አጫጭር ዜናዎች

 

በኢራን ክርስትያናዊ ቅርሶችን የማጥፋት ዘመቻ

የክርስትና ቅርሶችን ከኢራን ለማጥፋት በሚደረገው ዘመቻ ብዙዎቹ  ወድመዋል!

ክርስትያናዊ ታሪካዊ ቅርሶችን ፈፅሞ ለማጥፋት በሚደረገው ከፍተኛ ጥረት ታሪካዊ የክርስቲያን ቅርሶች እንዲደመሰሱ ወይም እደሳ ሳይደረግላቸው እንዲፈራርሱ የኢራን ባለስልጣናት ጥረት እያደረጉ ነው። ቅድመ-እስልምና ቅርሶች፤ቤተ ክርስቲያንና የክርስቲያን የመቃብር ቦታዎች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ሲሉ ባለሙያዎች  ያሳስበሉ። በዚህ ወር መጀመሪያ የኢራን የክርስቲያን የዜና ወኪል እንዳስታወቀው ከ200 አመት እድሜ በላይ የሚሆነውን በጋል እ ዶክታር  በክርማን ክልል የሚገኘውን የክርስቲያን መቃብር ቦታን ካለባለቤቶቹ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ደምስሰውታል። መሐመድ አፍዛሊ ከባህልና ቅርሳ ቅርስ ድርጅት ሲናገር እንደተደመጠው «የዚህ የመቃብር ቦታ ድምሰሳ የማዘጋጃ ቤት፣ የባህልና ቅርሳ ቅርስ ድርጅት ከእቅዶች አንዱ አካል ሲሆን በጋል እ ዶክታር  በጋል እ አርድሸር አካባቢ ቦታ ለማስፋት ነው» በማለት ነው።

ይህም የሆነው በዚሁ በክርማን የቅዱስ እንድሪያስ ቤተክርስቲያን ከተደመሰሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው።.  የቤተክርስትያኑ ህንፃ የብሔራዊ ቅርስ እንዲሆን በማርች 2009 እውቅና አግኝቶ ነበር፣ የ60 ዓመት እድሜ ያለው ህንጻ እድሳትና ጥበቃ ይገባዋል የሚባለው ደረጃ የነበረውም ቢሆን በአንድ ምሽት ነበር በማረሻ መኪናዎች አፈር የተደረገው። ቀደም ብሎ ቤተክርስቲያኑ ወደ ታክሲ አገልግሎት ቢሮነት ተቀይሮ ነብር።

በሳልማስ ክልል የሚገኘው የሃፍትቮን ቤተክርስቲያንም በተደጋጋሚ ጥቃት ደርሶበታል በመፈራረስም አደጋ ላይ ይገኛል፡፡ እርሱም በ2002 እንደ ብሔራዊ ቅርስነት የተመዘገበ ቢሆንም ሳይታደስ እንዲበሰብስ ስለተተወ እፀዋቶች በህንፃው ላይ በመብቀላቸው መሰነጣጠቅ አስከትሎበታል። ተላላፊዎች ቤተክርስያኑን መዝብረውታል የተደበቀ ቅርስም ፈላጊዎች ግቢውን ቆፍረው አፈሩ እንዲሸረሸርና የቤተክርስቲኑ ግርግዳ እንዲዳከም አድርገዋል።  

አንድ ክርስቲያን ከሳልማስ እንዳለው «የእስላሚክ ሪፑብሊክ የክርስቲያን ቅርሶችን በተግባር እያወደመ ነው። ይህም በሃፍትቮን ብቻ አይደለም፤ በአሽናክ መንደርም የሚገኝ ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ወይም ከዚህ የሚብስ ሆኖአል፡፡ የዚህም ምክንያቱ አንዳንድ ተላላፊዎች የመንግስቱ ባለስልጣናት የሆኑት መዝብረውታልና ነው። የእስላሙ አገር ሕጐች እነዚህ ቅርሳ ቅርሶች እንዳይደመሰሱ ፈጽሞ አይከላከልም።»

ከ1850 ጀምሮ በቡሽህር በሚገኘው የመቃብር ቦታ ያሉ ትላላቅ መስቀሎች ከመቃብር ድንጋዮች ላይ ተወስደው አሁን ቦታው የፈራረሰና በሳር የተሸፈነ ሆኖአል።

ሞሃባት ዜና እንዳለው «የእስላሚክ ሪፑብሊክ ባለስልጣናት፤ ህዝቡን በማስጨነቅ፣  በማሰር፣ ወደ ክርስትና የተቀየሩ አማኞች ቤተክርስቲያን እንዳይሄዱ ቢከለክሉም የክርስትናን እድገት ከህዝቡ መካከል ለማቆም ያልተሳካላቸው አስመስሎታል። ስለዚህም ፍላጐታቸው ከኢራን ምድር አገሪቱን ከክርስትና ጋር የሚያይዙዎትን ታሪካዊ የሆኑ የክርስትና ቅርሶችን ፈጽሞ ማጥፋት ነው።»

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

እስላማዊ አገዛዝ ባለባቸው አገሮች ውስጥ ያሉ ክርስትያኖች የሚሰቃዩት ስቃይ ከመነገር ያለፈ ነው፡፡ በሕይወት ያሉት ክርስትያኖች ይቅርና ከክርስትና ጋር የተያያዙ ታሪካዊ ሕንፃዎችና የመቃብር ቦታዎችም ለመደምሰስ የተፈረደባቸው ሆነዋል፡፡ ይህ በኢራን የምናየው በሌሎችም የእስላም አገሮች ውስጥ የሚከናወን ነው፡፡ ኢትዮጵያም በእስላም አገዛዝ ስር ብትወድቅ ከዚህ የተሻለ ዕድል ሊኖራት እንደማይችል አመላካች ነው፡፡

ይሁን እንጂ ሙስሊሞች ክርስትናን እንደዚህ የሚጠሉት ስለምንደነው? ክርስትያኖች ለሙስሊሞች ጥላቻ የላቸውም ስለምን ሙስሊሞች ክርስትናን ይጠላሉ? ስለምን ሙስሊሞች የሰውን የመረጠውን የማመንና የማምለክ መብት ይገፍፋሉ? እምነታቸውን ስለማያምኑበት፣ እምነታቸው ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስን ሊሰጥ አይችልም ብለው ስለሚፈሩ ወይንስ በእምነታቸው ላይ እምነት ስለሌላቸው ነውን?

አስገራሚ አስተያየት፡

የሞሃባት ዜና አቅራቢ በኢራን የታዘበው ነገር አስገራሚ ነው፡፡ የኢራን ባለስልጣናት በረቀቀው የመረጃ አውታራቸውና የጭከና ግድያቸው እንዲሁም የክርስትናን ስምና ማህተም የያዙትን ነገሮች ሁሉ ለማጥፋት ቢጥሩም ሰዎች ክርስትያን እንዳይሆኑ ማድረግ አልተቻላቸውም፡፡

በየአገሩ እጅግ ጥብቅ እስልምናም ባለበት አገር ሁሉ የጌታን የኢየሱስን የማዳን ወንጌል በመስማት ወደ ጌታ የሚመጡት ቁጥር ከአዕምሮ በላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች ክርስትያን የሚሆኑት ተገደውና ተደልለውም አይደለም፡፡ ሰዎች ክርስትያን ሲሆኑ የሚያገኙት አዲስ እና የዘላለም ተስፋ ያለው ሕይወትን ነው፡፡ ሰዎች ክርስትያን ሲሆኑ እውነት ገብቷቸው ነው፣ ክርስትያን ሲሆኑም ስደትንም ጥላቻንም ንቀትንም ግድያንም እንኳን ስለ እምነታቸው ሲሉ ለመቀበል ነው፡፡

ዘለቄታ ያለው እውነት፡

የክርስትና እምነት በእስላሞችና በሌሎችም ስደት ይጠፋልን? የክርስትናን እምነት ለማጥፋት እጅግ ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል አሁንም አሉ፡፡ ክርስትና እምነት በእግዚአብሔር የተጀመረና በእግዚአብሔርም የተጠበቀ ነው፡፡ አማኞች ቁጥራቸው ሊቀንስ ይችል ይሆናል እምነቱ ግን በፍፁም አይጠፋም፡፡ ምናልባት አሁን በፈረሱት ታሪካዊ ቤተክርስትያኖች ምትክ ሌሎች ባይሰሩም እንኳን ታላላቅ መስጊዶች የወንጌል መስበኪያ ቦታዎች እንዲሆኑ እየተሰሩ ይሆንን? ሳይሆን አይቀርም ለእውነተኛው እግዚአብሔር የሚሳነው የለምና፡፡ አሁንም በዚያን ጊዜም የክርስትና የፍቅርና የነፍስ ማዳን መልእክት ጌታችን ኢየሱስ እስከሚመጣ ድረስ ይቀጥላል፡፡

የዜና ምንጭ: Monuments destroyed in bid to wipe out Iran’s Christian heritage

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ