ወደዚህ ገጽ እንኳን ደህና መጡ!

መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ቁጥር 3፡16 እንዲህ ይላል : “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና”። በዚህ መሠረት፣ የኢየሱስን የማዳን ስራ ለሚቀበሉ ሙስሊሞች የዘላለም ህይወት አለ ነው። የዚህ ገጽ ዓላማ ሁለት ገፅታ ያለው ነው። የመጀመሪያው ዓላማ ክርስትያኖች ለእስላም ወገኖቻቸው ወንጌልን የማድረስ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ መርዳት ሲሆን ፣ ሁለተኛው ዓላማ ደግሞ እግዚአብሔርን ለማግኘት በመፈለግ ላይ ያሉ እስላሞችን ወደ እውነት እንዲመጡ መርዳት ነው።

በሐዋርያት ስራ 17:23 እንደተፃፈው፣ ጳውሎስ በአቴና ያሉ ሰዎች "የማይታወቅ አምላክ" ሲያመልኩ አግኝቶ፣ ይህ እነርሱ "የማይታወቅ አምላክ" የሚሉት እራሱን በኢየሱስ እንደገለጸ እየተናገረ የምስራቹን ወንጌልን ሰብኳል። ተመሳሳይ ሁኔታ በሙስሊም ወገኖቻችን ዘንድ እናገኛለን። ማለትም እነሱም እግዚአብሔር የማይታወቅ፣ ከፍጡራኑ እራሱን ያራቀና የለየ ነው ብለው ያምናሉ። ክርስትና ግን እግዚአብሔር ለኛ ለፍጡሮቹ ቅርብና ከእኛ ጋር ግላዊ  ግኑኝነትን የሚፈቅድ፣  አባታ ሆይ ብለን ልንጠራው የምንችል እንደሆነ ይነግረናል። በተጨማሪ እኛ ክርስትያኖች ፀሎታችንን እንኳን ስንጀምር አባታችን ሆይ ብለን ነው። ይህን ውብ የሆነ ግንኙነት የማግኘት እድሉን ሙስሊም ወገኖቻችን ቢጠቀሙ እንዴት ደስ ያሰኛል። ነገር ግን እነርሱ ከአምላካቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደ ጌታና ባርያ መሆን አለበት ብለው ያምናሉ። ለመፅደቅም ራስን አስገዝቶ ህጎችን መከተል ብቻ በቂ ነው ብለውም ያምናሉ። "ኢስላም (Islam)" የሚለው ቃል ምንጭ እንኳን  ሲተረጉም ራስን ወይም ስሜትን ረግጦ ማስገዛት ማለት ነው።

በማቴዎስ ወንጌል ቁጥር 28:19-20 የኢየሱስ የመጨረሻ ትእዛዝ ክርስትያኖችን “ሂዱና ወንጌልን ስበኩ ፣ ዓለምንም ሁሉ ደቀመዛሙርት አድርጉ” ይላል። ወንጌልን በኢንተርኔት ማካፈል ዓላማችን ነው፤ የክርስቶስንም ሕዝብ ለእስላሞች የመመስከር ብቃትና ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ለመርዳት ፍላጎታችን ነው። እስላም ወንድምና እህቶቻችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እውነትና የዘላለም ህይወት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ለጥያቄዎቻቸው በዚህ መድረክ መልስ እንዲያገኙ እንሻለን።

በዚህ ፕሮጀክት ተሳትፎ ማድረግ ከፈለጉ፣ ጥያቄዎች ወይም አስተያየት ካለዎት፣ ወይም ጠቃሚ መረጃዎችን ሊልኩልን ከፈለጉ ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን። በቅርቡ ብዙ ተጨማሪ ጠቃሚ መረጃዎችን በዚህ ገጽ ስለምናደርግ፣ በየግዜው ይጎብኙን።

የኢሜል አድራሻ: melseleeslam(at)googlemail.com

ለእስልምና መልስ የአማርኛ ቡድን።

Welcome to Answering Islam Amharic 

The bible says "For God so loved the world that he gave his one and only Son, that whoever believes in him shall not perish but have eternal life" (John 3:16). In this regard, eternal life is what is available for muslims who accept the saving work of Christ.

The main purpose of the Amharic section of Answering Islam is two-fold.Firstly, we want to present the truth to Muslims so that they may understand the gospel and come to know the truth. Our second objective is to equip Christians in being effective witnesses to muslims. As we find in Acts 17:23 Paul discovered that the people in Athens worshiped the ʽunknown godʼ and it is in this regards that he preached the gospel to them telling them that the god they worship as the unknown has revealed himself through Christ. Likewise, we find the same occurrence with our Muslim friends. That is to say, their view of God is one of unknowable, distant God who is separate from his creation. Yet Christians affirm that God is relational and that we call him father and could know him personally. Moreover, the Lord's prayer starts by the affirmation of ʽOur Fatherʼ and this is what Muslims could experience. However, Muslims' perception of their relationship with God is one of a slave and master; what is required of Muslims is just to obey and submit (as the word Islam itself means that.)

The last instruction of Jesus, as found in the Gospel of Matthew (28), is to go into all the world and make disciples of all nations. We aim to share the gospel through the internet, to equip the body of Christ into being an effective witness to Muslims and to help Muslims to find answers to the question they may have in order that they will encounter the truth found in Jesus Christ.

 It would be good to hear from you, be it related to a question or a comment you would want make. In the near future we are going to have more materials uploaded and we would encourage individuals who are interested in contributing materials of relevance to contact us.

The Amharic team of Answering Islam

 Email Us:    melseleeslam(at)googlemail.com