸው ለየራሳቸው ጥያቄ  ዘለቄታዊ የሆነ መልስ የሚያገኙባትና መንፈሳዊ እርካታን የሚረኩባት የእውነት መሰረት ናት፡፡

ቤተ ክርስትያን ጦርነት የሚታወጅባት ቦታ ሳትሆን ጦርነት የሚሰረዝባት፣ የተጣሉ የሚታረቁባት፣ ሰላምና እረፍት ፍቅርም የሚታወጅባት ቦታ ናት፡፡ ከዚህም ባሻገር ቤተክርስትያን ሰዎች የዘላለምን ሕይወት ማለትም መንግስተ ሰማይን የሚወርሱበትን የነፃ ስጦታ በክርስቶስ አማካኝነት የሚተዋወቁበት ቦታ ናት፡፡

አንባቢዎች ሆይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቤተክርስትያን ጎብኙና በየዕሁዱ የሚሰጠውን ትምህርት በቅንነት አዳምጡ፣ ምናልባት እግዚአብሔር ለዘላለማዊ ሕይወታችሁ የሚጠቅምን ነገር ይሰጣችሁ ይሆናልና፡፡

 

ወደ ማውጫው መመለሻ

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ